July 25, 2022
22 mins read

“ጉርጥ አደፈጠም ዘለለም ፤ ያው ጉርጥ ነው“ እና ከእውነት ጋር እንታረቅ – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Ethiopia
An Eritrean refugee woman seats with a child at the door of a house at Mai Aini Refugee camp, in Ethiopia, on January 30, 2021. - Eritrean refugees in Ethiopia fear their suffering may not be over, as Prime Minister Abiy Ahmed strains to end a brutal conflict in the northern region of Tigray that has rendered them uniquely vulnerable. Nearly 100,000 refugees from Eritrea, an oppressive, authoritarian nation bordering Ethiopia to the north, were registered in four camps in Tigray when fighting erupted in November between Abiy's government and the regional ruling party, the Tigray People's Liberation Front (TPLF). (Photo by EDUARDO SOTERAS / AFP) (Photo by EDUARDO SOTERAS/AFP via Getty Images)

በኢትዮጵያችን ማንኛውም አገር ወዳድ ዜጋ ፣   በልቡ ውሥጥ ያለውን ንፁህ እውነት ፣ ሳይፈራና ሳይሸማቀቅ ጮክ ብሎ በአደባባይ “ እኔ ሰውን በሰውነቱ እንጂ በሌላ አላውቀውም ። በአማራነቱ ፣ በትግሬነቱ ፣ በኦሮሞነቱ ፣ በጉራጌነቱ ፣ በሲዳማነቱ ፣ በሱማሌነቱ ፣ በጋምቤላነቱ ፣ በጉምዝነቱ ፣ በሐረሬነቱ ፣ በአፋርነቱ ። ወዘተ ።  ሳይሆን ፣ እንደ እኔ ሰው በመሆኑ ብቻ ነው የማውቀው ። ሰውን ሰው ብሎ ከመጥራት በመግባብያ ቋንቋው ስያሜ መጥራት ሰውን እንደ ግዑዝ ነገር መከፋፈል ነውና ግብዝነትን ያራባል ። አንዱን የሰው ሰብስብ በቋንቋው አንግሶ አንዱን ባርያ እንዲሆን ያሥገድዳል ። በዚህም ሰበብ የማያባራ ግጭት ውስጥ ሰዎች ሰውነታቸውን ክደው እንዲዘፈቁ ያደርጋል ። ትብብርና መደጋገፍ በሚሻው በ21ኛው ክ/ዘ ዘመን መራራቅን እና ጥላቻን ያነብራል ። እናም ይኽ የቋንቋ ሥርዓተ መንግሥት እሥከቀጠለ ጊዜ ደረስ የውጪ ጠላቶቻችን የመጫወቻ ካርድ ሆኖ በማገልገል በሚረጩት ገንዘብ ሰበብ መገዳደላችን የማያባራ ይሆናል ።“ ብሎ ቢናገር ፤ ይኽ እውነቱ  ለሥንቱ ሰው ይገባዋል ?

ከቶስ ተፈጥሮ በሂደት እኛን በክብር ከማሰናበቱ ቀድመን ትርጉም በሌለው ጥላቻ ፣ የተሻለ ለመብላት ብለን ፤ ለተሻለ የግል ኑሮ ብለን ነገ መሞታችን ላይቀር ለምን ዛሬ በስግብግብ አእምሮና በውሸት ቅስቀሳ ተገፋፍተን ጥቂቶች  ብዙሃን ንፁሐንን እንደእኛው ሰው መሆናቸውን እያወቅን በቋንቋ ልዩነት ብቻ ፣ ለምን እንገድላቸዋለን  ?

እኛ እንደ ህዝብ ተራ ሟች በመሆናችን ፤ ከዕውቀት በመራቃችን እና ኃይማኖተኞች ነን እንላለን እንጂ በተግባር ፀረ _ እግዚአብሔር ወይም ፀረ_ ፈጣሪ በመሆናችን ወደጥፋት ሥናመራ ፣ የሚመሩን የአገር አሥተዳዳሪዎች የባሰ በመገዳደላችን  እንድንቀጥል ለምን አሥፈላጊውን ሤጣናዊ ድጋፍ ሲያደርጉ ይስተዋላሉ   ? የሞትን ፅዋ መሪዎች ሣይቀሩ እንደሚጨልጦት ፍፁም ዘንግተው አይደለምን ? በመንግሥት ውሥጥስ  ተራ ሟች ሰዎች አልተሰባሰቡምን ? ከጥቂት ሚኒሥትሮች ውጪስ ሌላው የመንግሥት አካል በታሪክ የሚወሳበት ሰፊ ሥፍራ ይኖረዋልን ? ከቶስ ከመሪው በሥተቀር ማነው በተደጋጋሚ ፣ ሥሙ በደግና በክፉ ሥራው የሚነሳው ? የሚወሰው ?

ራቁት መወለድ ፤ ማደግ ፣ መጎልበት ፣ መጎልመስ ማርጀት ፣ መጃጀት መሞት የተፈጥሮ ሂደት ነው ። ከነዚህ ደረጃዎች ውሥጥ  በአንዱ እያሉም ፣   በህመም መሰቃየት እና መሞት የሁላችንም ዕጣ ፈንታ እንደሆነ መገንዘብም ታላቅ እውቀት ነው  ። የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ከመሞታቸው በፊት ጥይት ባይገድለን ባዮሎጂ ይገለናል ። ያሉት ይኽንን እውነት ይገልፀዋል ። (ጠ/ሚ አብይ አህመድ ታመው ቢሞቱ አዲስና እንግዳ ነገር ከቶም አይሆንም ። ሰው “ ተወለደ  ! “ ሲባል “ ሞተ ! ማለት ነው ። “ የሚባለውም ሞት ሁሌም ከህየሸወት ጌር አብሮ በሠኖሩ ነው ። ምናልባት  የሚቆጨው አንድ መሪ እንደሚሞት አሥቀድሞ በመገንዘብ  መሪ ያለማዘጋጀት ነው ። ለአፍሪካ ፖለቲካ ግን ይኽ አሥፈሪ ና አሣፋሪ መንገድ ከቶም አይደለም ። )

የሰለጠኑት  አገራት መሪዎች ይኽንን እውነት ከመቶ አመት በፊት ተገንዝበውታል ። እናም እንደ ሰው ሞት የማይቀርላቸው በመሆኑ ፣ የመንግሥት ቅብብሎሻቸውን ወገኛ አድርገውታል ። በአፍሪካ ግን ወገኝነት በጣት በሚቆጠሩ የአፍሪካ አገራት  ብቻ ነው ያለው ።

በአውሮፓና አሜሪካ መንግሥታቱን ፣  ተቀናቃኞቻቸው እና ምሁራን በአደባባይ ቢተቿቸው እና ቢያብጠለጥሏቸው “ ለምን ሥሜ በመጥፎ ተነሳ ? “በማለት ዘረፍ አይሉም ።  በመንግሥት ባለሥልጣናት ደርጊት ከበሸቀው  ህዝብ ጋር በመወገን ወቅታዊውን  ፖለቲካዊ ጉዳይና ፣ የህዝቡን ወቅታዊ የፍላጎት ትርታውን  አድምጠው  እያዋዙ ባለሥልጣናቶቻቸውን ተው ፣ እረፉ ይኽ ለዚህ ህዝብና አገር አይመጥንም ። ለእናንተም ቅሌት ነው ፤ በማለት የሚመክሩትን ኮመዲያንን ለምን ቀለድክብኝ በማለት አፍንጫቸውን በቦክስ አይሰብሩም  ። በግራና ቀኙም  ምንም ያህል መራራ እና የሚያንገፈግፍ ተረብ እና የትችት ናዳ ፤ ሸንቋጭ  ሂሥ ና  መዓት  የቃላት ውርጂብኝ ቢያጋጥማቸው ፤ ባለሥልጣናቱ ከሥህተት መንገዳቸው ከመማር ባሻገር ፤ ሂሱን እንደ ስድብ በመቁጠር ፣ መንግሥት ሆኜ ሣለ ፣ ሊሰግድልኝ ሲገባ ትችትና ወቀሳ   በእኔ ላይ በማዝነብ ፣ እውነትን ለህዝብ አሳውቋልና  እንደ ዮኃንስ መጥመቁ አንገቱ ተቋርጦ በሳሕን ይቅረብልኝ አይሉም   ። “ አፍኑት ! “   ብለው ሥውር  ትእዛዝም አይሰጡም  ።

እዚህ አገር አስብቶ ማረድ ፤ ልኩን አሳየው በማለት የራስ ቆዳን በማዋደድ ( ራቁታቸውን እንደተወለዱ ና ራቁታቸውን እንደሚቀበሩ በመካድ ) ዜጎች ተፈጥሮ በሰጣቸው አንደበት ለምን ተናገሩበት ብለው “ ለእግረ ሙቅ “ የሚዳርጉ ህግ አሥፈፃሚዎች ፣  እንዴት እና በማን እንደተቋቋሙ ግልፅ ባይሆንም ፣  ጤነኛና አሥተዋይ አእምሮ ላለው ማንኛውም ዜጋ ጉዳዩ እጅግ  አሣሣቢና አናርኪሲዝምን የሚያሰፍን ነው ። በዙ ጥያቂም ህዝብ እንዳያነሳ ያሥገድዳል  ።

“  በዚች ቅድስት አገር  በመንግሥት አርቆ አሳቢነት የሚተማመኑ ፣   ንፁሐን በማሰባቸው ብቻ ዘብጥያ ለምን ይወርዳሉ  ? እንዴት እውነትን ያለፍርሃት በመናገራቸው ፣ እውነቱ ለሌሎች ጠረዘኛ ፖለቲከኞች የሚጎመዝዝ በመሆኑ ብቻ የተፈጥሮ አንደበታቸው  ይለጎማል  ?   ደግሞስ የቋንቋና የጎሣ ፖለቲካው ያመጣው መሞሻለቅ አይደለም ወይ ? …  ። ሥንትና ሥንት ተሣዳቢዎች ደረታቸውን ገልብጠው በኩራት በሚራመዱባት አገር ውሥጥ እነዚህ በጣት የሚቆጠሩ መንግሥትን ለበጎ ሥራ የሚያነሳሳ ፣ ህፀፆቹን ነቅሶ በማውጣት እንዲታረም አሥቀድመው ምክረ ሃሳብ የሚለግሱ ፣ ለበጎ ሥራ ኮርኳሪ አንደበትና ብዕር ያላቸው ዜጎች ለምን ይታሰራሉ ???….. “ በማለት ዘወትር መንግሥትን የሚሞግት ጥያቄ ህዝብ ሲጠይቅ የሚሰማውም ከዚህ እውነት አፃር ነው ። በየደጁና በየቤቱ ። በየትም ሥፍራ ውሸት ሰልችቶናል ። እያለ ነው ህዝብ ።

እንደምታውቁት  ከደርግ የሶሻሊዝም “  የአብዮተኛ “ እና “ የፀረ አብዮተኛ “ ፍረጃ ጀምሮ አውዳሚው ውሸት ወይም ቅጥፈት  እየተለመደ መጥቷል  ። ያኔ በደርግ የሶሻሊዝም ሥርዓት ፣ ንፁሐን ያለ  ፍትህ ፣ ፍርድ ቤት ሣይቀርቡ ፣ በግለሰቦች የግል ውሳኔ ፣ በነፃ እርምጃ ይገደሉ ነበር ። ያም  እኩይ ድርጊት  “በየፍየል  ወጠጤ … “ ዜማ ታጅቦ   በሬዲዮ ይነገር ነበር ። ይኽ  ትክክል ያልሆነው ፣ ውሸት የሆነው ማብራሪያ በሥሜት ተጆብኖ ፤ በበቀለ ወፍሮ ፤  ለህዝብ   ሲቀርብ ብዙሃኑ “ አሹ  “ ይል ነበር ። ከወታደራዊ  መንግሥት ሥርዓት  በኋላ   ደሞ  ፤ መልኩን ቀይሮ ብቅ ያለው ፤ በሎጂክ እንጂ በመንግሥት ሥርዓትነት በዓለም ቅቡልነት የሌለው የተጨቋኝ እና የጨቋኝ ቋንቋ ትርክትና የተረኝነት መንገድ ነው ። ኢህአዴግ ወያኔ የዚህ ሥርዓት ዋና ተዋናይና የመድረኩ ባለቤት ሆኖ የመጣበት ። ( …  ። ) የሰው መግባቢያ የሆነን ቋንቋ ሲወለድ ጀምሮ በደም ውሥጥ ያለ  የአንድ ጎሣ ብቻ መግባቢያ አድርጎት አረፈው እና ሰውን በቋንቋ ከፋፍሎ ክልል ብሎ አጥር ሰርቶለት አረፈው ።

በመሠረቱ ቋንቋ የሰዎች በሙሉ ቋንቋ ነው ።  የአንድ ዘውግን እና ጎሣ ቋንቋ ሊሆን አይችልም ። ከተማርከው ፣ በቋንቋው ተናገሪ ቤተሰብ ውስጥ ካደክ ፤ ወይም በልዩ ለዩ አጋጣሚ ከቋንቋው ተናጋሪ ቤተሰብ ጋር ከኖርክ ፤ ቋንቋውን በቀላሉ ታውቃለህ ። አንድ ቋንቋ የእኔ ብቻ ነው ማለት    በመሠረቱ ሥህተት ነው ። ሥለቋንቋ መወለድ ፣ ማደግ እና ዓለማቀፋዊ መሆን ብቻ ሣይሆን ቋንቋ እንደሚወለድ ሁሉ እንደሚሞት ያለማወቅም ነው ። ቋንቋውን በመማር ብቻ የየትኛውም አገር ዜጋ የኢትዮጵያን ቋንቋዎች የራሱ ማድረግ ይችላል ። ይሁን እንጂ የቀድሞው  የወያኔ ሥርዓት የእነሱ እና የእኛ ቋንቋ በማለት ዜጎችን በቋንቋ መጥራት በመጀመሩ እና ግለሰቦች በቋንቋ ብቻ   ለህብረተሰባቸው የሚፈይዱት አንዳችም ሳይኖር ፤ እውቀቱ ፣ ችሎታው ፣ ክህሎቱ ሳይኖራቸው ፣ በቋንቋ ብቻ ተደራጅተው ፣ ተቧድነው ፣ ኔት ወርክ ፈጥረው ፤ በቀላሉ   ሀብት ለማፍራት የሚያሥችል  ሥልጣን አሥገኘላቸው ። በደርግ የሶሻሊዝም ሥርዓተ መንግሥት “ ሁሉም ጎሣዎች እኩልናቸው ሌብነትም ጥዩፍ ነው “ ተብሎ ተጨቋኝ መደብ አሸናፊ የሆነበትና ኃይልና ሥልጣን የሰፊው ህዝብ ነው ። “ ተብሎ  በገሃድ የተዜመበት ሥርዓት በቋንቋ የበላይነትና ገዢነት ሥም የጥቂቶች ፈላጭ ቆራጭነት የሚፀባረቅበት መንግሥታዊ ሥርዓትን ይዞ ብቅ አለ ። የወቅቱ  ፕሬዚዳንት  መለሥ ዜናዊ በቋንቋ ሥም የትግሪኛ ተናጋሪዎችን ፈላጭ ቆራጭነት አበሰሩ ። ሌብነት በወጉ ለህወሓት ፓርቲ ጥቅምና ጥቅም ብቻ እንዲውል ተደረገ ። በመለሥ ዜናዊ ዙሪያ ያሉ  ጥቂት የህወሓት ዓባላትም ቢሊዮነር ሆኑ ። በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ና ሀብት በአሜሪካና በአውሮፓ አከማቹ ።

ይኽ ሌብነት መለሥ ከሞቱ በኋላ በሁሉም የኢህአዴግ ዓባል ድርጅቶች ውሥጥ ተስፋፋ ። እና ህብረተሰቡ የሚጠየፈው ሌብነት እጅግ እያበጠ መጣ ። …

ቀስ ፣ በቀስ  መልካሙ ባህላችንን ፣እሴቶቻችንን እና ኃይማኖተኝነታችን  በእጅጉ ሸረሸረው ። ጥቂት የማይባለው አጋጣሚው የተመቻቸለት ቋንቋኛ ያለምንም ድካም  በአቋራጭ ገንዘብ እያገኘ ቱጃር ለመባልም በቃ ።  እንሆ  ለዛሬው ፈጣሪን ያለመፍራት ደረጃ ጥቂት የማንባለውን  ቋንቀኝነት አደረሰው ።  ሰውን በቋንቋው መከፋፈል ። ሰውን ከፋፍሎ  በየቋንቋው መፈረጅም በእጅጉ ተሥፋፋ ። ከአንድ ቋንቋ ቤተሰብ የተወለደ ግለሰብን እንኳ በነውረኛ ድርጊቱ መኮነን  መላውን የቋንቋውን ቤተሰብ መድፈር እንደሆነ ተቆጥሮ በየመንደሩ የሁከት ፣ የብጥብጥና የመገዳደል ሰበብ ሆኖ ነበር  ።

የእገሌን ልጅ ተናገርክ ፤ ሰደብክ ፤ ነገሩን ፣ ድርጊቱን ኮነንክ ፤ …አንተ እንትን ሥለሆንክ ። የሚሉ የነገር ሰይፎች እጅግ   በርክተው የስንቱን ንፁሐን አንገት እንደቀነጠሱ ሾርት ሚሞሪ ከሌለን በሥተበር አንረሳም ። የባሰ አውሬነት ደግሞ በቅርቡ  በምዕራብ ና በምሥራቅ ወለጋ ሲከሰት ሰብዓዊነት ጠፍቶ ለዜጎች ሞት የሚቆጭና የሚንገበገብ ባለሥልጣን ጠፋ   ።

እኛ ኢትዮጵያዊያን ፣ ዛሬ እና አሁን ያልባነንን መቼ እንደምንባንን ከቶም አይገባኝም ። መንግሥት ህዝብን በሚበጀው ወይም ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርገው ፣ ዜግነቱን በሚያሶድደው መንገድ ህዝብን መመራት አለበት እንጂ በጠላቶቻችን በሚዘወሩ ኢ _ ሰው እና ፀረ _ፍቅር በሆኑ ባለነፍጥ ፖለቲከኞች ማስፈራርቾ እሥከመቼ ፓለቲካውን  እያስታመመ አገርን በተረጋጋ ሁኔታ ማሥተዳደሩን በወከባ ይቀጥላል ?

የበለፀጉት አገራት ታሪክ የሚነግረን ጠንካራ መንግሥት ለመገንባት በወታደራዊ ህግ ብቻ የሚመራ መከላከያ ሠራዊት እና የአገርን ጠላቶች አሥቀድሞ በማነፍነፍ ፤ከጥፋት የሚታደግ የሲቪሊና ወታደራዊ ደህንነት አሥቀድሞ መገንባት ያሥፈልጋል ። ( ዛሬም የተጠናከረ የደህንነትና የመከላከያ ተቋም እንዲኖራቸው ለነዚህ ተቋማት የሚያወጡት ወጪ የሠራዊት እንክብካቢያቸው ከፍተኘ ነው ። )  እኛም በአቅማችን ከፍተኛውን በጀት   ለመከላከያ ና ለደህንነት ኃይል በመሥጠት መንግሥትን አጠናክረን ፣ በዜጎች ቅቡልነት ያለው ተከታታይ የሆነ ጠንካራ መንግሥታዊ ተቋማ ሊኖረን ይገባል ። ብዬ አምናለሁ ። በዚህ ረገድ የመንግሥት ጥረት የሚያስመሰግነው ቢሆንም ፣ ከፓለቲካው አንፃር ግን ፈቀቅ ያለ ተጨባጭ ለውጥ በበኩሌ አላየሁም ። መንግስት ዛሬ በከፍተኛ “ የማንን ልመን ? “ ጥርጣሬ ውሥጥ የወደቀም ይመሥላል ።

ዛሬ እና አሁን  መንግሥት እንደግለሰብ ማንን ማመን ማንንስ ያለማመን ጥርጣሬ ውሥጥ ሊወድቅ የቻለው ፣ካለፈው የደርግ አዙሪት ያልወጣ የፓርቲ አባላትን ይዞ ሥለሚጓዝ ነው ። እርግጥ ነው በሥም ፓርቲው ተለውጧል ። በግብር ግን የተለወጠ አንዳች ነገር የለም ። መንግሥት በአንክሮ ከተመለከተ ዘሬም የሚጓዝበት አደረጃጀት ደርግ ከመሠረተው ቀበሌ ና ገበሬ ማህበር የሚነሳ ነው ። ዛሬም የማዘጋጃ  ተቋማዊ ሥርዓት ሳይሆን የካድሬ ቀበሌያዊ አሥተዳደር ነው ።  ዛሬም ፓርቲና መንግሥት አልተለየም ። በመሆኑም በፓርቲ ሥም  ከቀበሌ ጀምሮ በሰው ነፍሥ የሚወሥኑ እግዜሮች ቢኖሩ አይገርምም ። ከደርግ ጀምሮ ነበሩና !!!!!!!!

በበኩሌ መንግሥት ወይም ገዢው ፓርቲ  ለ21 ኛው ክ/ዘ የሚመጥን የመንግሥት ሥርዓት ለማዋለድ አንድ ብርቱ ዘዴ ካልቀየሰ በታሪክ ተወቃሽ ሊሆን የሚችልበት መሥቀለኛ መንገድ ላይ እንዳለ ይታየኛል ።

በተለይም በትግራይ  ያለው ፣ ሰው መሆንን የካደ የሊሂቅ ሥብሥብ አጥፍቶ መጥፋት አላማው ነውና አሁንም የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ንብረት በሆነው መሬት ፤ በእኔነው ባይነት በብርቱ ይከራከራል ። ይኽንን ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት እኩይ መንገድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያከትም ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ቅቡል የሆነ ልዩ ዘዴ እና ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣ አዲስ የዜጎች እኩልነት መንገድን  መንግሥት ሣይዘገይ መቀየሥ ይኖርበታል ብዬ አምናለሁ ። ያ ዘዴም የትግራይ ህዝብ ሰውነትን በካደው ፣ የትግራይ ሊሂቅ ላይ የሚነሳበት እና እሥከወዲያኛው የሚጠራርገው መሆን ይኖርበታል ። ልብ በሉ የትግራይ ህዝብ እንደ ኢትዮጵያዊነቱ የኢትዮጵያ ግዛት ሁሉ አገሩ መሆኑንን በተጨባጭ ከተረጋገጠለት እጅግ የሚያስደንቅ ኢትዮጵያዊነቱን የወያኔንን ግብአተ መሬት በመፈፀም ያረጋግጣል ።

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

vision
Previous Story

በአማራ ሕዝብ ላይ የሚካሄደውን የዘር ፍጅት አስመልክቶ የሚደረገዉን የረሃብ አድማ በመደገፍ ከቪዥን ኢትዮጵያ የተሰጠ መግለጫ

44rere
Next Story

ከሞፈር ያዥ ወደ ጠመንጃ ያዥ! የበጋ የመስኖ ስንዴ ፋና ወጊዎች የወርቅ ሜዳልያ ሊሸለሙ ይገባል!›› – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop