እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ በዉስጧ የሚፈጠሩ ልጆቿ ፍየል ሁለት ወልዳ አንዱ ለመጻፍ ፤አንዱ ለወናፍ እንዲሉ የናት ጡት ነካሾች በዘመኗ አታጣም፡፡
ለአለፉት የጭለማ ዘመን በህዝቦች ደም እና ዕንባ ዕድሜያቸዉን የሚገፉ የአገር እና ህዝብ መከራ የማይሰማቸዉ ዛሬም በህዝብ እና በአገር ስም የሚደርሱት ግፍ ቀጥሏል፡፡
በ1960 ዎች የህዝብ የለዉጥ እንቅስቃሴ ዉስጥ በመቀላቀል ኢትዮጵያን የማፈራረስ ስዉር ሴራቸዉን ጀምረዉ ዛሬ በተለያየ መንገድ ገፍተዉበታል ፡፡
አሁን ላይ ከዚያን ጊዜ የሚለዩበት ስንቅ እና ትጥቅ ለኢትዮጵያ እና ለአገራቸዉ ከሚሰሩት በላቀ ሁኔታ በሚጠሉት ህዝብ እና አገር መኃል ሆነዉ የሚያገኙ መሆናቸዉ ነዉ ፡፡
በዚያን ጊዜ በኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት ከዉስጥ ከኢትዮጵያ ህዝባዊ ሠራዊት ጦር ጋር የለበሰዉን መስለዉ ፤ ከቀመሰዉ ቀምሰዉ እያደሩ አመች ባሉት ጊዜ እና አጋጣሚ ጦሩን ከህዝብ እና ከመንግስት የሚያጋጩ ፤ ሲመች ከሶማሊያ ጦር ጋር ወግነዉ የወጉ ፤ያስወጉ እንዲሁም የሶማሊያ ዜግነት እና ቅጥረኛ ወታደር ሆነዉ የኢትዮጵያን ጦር የወጉ ከኃዲዎች እና ባንዳዎች ነበሩ ፡፡
ዛሬ ላይ የአገሪቷን መከላከያ ሆነ የሌሎችን የፀጥታ ኃይሎች ልብስ መልበስ እና መመሳሰል ለነዚህ ጠላቶች ቀርቶ የኢትዮጵያን ስም እና ባንዲራ ሳያሳልሱ በሚጠሩት የሚታወቅ ነዉ ፡፡
በዓማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ላይ ጥቃት ተመሳስሎ በመግባት በክልል የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት መፈፀሙን ስንሰማ ብናዝንም ዕዉነት አለ ብለዉ ለአገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ የከፈሉት የህይወት ዋጋ ግን በትዉልድ እና በታሪክ ህያዉ ሆኖ ይኖራል ፡፡
ጥያቄዉ መሆን ያለበት ለዚህ ከፍተኛ የሆነ የሰዉ ልጆች አሰቃቂ በደል እና ግፍ ከፋይ እና ተጠያቂ የማይኖረዉ ለምንድን ነዉ ፡፡
እንኳን ለብስ አይደለም የኢትዮጵያ ህዝ ያልታተቀዉን የህዝብ ሀብት (የጦርመሳሪያ) የታጠቀ አፍራሽ እና ከኃዲ ስብስብ በዚህ ቅርበት እና ዝግጂት ጥፋት አስኪያደርስ የት፣መቸ እና በየት እንደመጣ አለማወቅ እንዴት ጥቻላል፡፡
መኃል አገር ላይ ሆኖ ህዝብን እና አገርን የሚያፈርስ ኃይል ከሰማይ ነዉ ከምድር የመጣ ፡፡
ለዚህ የሚጠየቀዉ የመንግስት መዋቅር ላይ የሚሠራዉ እንጂ አጥፊዎች አይሆኑም ፡፡
ህዝብ ካለቀ …ጠላት የትፋት ስራዉን ካጠናቀቀ በኋላ ጂብ ከሄደ ዉሻ ጮኸ …ዓይነት የጠላት ከወገን ጋር መቀላቀል እና መመሳሰል በተለያየ ጊዜ የሚታይ እንደመሆኑ በምንም ዓይነት ሁኔታ የለብስ እና ባንዲራ መያዝ የጠላት እና የወዳጂ መለያ ሆኖ ሊታይ አይገባም ፡፡
ጠላት እና ወዳጂ ሊለይ የሚችለዉ በልብስ እና ባንዲራ መመሳሰል ሳይሆን ለአገር እና ህዝብ ቀድሞ ከፊት በመገኘት ብቻ ነዉ ፡፡
የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ (አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ) ለምን ያዛችሁ በሚል ህዝብ በሚወነጀልባት አገር በኢህአዴግ ህገ መንግስት የሚፈቀደዉን ባንዲራ እና አልባሳት መደረብ ኢትዮጵያዊ ነዉ ማለት “ ሁሉም ባለሻሽ ቄስ ” ማለት ነዉ ፡፡
“ወፍ በአናትችን ላይ አይብረር አንልም ፤ ጎጆ እንዲሰራብን ግን ፈጽሞ አንፈቅድም ፡፡”
ለአገር እና ለህዝብ ዕድገት ጠንቅ የሆኑ የአገር እና ህዝብ ጠላቶች ዕንቅፋትነት በአድርባይነት እና በምንቸገረኝነት ማለፍ ለተዉልድ እና ለአገር እንቅፋት ማቆየት ነዉ፡፡ ዕንቅፋት እያየ የማያስወግድም ራሱ ዕንቅፋት ነዉ ፡፡
ነፃነት ወይም ሞት !!!
NEILOSS –Amber