ጠ/ሚ በጀርባ ሕመም ምክንያት ሕክምናቸውን በተባበሩት አረብ ኢምሬት እየተከታተሉ መሆኑ ተሰምቷል (ምንሊክ ሳልሳዊ)

July 28, 2022

294687064 10229016690345401 4248275892395723478 n

ጠ/ሚ በጀርባ ሕመም ምክንያት ሕክምናቸውን በተባበሩት አረብ ኢምሬት እየተከታተሉ መሆኑ ተሰምቷል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመርዘዋል ወይንም በጥይት ተመተዋል መባሉ ይታወቃል።

ለሳምንታት ቢጠፉም እያገገሙ ስለሆነ ብቅ ማለታቸው አይቀርም። ዘመቱ ከተባለ ከቀናት በፊት ነው ለሕክምና ከሃገር የወጡት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘምተዋል በሚል ነገሮችን ለማድበስበስ ቢሞከርም ሳይሳካ ቀርቶ ያሉበት ታውቋል። አገግመዋል ሰሞኑን ብቅ ይላሉ የተባሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንትና ተጽፎ የተለቀቀው ባለ ሶስት ገፅ የምስጋና መልዕክት የተዘጋጀው በዳንኤል ክብረት በሚመራው በሕዝብ ግንኙነት ሰራተኞቻቸው መሆኑ ታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቅ ከማለታቸው በፊት በአክቲቪስቶቻቸው በኩል አጀንዳ ይሰጣሉ ተብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሕዝብ ጥያቄና ብሄርተኛ በሆኑ የኦሮሞ ባለስልጣናትና ጄኔራሎች በሚፈጥሩባቸው ችግር መካከል አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልልቅ እንግዶችን አልተቀበሉም። በአትሌቶች የአቀባበል ስነስርዐት ላይም አልተገኙም ።

ምንሊክ ሳልሳዊ

7 Comments

  1. ምንሊክ እስከ ዛሬ የሚታወቀው በቀዳማዊና በዳግማዊ ብቻ ነው ያለው። ሳልሳዊ ኖሮ አያውቅም። ሳልሳዊ ፈጠራ ነው። እንደ ስሙ፣ የሌለ ነገር፣ ምኞቹን ይሞነጫጭራል።
    ~ ጠ/ሚ በጀርባ ሕመም።
    ~ ተመርዘዋል።
    ~ በጥይት ተመተዋል።
    ~ እያገገሙ።
    ~ ዘምተዋል።
    ~ የኦሮሞ ባለስልጣናትና ጄኔራሎች አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል።

  2. ሮጠው ኒሻን ለሃገራቸው ያገኙትንና ባጠቃላይ ተሳታፊ የነበሩትን ህብረ ብሄር አትሌቶች በተደረገ አቀባበል ላይ ንግግር ያሰሙት ወይዘሮዋ ፕሬዚደንት ሃገሪቱ እጅግ አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለች ከድሮው በበለጠ ሁኔታ አምርረው ተናግረዋል። እርግጥ ነው ሃገሪቱ በኦሮሞ ብሄርተኞችና በትግራይ ተገንጣይ ሃይሎች ትርምሷ እየወጣ እንደሆነ የየቀኑ ዜና ይናገራል። ግን የሚነገረንን ሁሉ ወሬ ሳያኝኩ መዋጥ መታመም ነው። ለምሳሌ የሰሜኑ ግጭት እንደ ተጀመረ ዶ/ር ደብረጽዪን ተገሎ አንድ የሰውነቱ ክፍል እዚህ ጋ ሌላው እዚያ ጋ ተቀበረ ብለውን ነበር። ግን ያ ሁሉ የሞት ምኞት ሳይሆን ቀርቶ አሁን እንሆ ዶ/ሩ አሜሪካንን ወይ አስታርቁን ያለበለዚያ ውጊያ እንከፍታለን እሰከማለት ደርሰዋል። ሲጀመር በሰው ሞት ደስ የሚለው ሰው ራሱ በቁሙ የሞተ ብቻ ነው። ቀጥሎ የወያኔ ዳግም ውጊያ እከፍታለሁ ማለት ረጅም ድላ ባይመቱበት ያስፈራሩበት እንጂ የትም የሚያደርስ ነገር አይሆንም። ወያኔ መጠራቅቅ ውስጥ ገብቷል። የትግራይ ህዝብ አክ እንትፍ ብሎታል፤ ሰራዊቱ በዚህም በዚያም አልቆበታል፤ አይዞህ ያሉትና በየሚዲያው ወያኔን ሲያገኑ የነበሩ ሁሉ አሁን ረስተውታል። ዓለም እንኳን የሃበሻውን የእርስ በእርስ መፈናከት ቀርቶ የራሺያና ዪክሬንን ፍልሚያም ሽፋን መስጠት ቀንሰዋል አንዳንዶች ደግሞ ጭራሽ አቁመዋል። ዓለም ወረተኛ ናትና!
    አሁን ዶ/ር አብይ ወገቡን ታሞ በጥይት ተመቶ ገለ መሌ የሚለው ሁሉ የመላ ምት ዜና ነው። ግን ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በህመም ሞተ የሚለውን እንደማልቀበለው ሁሉ አፍሪቃ ውስጥ በአስተሳሰብ የላቀ መሪ ብቅ ሲል በአጭር መቅረቱ በሃጉሩ ውስጥ በተደጋጋሚ የታዬ ጉዳይ ነው። ተመርዘው የተገደሉ፤ በግርግር መካከል በጥይትና በስመ መፈንቅለ መንግስት ግባዕተ መሬታቸው የተፈጸሙ ብዙ ናቸው። እውቁ የፍልስጤም ታጋይ ያሲር አራፋት በፕሎኒዪም ተመርዞ እንደሞተ በሳይንሳዊ ምርመራ ተደርሶበታል። ግን ማን መርዙን ሰጠው ለሚለው ጥያቄ ግን እስከ ዛሬ ድረስ መልስ የለም። አንድ በመጀመሪያ ደረጃ በፈረንሳይ የአረፋትን ምርመራ ያካሄደ የህክምና ባለሙያ ጋዜጠኛ ለጠየቀው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ” መልሱ ያለው ከፓለቲከኞች ነው። እኔ መናገር አልችልም ነበር ያለው”። ጠ/ሚሩ ያገኘውን ሲያቅፍ፤ አላፊ አግዳሚውን ሲጨብጥ ተከፍሏቸውም ሆነ በዘር ፓለቲካ ሰክረው ችግር ሊፈጥሩ እንደሚችሉ መገመት ነበረበት። ይህም ተባለ ያ ጠ/ሚሩ ከህዝብ ፊት መጥፋቱ መልካም ነገር አይደለም። የጀርባ በሽታም የለውም። ያው የመሸፈና ብልሃት ይሆናል እንጂ። ጠ/ሚ መለስ ዜናዊስ ሥራ ይጀምራሉ እያሉን አይደል እንዴ ሞታቸው የተሰማው። ያለንበት ዓለም ምንም የሚያስተማምን ወሬ የለውም። ስለሆንም ይህንም ያንም ወሬ እየቃረሙ የልብ በሽታና ቃር ከመሸመት መሽቶ ሲነጋ የሚሆነውን እውን ነገር መጠበቅ መልካም ይመስለኛል። በቃኝ!

  3. You are right Ato Yohannes,
    Cadres sell their country, friends and even their families for money and dirty bellies. We saw these under the Dergue and the Woyane and now getting worse under the Oromo-led Abbay dictatorship, Abbay who was also the Woyane loyal cadre from his 14 years old.

  4. ለአቢይ አህመድ እሥር ሽፍታዊ አፈና
    ይገባል ውዳሴ ስባሔ ምስጋና
    ኢትዮጵያን ለማየት የሰው ቄራ ሆና
    በመታደላችን እናቅርብ ምስጋና
    ማን ያርደን ነበረ ባይኖርልን ኖሮ ኦነግ ብልጽግና
    ሕፃን ሽማግሌ እርጉዝና ጨቅላ
    የሚጨፈጭፈው ሁሉን ሳያዳላ
    አንደኛ ለወጣው ሬሳን በመደመር
    ምስጋና ይድረሰው እጅን በማጣመር
    አዎ እጅ ይጣመር ከቀኝ ወደ ግራ
    ልብን ይጫን ደግሞ
    ጭ..ጭ ምጭ..ጭ እንዲል መምታቱን አቁሞ
    አይሻለውም ወይ ትር ትር እያለ ከመጠባበቁ
    የአቢይ አህመድ ጭፍራ የወሃቢን ስለት እስኪሞሸልቁ
    እይሻለውም ወይ ራሱን መሸኛኘት እንዲህ በምስጋና
    እስኪቀብር ከመዋል የጅምላ መቃብር ምሶ ብልጽግና።

  5. ተችዎችን ሳላስቀይም የወገብ በሽታ ክፉ ነው የደረሰበት ያውቀዋል የሚቀርባቸው ካለ ይህንን አጭበርባሪ ፓስተሮች ወዲያ ብለው ለአምላክ የቀረበ ቄስ በመስቀል ቢባርኬቸው ቀውስ ዬገኙ ነበር ጁዋርና ሽመልስም ሞታቹውን አዬፋጥኑም ነበር። እንግዲህ ፕሮፌሰር ስዩም የሚተረተረውን እየሳቁ ማድመጥ ነው።

  6. አለም፣ ተስፋ፣
    መቼም ቢሆን የኦሮሙማ ስርአት እስካለ ድረስ አብይ ኖረም አልኖረም ክፍያችሁ ስላምይቀርባችሁ ተረጋጉ፡፡
    በተለይ ተስፋፕሬዝዳንት ተብየዋን የደፍክ መስለህ እዚያው “ሁሉን ነገ ሳያኝኩ መዋጥ መታመም ነው ብለሀቸዋል፡፡ ይህም አካሄድህ ንቁ የአብይ አህመድ ተከፋይ ተቺወች ቁንጮ ያደግሀል፡፡
    እውነቱ ግን ይህ ነው፡፤ ተመዝኖ ቀልሎ የተገነው አብይ አህመድ በህይወት ኖረ አልኖረ ስርአቱ ተመልሶ እንዳይስተካከል አድርጎ አበለሻሽቶታል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ዘብ ይቁም በቦታው ነው መዝሙሩ!!!

    • ዲንቁ – ናና ገንዘቡን አቋጥረኝ። ወረኛ የወያኔ ሾተላይ። የሙታን የብሄር ታጋይ። አሁን ምን ልትሉ ነው ሰውዬው ከነበረበት ብቅ ብሎ አለሁ ሲል? የፈጠራ ወሬን ከማውራት ዝምታ አይሻልም ነበር? እኔ የማንም ደጋፊ አይደለሁም። ልሆንም አልችልም። ግን ድመቷ ከሌለች አይጧም በጊዜዋ ትጫወታለች ስለሆነ ሰውን ጭቃ መቀባት ልማዳችሁ ነውና ያላችሁትን በሉ። የአሻሮ ጥርቅም!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

296035908 5641361102611291 7571467774394405913 n
Previous Story

የደስታችን ምንጭ ሜዳሊያው ብቻ ሳይሆን አትሌቶቻችን ኢትዮጵያን አሸናፊ ለማድረግ ያሳዩት ትብብርና ህብረት ነው- ሻለቃ አትሌት ኃይሌ

Ethiopia 1 1
Next Story

ዕዉነት እና ለነፃነት የምንኖረዉ መቸ ይሆን ? –

Go toTop