ከሞፈር ያዥ ወደ ጠመንጃ ያዥ! የበጋ የመስኖ ስንዴ ፋና ወጊዎች የወርቅ ሜዳልያ ሊሸለሙ ይገባል!›› – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

የቄሣርን ለቄሣር፣ የእግዜብሔርን ለእግዚያብሔር ስጡ!  “Give to Caesar what belongs to Caesar and to God what belongs to God.”

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በግብርና ዘርፍ ላይ ጥገኛ ነው፡፡ ግብርና ዘርፍ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት (GDP) 40 በመቶ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ግብርና 80 በመቶ ወደ ውጭ የሚላክ ምርቶች ገቢ በማስገኘት የውጭ ምንዛሪ ያስገኛል፡፡ ግብርና ዘርፍ 75 በመቶ የሰው ኃይል ይሸፍናል፡፡ “Ethiopia’s economy is dependent on agriculture, which accounts for 40 percent of the GDP, 80 percent of exports, and an estimated 75 percent of the country’s workforce.”  በኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የተሠማራው  አርሶ አደርና አርብቶ አደር ተገድዶ ከግብርና ሥራ ወደ ውትድርና ሥራ  በመሠማራቱ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በጦርነት ቀለበት ውስጥ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ የማያባራ አውዳሚ አረመኔያዊ ጦርነት  በወያኔ፣ በኦነግ፣ በኦነግ ሸኔ፣ በኦህዴድ ብልፅግና ወዘተ በትግራይ፣ በአማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ተስፋፍቶል፡፡ በክልሎቹ ውስጥ ከግብርና ስራ ይልቅ ወታደራዊ ሥራ በመዘዋወሩ አምራቹ ኃይል ወደ ኢአምራችነት ኃይል (from Productive force to Nonproductive force) ¨ ተዘዋውሮል፡፡ ከሞፈር ያዥ ወደ ጠመንጃ ያዥነት ተቀይሯል፡፡ ይህ አረመኔዊ ኃይል ከገጠር ወደ ከተማ ጦርነት በማድረግ መሠረተ ልማቶችን ትምህርት ቤት፣ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ ሆስፒታሎችን፣ ቴሌኮምኒኬሽን፣ መብራት ፣ ውኃ፣ ባንኮችን  ወዘተ ተቆሞችን በማውደምና የአርብቶ አደሩን ከብቶችና የእህል መጋዘኖች በመዝረፍ ልማታዊ ስራዎችን ሁሉ አጥፍቶል፡፡ ይህ አረመኔ ሽብርተኛ ኃይል እቅዱ በአማራ ዘር ላይ ያነጣጠረ የዘር ፍጅት በማድረግ፣ ከተሞችን በመዝረፍ ሃገሪቱን በማያባራ ጦርነት ከቶ ማፍረስ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ገበሬዎች በአንድ እጁ ሞፈር ይዞ፣ በሌላ እጁ ጠመንጃ አንግቦ በህይወት የመኖር መብቱን ለማስከበር በመታገል ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ እልህ አስጨራሽ የህልውና ጦርነት ውስጥ  የግብርና እርሻ በመቀጠል የበጋ የመስኖ እርሻን በማስፋፋት የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት የሠብል ምርምር ሳይንቲሰቶችና ሠራተኞች የበጋ መስኖ የስንዴ እርሻን በማስፋፋት  5.7 (አምስት ነጥብ ሰባት) ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የስንዴ ምርት፣  10.2 (አስር ነጥብ ሁለት) ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የበቆሎ ምርት እንዲመረት ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት የሠብል ምርምር ሳይንቲሰቶችና ሠራተኞች የበጋ የመስኖ ስንዴ ፋና ወጊዎች የወርቅ ሜዳልያ ሊሸለሙ ይገባል እንላለን! በየስንዴ ማሳ ውስጥ የሚንጎማለሉ የኦህዴድ ብልጽግና ካድሬዎች የስንዴ ኬኛ ፖለቲከኞች ሊያፍሩ ይገባል እንላለን፡፡  ታሪኩ እንደዚህ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሱዳንም ቀደመችን?! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

 

ዘጋቢ ፊልም – ራስን መቻል Etv | Ethiopia | News – YouTube

ይህን ዘጋቢ ፊልም በማየት የበጋ የመስኖ ስንዴ ምርትን በፋና ወጊነት ለውጥና ውጤት ያስገኙ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት ተመራማሪ ሠራተኞችን ድንቅ ስራ በመመልከት ለሙያተኞቹ እውቅና እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡

ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ፡የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲቲዩት ዋና ስራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡ ፒኤችዲ በጥናተ ዕፅ ሥነ ባህሪ እንዲሁም ኤምቢኤ የተክል እዐዋት ዘር በማርባት ትምህርት በመቅስም ለሁለት አስርት ልምድ በማካበት በፖሊሲ፣ በምርምር፣ በልማት ሥራና በማስተማር ስራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡

Mandefro Nigussie Ethiopia · Chief Executive Officer · Agrcultural Transformation Agency of Ethiopia. He has PhD in Genetics and Plant Breeding (and MBA) with over two decades of work experience in policy, research, development and teaching as

ዶክተር ዳንኤል ሙለታ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት የመስኖ ስንዴ ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶክተር ነጋሽ ገለታ፣ ዶክተር ደምስ ጫንያለው አግሮኢኮኖሚስት፣ ዶክተር ታዬ ታደሠ፡ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት የስብል ምርምር ዴሬክተር፣ ዶክተር ኃይለማርያም ከፍያለው ሌሎችም የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት ተመራማሪ ሠራተኞችን ገድል በዘጋቢ ፊልም – ራስን መቻል Etv | Ethiopia | News – YouTube  ይመልከቱ፡፡

 

የአፍሪካ አገራቶች 25.7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የስንዴ ምርት ሲያመርቱ፣ አህጉሯ 54.8 ሜትሪክ ቶን የስንዴ ምርት ከውጭ አገራቶች ኢንፖርት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ As a result, African nations rely on imports to meet the demand and need for wheat. For instance, during the 2020/2021 trade year, African imports of wheat reached 54.8 million metric tons, whereas the continental production of wheat amounted to 25.7 million metric tons.Apr 14, 2022

የኢትዮጵያ የስንዴ ምርትና የስንዴ ፍጆታ፤ ከባር ግራፉ ላይ እንደሚስተዋለው ሰማያዊው ባር የስንዴ ምርት ሲያሳይ፣ ቀዩ ባር ደግሞ የሃገር ውስጥ የስንዴ ፍጆታን ያሳያል፡፡ የስንዴ ምርትና ፍጆታ ተጣጥሞ ስለማያውቅ ሀገራችን ልዩነቱን ከባህር ማዶ ሀገራት ከዩክሬን፣ ከራሽያ፣ አሜሪካ፣ አርጀንቲና፣ ቡልጋሪያ፣ ወዘተ አገራቶች ስንዴ ትገዛለች፡፡ በመረጃው መሰረት ሃገራችን በስንዴ ምርት ገና እራሶን አልቻለችም፡፡ ስለዚህም ወደ ውጭ ሃገራት የስንዴ ምርት መላክ ደረጃ ላይ አልደረስንም፡፡

  • በ2017/18 እኢአ የስንዴ ምርት 4.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲገመት፣ የስንዴ ፍጆታ 6.7 ሚሊዮን ቶን የነበረ ሲሆን ልዩነቱ ከውጭ ሀገራት በግዢ ኢንፖርት ይደረጋል
  • በ2018/19 እኢአ የስንዴ ምርት 4.8 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲገመት፣ የስንዴ ፍጆታ 6.0 ሚሊዮን ቶን +የነበረ ሲሆን ልዩነቱ ከውጭ ሀገራት በግዢ ኢንፖርት ይደረጋል
  • በ2019/20 እኢአ የስንዴ ምርት 5.1 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲገመት፣ የስንዴ ፍጆታ 6.8 ሚሊዮን ቶን የነበረ ሲሆን ልዩነቱ ከውጭ ሀገራት በግዢ ኢንፖርት ይደረጋል
  • በ2020/21 እኢአ የስንዴ ምርት 5.0 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲገመት፣ የስንዴ ፍጆታ 6.9 ሚሊዮን ቶን የነበረ ሲሆን ልዩነቱ ከውጭ ሀገራት በግዢ ኢንፖርት ይደረጋል
  • በ2021/22 እኢአ የስንዴ ምርት 4.9 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲገመት፣ የስንዴ ፍጆታ 6.8 ሚሊዮን ቶን የነበረ ሲሆን ልዩነቱ ከውጭ ሀገራት በግዢ ኢንፖርት ይደረጋል
  • በ2022/23 እኤአበኢትዮጵያ የስንዴ ምርት7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን፣ የበቆሎ ምርት 10.2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ( Wheat production in Ethiopia for 2022/23 projected at a record level of 5.7 million MT while corn forecasted to 10.2 million MT. (Report Name: Grain and Feed Annual………………………….….(1) 
ተጨማሪ ያንብቡ:  የጾመ ነነዌ ሁለተኛ ቀን ጸሎተ ምሕላ በባሕርዳር መስቀል አደባባይ

 

በኢትዮጵያ የስንዴ ማሳ በሄክታር፣ የስንዴ ምርት አቅርቦት፣ ምርታማነት በሄክታርና የስንዴ ፍላጎት …………………………….(2) 

  • በ2016/17 የስንዴ ማሳ 1.600 ሚሊዮን ሄክታር መሬት የታረሰ ሲሆን፣ 3.9 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የስንዴ ምርት ሲገኝ፣ ምርታማነት  2.44 ቶን በሄክታር ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የስንዴ ፍላጎትና የስንዴ ፍጆታ 5.697 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነበረ፡፡
  • በ2017/18 የስንዴ ማሳ 1.600 ሚሊዮን ሄክታር መሬት የታረሰ ሲሆን፣4.2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የስንዴ ምርት ሲገኝ፣ ምርታማነት  2.63 ቶን በሄክታር ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የስንዴ ፍላጎትና የስንዴ ፍጆታ 5.950 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነበር፡፡
  • በ2018/19 የስንዴ ማሳ 1.750 ሚሊዮን ሄክታር መሬት የታረሰ ሲሆን፣ 4.7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የስንዴ ምርት ሲገኝ፣ ምርታማነት 2.69 ቶን በሄክታር ነበር፡፡  የኢትዮጵያ ህዝብ የስንዴ ፍላጎትና የስንዴ ፍጆታ 6.557 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነበር፡፡
  • በ2019/20 የስንዴ ማሳ 1.800 ሚሊዮን ሄክታር መሬት የታረሰ ሲሆን፣ 4.925 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የስንዴ ምርት ሲገኝ፣ ምርታማነት 2.73 ቶን በሄክታር ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የስንዴ ፍላጎትና የስንዴ ፍጆታ 6.670 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነበር፡፡
  • በ2020/21 የስንዴ ማሳ 1.850 ሚሊዮን ሄክታር መሬት የታረሰ ሲሆን፣ 5.025 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የስንዴ ምርት ሲገኝ፣ ምርታማነት  2.76 ቶን በሄክታር ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የስንዴ ፍላጎትና የስንዴ ፍጆታ  6.705 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነበር፡፡

 

ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ኢምፖርት የምታደርገው የምግብ ነክ ምርቶችና ሸቀጦች ሁለት ቢሊዮን ዶለር በአመት እንደሆነ ዩኤስ ትሬድ ሪፕሬዘንታቲቨ መረጃውን አውጥቶል፡፡ Official Ethiopian trade statistics indicate that Ethiopia imports nearly $2 billion worth of food products per annum. According to data from the U.S. Trade Representative (USTR). ከዚህ ውስጥ የስንዴ ግዢ ከ700 ሚሊዮን እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የምግብ ዘይት ግዢ ወጭ  አንድ ቢሊዮን ዶላር በአመት ይገመታል፡፡ ስንዴንና የምግብ ዘይትን በሃገር ውስጥ ምርት በመተካት የምግብ ነክ ምርቶችን ወጭ መቀነስ ይቻላል፡፡ በዚህም የውጭ ምንዛሪ ኃብትን መቆጠብ ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ በምግብ ራሶን እንድትችል ያግዛል፡፡ ኢትዮጵያ በምግብ ራሶን ችላ ወደ ባህር ማዶ የስንዴ ምርትን በመላክ ተጠቃሚ መሆን ትችላለች፡፡ Although Ethiopia’s wheat output jumped about 70% this decade, the country still depends on 1.2 million imported tons a year, which represents USD 210 million that the country spent on wheat imports in 2019. Since taking office last year, Prime Minister Abiy Ahmed’s government has pledged to invest in irrigation and machinery and encourage more farmers to plant wheat to avoid reliance on imports by 2022. The government has been working vigorously to secure the country 1 billion USD through wheat import substitution efforts.

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለተፈናቃዮች ሀገራቸው የት ነው?

ተጨማሪ  መረጃዎች  ለማግኘት

World Grain. ¨Ethiopia wheat, corn production on the rise¨

USDA Grain and Feed Annual Report

Bloomberg. ¨Ethiopia Will Need Imported Wheat for a While Yet Despite Self-Sufficiency Plan¨

World Grain. ¨Ethiopia’s wheat production to increase¨

Agri Census. ¨Ethiopia confirms three outstanding wheat tenders¨

Wheat production, consumption and import, Ethiopia (1995/96 – 2012/13)   | Download Scientific Diagram (researchgate.net)

 

ምንጭ

(1) Ethiopia: Grain and Feed Annual | USDA Foreign Agricultural Service

(2) Ethiopia’s increasing wheat demand hinders the country from being self-reliant – Tridge Source: FAS/Addis

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share