ዕዉነት እና ለነፃነት የምንኖረዉ መቸ ይሆን ? –

July 28, 2022

ዓለማችን በዉሸት እና ክህደት እንድትሞላ  የሚሰሩ መሰሪዎች መሞላቷ ድንቅ እና ብርቅ ባይሆንም ከክፉዎች ደግነት ፤ ከከኃዲዎች መታመን አለመማር ግን ዓለም በጥርጣሬ እንድትታይ አድርጓታል፡፡

ዕምነትም ሆነ ሠዉነት ከሰባዊነት የሚቀዱ ሆነዉ ሳለ በዓለም ላይ ክቡር የሰዉ ልጆች ህይወት እና ደህንነት በግፍ እና በማን አለብኝነት ሲነጠቅ እያዩ እንዳላዩ የሚሆኑ የሠላም እና ሠባዊ መብት ሀዋርያ እና ፊዉታራሪ ነን የሚሉት ሀገራትም ሆነ መሪዎች ፣ የሠባዊ መብት ባላ አደራ ነን ባዮች…… ቦታ ፤ ጊዜ እና ሟች እያዩ  የአዞ ዕንባ የሚያነቡ በዝተዉባት አስመሳዮች በሰባዊ ቀዉስ እና ትርምስ ዘመናቸዉን ሲያራዝሙ ማየት በሰፊዉ የተለመደ ሆኗል፡፡

ሠባዊነት እና ተጠያቂነት በዕዉነት እና በዕምነት ሳይሆን ለግል እና ቡድን ጥቅም ማስጠበቅ በመዋላቸዉ ፍትህ እና ነፃነት የተነፈጉ የዓለማችን ህዝቦች ብዙዎች ናቸዉ ፡፡

በተለይም ወደ አፍሪካ ቀንድ የኛዉ አገር ስንመለስ በታሪክ እና በዘመናት ጅረት  የማይታወቅ  የዉርደት መገለጫ የሆኑት ድህነት ፣ ስደት ፣ ሞት እና ጅምላ ማግለል እና መግደል ከሶስት አሰርተ ዓመታት በላይ በህዘብ እና በአገር ላይ እንደ ድንጋይ ተጭኖና ከብዶ በዚህ በ21ኛዉ ክ/ዘመን ዘመናዊ ባርነት ተስፋፍቷል፡፡

ኢትዮጵያ ሆነች ህዝቧ ገጥሟቸዉ የማያዉቅ የመከራ  ግርዶሽ አንዣቦባቸዉ ይገኛል ፡፡  ይህ የጥፋት ግርዶሽ ኢትዮጵያ የነበራት የረጂም ዘመን ጥንተ መሰረት እና ታላቅነት ከታሪክ እና ትዉልድ ምልከታ ለመሰወር ታሪክ መበረዝ እና ትዉልድ መመረዝ ከጥፋት ስምምነት  የ1968 ስምምነት/ መኒፌስቶ የሚመነጭ መሆኑን ዓለም ሲያወቅ ይህም ሠባዊ እና ተፈጥሯዊ መብቶችን የሚገፍ መሆኑን በአስተሳሰብ እና በተግባር እየተመለከተ ከዉጭም ከዉስጥም በዝምታ አልፎታል፡፡

ኢትዮጵያን ለማፍረስ ፣ ማንነትን (ኢትዮጵያዊነት) ፣ ዓማራነት ፣ ባህል እና ዕምነት በጥላቻ ተፈርጀዉ የነፃነት ትግል መንስዔዎች ሆነዉ በኢትዮጵያ ምድር ነባር ባይተዋር ፤ ክሃዲ ባላገር ሲሆን ከዚያ አስከዚህ ዘመን ለምን የሚል ዕምነት እና ሠባዊነት አልተገኘም ፡፡

የአገር እና ህዝብ ጉዳይም ከግል፣ ከቡድን ፣ ከፖለቲካ እና ከህግ በታች ሆኖ ጨለማ ብርሀን ሲባል ዓሜን ከማለት ዉጭ ለዕዉነት እና ለዕምነት የሚኖር አልተገኝም ፡፡

በየትኛዉም የዓለም ክፍል እና አገር የማይደረግ የሰባዊ መብት ጥሰት ፣ የዜጎች ሞት እና ስደት ….. የዕለት ወሬ በሆነባት አገር ስለብዙኃን የሚናገር አንደበት በጠፋበት እየተመረጠ በግል፣ በሙያ ፣ በኑሮ ደረጃ……..ሠዉነት በመበላለጥ ሲለካ የሚታየዉ በኢትዮጵያ ነዉ ፡፡

የሰባዊ መብት ያሳስበናል የሚሉት አገራት ለጋዜጠኞች (ጀማል ካሾጊ) ሞት ፣በእኛም አገር በደቦ እየተመረጠ ፍትህ እና ሠባዊነት ሲለካ ማየት ያሳዝናል ፡፡

ጥላቻ እና ፍርኃት በወለደዉ ጭካኔ በማንነቱ ስለ ተሰደደ ፣ ስለሞተ እና ስለተዋረደ ህዝብ ወይም ክቡር የሠዉ ልጂ ህይወት ዕዉቅና እና ዋጋ መስጠት ያቃተን ስለ ዕምነት ፣ ሠባዊነት ፣ነፃነት እና ሉዓላዊነት እንዴት እና መቸ ልንናገር እንችላለን ፡፡

ግፍ እና ጉድፍ አይቶ እንዳላየ ማለፍ መለማመድ ክህደት እና አድርባይነት ያስከተሉት የክፋት ዉርስ ነዉ ፡፡

አገር ፣ ህዝብ  እና ብሄራዊ ሀብት እና ቅርስ ሲመዘበር ቆሞ የሚመለከት እና ያለማንም ከልካይ አገር የግፈኞች መፈንጫ እና ማላገጫ ስትሆን  ምንም የማይል በሌሎች ላብ እና ጥቅም አፉን የሚያላቅቅ ፤ በበጎ ነገር የሚጨነቅ አገሪቷን እንደተምች ወሯታል፡፡

አገር እና ህዝብ ከምንም በላይ ብሎ የግለሰብ ነፃነት በማይከበርባት አገር የብዙኃን ነፃነት እና መብት ዕዉን እንደማይሆን አዉቆ ለራሱ ፣ ለወገኑ እና ለአገሩ ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ ፣ የሚማልድ እንዲሁም ከህዝብ እና አገር ችግር በፊት የሚገኝ ለዕዉነት እና ነፃነት የሚኖር ትዉልድ እስኪፈጠር በማይናወጥ የአንድነት ህብረት በገራ ለእኛ እና ለአገራችን በዕምነት ፣በፀሎት እና በዓላማ አንድነት እና ጽናት ዘብ ልንቆም ይገባል፡፡

“ምንጊዜ ክብር ለኢትዮጵያ እና ህዝቧ  ”

NEILOSS-Amber

1 Comment

  1. ታሪክን በርዞ አዲስ ዲስኩር ጣፈ፤
    በራፉ ላይ ቆሞ ሃገሬና ምድሬ ይህችም ናት ያችም ናት ብሎ ተማማለ
    ወገኑን ገፍትሮ ጠላቱን አቀፈ
    እውነት ነጻነትን በከርሱ ለወጠ
    ጠግቦ የበላ እለት እልል ብሎ አደረ
    የበላው ሲጎድል ሊገድል ሊዘርፍ ከበራፉ ራቀ
    ውሸትን ሰንቆ ብዙ ሳይራመድ ጎዳናው ላይ ሞተ
    እውነትን ሳያውቃት ሄደ ተሻገረ ዝንተ ዓለም አረፈ
    እንዲህ ነው ወገኔ የእኛው ፓለቲካ
    የጠገበው ወርዶ የራበው ሲመጣ
    ለእውነት ለነጻነት የሚኖሩ የሉም
    ብዬ ለመናገር ድፍረቱ የለኝም
    ሰው ተመልሶ ለእውነት ለነጻነት ራሱን አግዝፎ
    ይኖራል አልልም የሚበላውና የሚያባላው ሞልቶ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

294687064 10229016690345401 4248275892395723478 n
Previous Story

ጠ/ሚ በጀርባ ሕመም ምክንያት ሕክምናቸውን በተባበሩት አረብ ኢምሬት እየተከታተሉ መሆኑ ተሰምቷል (ምንሊክ ሳልሳዊ)

adanech abebe
Next Story

የአዲስ አበባ ከተማ ኗሪነት መታወቂያ ማግኘት የገነት መግቢያ ቁልፍ እንደመቀበል በሚቆጠርባት አገር ኢትዮጵያ

Go toTop