ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ፣ በበቀል ስሜት ደም እንዳይለገስ የከለከሉ የመንግሥት አካላትን አወገዘ!!

July 14, 2022
8efdb9ec93f4f79f9a5b77ba33206917የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም በየዓመቱ ሐምሌ 7 ቀን የሚውለውን የልደት በዓሌን በማስመልከት ላለፉት ረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በመገኘት ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት ለመታደግ ደም በመለገሰ ሰብአዊ ተግባር ለምትፈፅሙ የልብ አድናቂዎቼና ወዳጆቼ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን እያቀረብኩ፤ በዘንድሮው ደም የመለገስ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ባልተገባ ሁኔታ ለገጠማችሁ መጉላላት የተሰማኝን ኅዘን ስገልፅ ይህን ፍፁም ሰብአዊ ሕይወት የማዳን መርሐ ግብር በተገቢው ሁኔታ እንዳይከናወን ክልከላ ያደረጉ መንግሥታዊ አካላትን በጥብቅ በማውገዝ ነው።
በተጨማሪም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት መልካም ምኞታችሁን በተለያየ መንገድ ለገለፃችሁልኝ ክቡራን ወገኖቼ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።
ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሣሁን ( ቴዲ አፍሮ)
293705674 588219309335011 2957886411510939817 n

4 Comments

  1. ዘሃበሻ በሰጠው የዜና አርዕስት ዉስጥ ያለው “በበቀል ስሜት ተነሳስተው” የሚለው ቴዲ የጻፈው ዉስጥ የለም። ቴዲ ያለው “በተገቢው ሁኔታ እንዳይከናወን ክልከላ ያደረጉትን መንግስታዊ አካላት በጥብቅ በማውገዝ ነው” የሚል ነው። መንግስታዊ አካላቶቹ በመስሪያ ቤት ደረጃም ይሁን በህላፊነት ያሉ ግለሰቦችን አይጠቅስም። ከቀይ መስቀልም ሆነ ከሚመለከተው መንግስት ሃላፊ ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋግሮ እንደሆነም አልነገረንም። ስለዚህ በጉዳዩ ከማንም አልተነጋገረም ብሎ ማስብ ይቻላል። በዛሬው ፖለቲካ በመንግስት መስሪያ ቤት ያለ ሁሉ ለመንግስት ያስባል ማለት አይቻልም። የሚሻለው ቴዲ ጉዳዩን በአድናቂዎቹ ስም ቢያንስ ከቀይ መስቀል [ብሄራዊ ደም ባንክ] ጋር ተነጋግሮ ለወደፊት መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች በሁሉም ወገን ተፈተው ደም መለገስ ያለምንም ፖለቲካዊ እንደምታ እንዲቀጥል ማድረግ ቢችል ነው። ደም መለገስ መንግስትን ጨምሮ በማንም ወገን የፖለቲካ መጠቀሚያ መሆን የለበትም።

  2. በኪነ ጥበቡ ብቻ ሳይሆን በሌላውም በርካታ ሙያ የተሰማራው አብዛኛው ባለሙያ ክፉ የአድርባይነት ደዌ በተጠናወተበት ማህበረሰብ ውስጥ እንደዚህ ራስን ቁጥብ ከማድረግ አልፎ የሚሰማንን ስሜት በቀጥታም ባይሆን በቅኔ አይነት አገላለፅ ሙዚቃ መግለፅ ይበል ያሰኛል!

    ይህች የፌስ ቡክ ምላሽም ከዚዚሁ አኳያ ስትታይ ይበል ታሰኛለች።

    በሌላ በኩል ግን መቸም እንደ ቴወድሮስ ካሳሁን አይነት ሰዎች ላይ ትንሽዬ ትችትም ብትሆን ስተሰነዘር እንደ ነውር ወይም እንደ መርገም ወይም እንደ ምቀኛ ወይም አገርን ጨምሮ ዝቅ እንደ ማድረግ ወይም እንደ ጨለምተኛ ወይም ፀጉር እንደ መሰንጠቅ ፣ እና በአጠቃላይ “ምንስ ሲል ይሞከራል” የሚል ክፉ ልማድ ሆኖብን ነው እንጅ ፦

    1) በቅኔ ለበስ ሙዚቃ ሳይሆን በአገኙት መድረክ ፣ ሜዲያና ሌላ አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመው ያለማሳለሰ ቀጥተኛና ገልፅ በሆነ (አካፋን አካፋ በሚል ) ገዥዎችን በመሞገታቸው ለአፈና እና ለእሥር እንግልት የተዳረጉ ድንቅየ ወገኖች ባሉባት አገር ውስጥ “መንግሥት” ከማለት ይልቅ “የመንግሥት አካላት” ነገር አበላሹ የምትለዋ ደምሳሳና ልፍስፍስ አገላለፅ ብዙም የሚነገርላት ይመስለኝም።

    2) ማሰብ የሚከብድ ሰቆቃ ለአራት ዓመታት ሲካሄድ ዝምና ጭጭ ብሎ የሚለቀቅ አንድ ቅኔ ለበስ የሙዚቃ ሥራ ለሞራል ድጋፍ መጥቀሙ ባይካድም ወደ ተግባር ይለወጥ ዘንድ ተጨማሪ ድርሻን በመወጣት ሥራ እሰካልተደገፈ ድረስ ከቶም ወንዝ አሻግርም። እንደዚያ ቢሆነማ ኖሮ ስንት ሙዚቃ ለስንት ዘመን እየሰማን አሁን ካለንበት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ራሳችንን ባላገኘነው ነበር።

  3. አይ ቴዲ እንዳንተ አይነት ሰዎች ሁለ አቀፍ እይታ ቢሆን ኑሮ ዛሬ ምድሪቱ ላይ ወርቅ በለቀምን ነበር። ግን አልሆነም። ኤልሻዳይ የሚባል ግብረ ሰናይ ከእርዳታ ሰጭው ኮሚሽን ጋር ሆኖ በችጋር በሚጠበሱ ወገኖች ላይ የሚነግድ የሰው ጭንቅላት ባለበት መሬት ላይ አንተና ደጋፊዎችህ ደም እንዳትሰጡ እንቅፋት መደረጉ የተንኮላችን ጆኒያ ሙሉ መሆኑን ያሳያል።
    በቅርብ አንድ የወለጋ ተወላጅ ከሆነ ኢትዮጵያዊ ጋር ስንጫወት እንዴት ስንት በእውቀት የላቁና ሃገራቸውን የሚወድ ያፈራችው ያቺ ውብ እና ለም ሃገር ህጻናትና ሽማግሌዎች የሚገደሉባት ሆነች አልኩት። ስማ ወንድሜ በኦሮሞ ስም የሚነግድበት ብዙዎች ናቸው። ግን በወለጋ በተደጋጋሚ የሚደረገውን ግድያ የሚፈጽሙትና የሚመሩት የትግራይ ልጆች ናቸው አለኝ። እንዴ ምን ነካህ ከየት መተው ስለው። በእኛው አቆጣጠር በ 1977-78 ደርግ በድርቁ ምክንያት ከትግራይ፤ ከሽዋ፤ ከወሎ አምጥቶ በወለጋ ካሰፈራቸው ውስጥ ይበልጦቹ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። እነዚያ እዚሁ ተወልደው ያደጉት ኦሮምኛ ተናጋሪ ትግሬዎች ናቸው ግፉን የሚፈጽሙት ብሎኝ ቁጭ። እንዴ ኦሮሞዎች የሉበትም እያልክ ነው ስለው። አሉበት እንጂ። አመራሩ ለስም ከላይ ኦሮሞ ይሁን እንጂ ቀጥታ ትዕዛዝ የሚቀበሉት ከወያኔ ነው። የግድያው መክፋትና ፍጅቱን ያጧጧፈውም በዚያው በወያኔ የሚመራው የኦነግ ሸኔ ከሚቀበለው ትዕዛዝ የተነሳ ነው አለኝ። ስማ ሌላ ልንገርህ እኔ ያለሁት ወለጋ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በወለጋ ይኖራሉ። አንድንም የሚነካቸው የለም። ይነኩም እያልኩ አይደለም። ግን አማራ መርጦ ማጥፋትን የመረጠው ወያኔ በግንባር ቀደምነት ሲሆን ኦነግ ሸኔ ሥራ አስፈጻሚ ነው በማለት በስፍራው የታዘበውን አስረዳኝ።
    ግብረ ሰናይ በሚል ስም ሰይጣናዊ ሥራ አዲስ አበባ ላይ ተቀምጦ የሚፈጽም የሰው ጭንቅላት ጫካ ገባ ከተማ ኖረ ዞሮ ዞሮ እሳቤው ዘረፋና ብሄርተኝነት ነው። ከግዕዝና ከትግርኛ ጋር ተቀራራቢነት ያለው “ሰናይ” የሚለው ቃል በጎ፤ ቅን፤ መልካም ወዘተ ማለት ነው። ኤልሻዳይንና ሰናይን የሚያክል ስም ተሸክሞ ረሃብተኛን የሚዘርፈው ቡድን ያ በፊትም ከስርቆት ጋር የተላመደ በመሆኑ ከራሱ ደስታ በስተቀር የሰው ልጅ መከራ አይታየውም። በዚህች ምድር ነው አንተና ደጋፊዎችህም ነፍስ አድን የሆነውን የደም ልገሳ እንዳታደርጉ የተከለከላቹሁት። ምን አይነት ሃገር ናት ግን ኢትዮጵያ? የሞተላትን ትታ የገደላትን የምታበላ? አይዞን:: የሚሆነውን ቆይቶ ማየት ነው። ይነጋ ይሆን? ማን ያውቃል? በቃኝ!

  4. ለቴዲ አፍሮ ቅድሚያ ራሱን ማስተዋወቅ እና ማተለቅ፣ ገንዘብ መሰብሰብ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

av5435h sri lankan protesters surround presidential residencejuly
Previous Story

ዕንቅፋትን አለማንሳት ለሞት መመቻቸት ነዉ፡፡

welkeit
Next Story

የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት እውነታዎች (ከታሪክ፣ ከሕግ እና ከስነ ሕዝብ ምህንድስና አንጻር)

Go toTop