July 25, 2022
6 mins read

በአማራ ሕዝብ ላይ የሚካሄደውን የዘር ፍጅት አስመልክቶ የሚደረገዉን የረሃብ አድማ በመደገፍ ከቪዥን ኢትዮጵያ የተሰጠ መግለጫ

vision

July 24, 2022

በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ መንግሥት እውቅና፣ በሺመልስ አብዲሳ አስተዳደር፣ በአማራ ሕዝብ ላይ በተደጋጋሚ የሚደርሰውን አረመኔአዊ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ዘመቻ ለማውገዝ እስካሁን ፈቃደኝነት ያላስየውን የእንግሊዝ መንግሥት ለመማለድ፣ ለአምስት ቀኖች እህልና ዉሃ ሳይቀምሱ፣ ለንደን ከተማ በረሃብ አድማ የሚገኙትን ሁለት ኢትዮጵያውያን ጀግና እህቶቻችንን ቪዥን ኢትዮጵያ (ራዕይ ለኢትዮጵያ) በታላቅ አድናቆት እያመሰገነ፣ ከጎናቸው የቆመ መሆኑን ሲገልጽ መጠን በሌለው ኩራትና ቆራጥነት ነው።

ወያኔ በሰሜን፣ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ በምዕራብ፣ እንዲሁም የኦሮሙማ መንግሥት በደቡብ፣ የተቀናጀ ዘመቻ ከፍተዉ ሲያጠቁት፣ የወግኖቻችንን ሰቆቃ ለመስማት መላው ዓለም ፊቱን ባዞረበት በአሁኑ ሰዓት፣ እነዚህ ጀግና ኢትዮጵያዉያን የሚያካሂዱት የረሃብ አድማ፣ በዉጭ ለምንኖረው የፍትህ ደጋፊዎች ሁሉ ትልቅ መልእክት ያዘለና፣ ወደፊትም መደረግ ለሚገባው የትግል መርሆ የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ ሊታይ የሚገባው ተግባር ነው።

የዐብይ አሕመድ መንግሥት ስልጣን ከጨበጠበት ጊዜ ጀምሮ፣ በኢትዮጵያዊነት ሰበካ የአማራውን ወገን አስክሮ፥ በአማራ ተወላጆችና ሌሎች ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ኢሰብአዊና አሰቃቂ የዘር-ፍጅት ድርጊቶች እያካሄደ፣ በአንጻሩም የኦሮሙማን የበላይነት ሲገነባ ቆይቷል:: ከዚያም አልፎ፣ በአሁኑ ወቅት፣ የአዲስ አበባን አስተዳደር በኦሮሙማ ቁጥጥር ስር አድርጎ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የተራኛነት አላማን በማክሸፍና የአማራውን በገሃድ መታረድ በመታገል እንቅፋት ይሆናሉ ብሎ የገመታቸውን ግለ-ሰቦችና፣ እንደፋኖ ያሉትን ቡድኖች፣ በማን አለብኝነትና በትኢብተኝነት በማጥፋት ላይ ይገኛል።

በጥንት ጊዜ ግራኝ መሃመድ በከፈተው በር ገብቶ፣ የነበረውን ስልጣኔ አጥፍቶ፣ የተስፋፋዉን የኦሮሙማን ስርአት፣ አባቶቻችን በነበራቸው ጥበብና አርቆ አስተዋይነት አግባብተው፣ ተዋልደዉና ተጎራብተው ቢኖሩም፣ ነብር ዥጉርጉርነቱን አይጥልም እንዲሉ፣ ዛሬ ደግሞ የወያኔን ፈር ተከትለው የተነሱት አክራሪ የኦሮሙማ ባለተራዎች፣ ታሪክ ሊረሳው የማይችለውን የዘር ጭፍጨፋ ሲያካሂዱ ይታያሉ።

በአማራው ሕዝብ ላይ የተደቀነውና እየተገበረ ያለውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ፣ ለፍትህ የቆመ፣ በዉጭ የሚገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሲቃወመው የቆየ ቢሆንም፣ የወንጀሉን አሰቃቂነትና አደገኛነት የሚመጥን እርምጃ፣ በተቀነባበረ መንገድ ተወስዷል ለማለት ያዳግታል። ስለዚህም ነው ቪዥን ኢትዮጵያ፥ የጀግና እህቶቻችንን የረሃብ አድማ በማድነቅና በማወደስ ለመደገፍ የተነሳው።

Page | 1

በይበልጥም፣ ጀግና እህቶቻችን እያስታወሱን ያሉት፣ የዊኒስተን ቸርችልን መርሃዊ ቃል፡ “Victory will never be found by taking the path of least resistance” ነው። ስለዚህ፣ ቪዥን ኢትዮጵያ በድጋሜ፣ በአገር ዉስጥና በዉጭ ለሚገኙ፣ ለፍትህ ለቆሙ ኢትዮጵያውያን፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እርምጃዎች በጥሪ መልክ ያቀርባል፤

1.በረሃብ አድማ ለተሳተፉት ጀግኖች እህቶቻችን እስፈላጊዉን ደጋፍ መስጠት፤

2.በሌሎች ምዕራባዉያን ከተሞች የሚኖሩ ወገኖች፣ ተመሳሳይ ግፊት ለመንግሥቶቻችው ማድረግ፤

3.የዐብይ አሕመድ መንግሥት በአማራው ሕዝብ ላይ የሚያካሂደውን የዘር ጥፋት ዘመቻ እስኪያቆም እና በዘር ላይ የተመሠረተውን አገዛዝ እስኪሰርዝ፣ ክዲያስፖራ የሚአገኝዉን የዉጭ ምንዛሪ ማድረቅ፤
4.የዐብይ አሕመድንና የሺመልስ አብዲሳን አስተዳደሮች በዘር ማጥፋት ወንጀል ለማስፈረጅ የሚደርግን እንቅስቃሴ መደገፍ፣
5.ለአብይ አሕመድና ሺመልስ አብዲሳ የዘር ጥፋት ዘመቻ ተባባሪ የሆኑትን የአማራ ክልል መሪዎች በዘር ማጥፋት ተባባሪነት ወንጀል ለማስፈረጅ የሚደርግን እንቅስቃሴ መደገፍ።

ድል ለተበደለ ሕዝብ

“Rebellion to tyrants is obedience to God.” – Benjamin Franklin

ቪዝን ኢትዮጵያ (ራዕይ ለኢትዮጵያ)

 

Ethiopia: ‘Horrific’ massacre of 400 ethnic Amhara must be investigated immediately

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop