July 16, 2022
16 mins read

የህወሃቱ የአቶ መለስ ዜናዊ ታሪካዊ ስህተት በጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ሊደገም ቋፍ ላይ ይመስላል

ይጠንቀቁ እንላለን!!

meles and Abiyእንደሚታወቀው የሃገር ኢትዮጵያ ርዕሰ ብሄሮችና ጠቅላይ ሚኒስትሮች የሚታይባቸው ትልቁ ችግር እራሳቸውን ከሕዝብና ከሃገር በላይ አግዝፈው ማየታቸው ነው።

ከዚህ ባሻገር በአገር ማህበራዊ፣ኢኮኖሚ፣ፓለቲካ፣ ጆግራፊ፣ ታሪክ ወዘተ “ከኛ በላይ ላሳር” ማለታቸው እና ወሳኞችም “እኛና እኛ “ ብቻ ነን የሚል አባዜ የተጠናወታቸው በመሆኑ ነው።

ሕግ እንደሚያስረዳው “ ማንኛውም ሰው ከአምላክም ሆነ ከምድራዊው ሕግ “ በታች እንደሆነ ያትታል። ይህ ሆነ እያለ የሃገራችን መሪዎች  የሚናገሩት፣ የሚፈፅሙትና የሚያስፈፅሙት ወዘተ. ጉዳዮች ከሕግ ፅንሰ ሃሳብ ጋር የሚጣረዝ መሆኑ የሚገርም፣ ግራ የሚያጋባና የሚያሳስብ ጉዳይ ነው።

ይህን ካልን ዘንዳ በመሪዎቻችን ዕፀፅ ሃገረ ኢትዮጵያ መልክአ ምድሯ እየተሸራረፈና እየተቆራረጠ እሁን ካለችበት ደረጃ የቆዳ ስፋት ጠባ እድትታይ ምክንያት ሁነዋል። ከዚህ ላይ የጥንቷን ኢትዮጵያ አፍሪካ አፍሪካ የሚለውን ስያሜ ከማግኘቷ በፊት  ኢትዮጵያ ትብላ ትጠራ እንደነበረ ፣ የፓስፊክና የህንድ ውቂያኔስ ኢትዮጵያ ውቅያኖስ ይባሉ እንደነበር ለመዘርዘር አይዳዳኝም። የቅርቡን እንጂ።

ጓድ መንግስቱ ኃይለማሪያም የአሳጡን መክሊት

ከላይ እንደገለፅኩት በዚህ አጭር መጣጥፍ ትኩረት ለማድረግ ያሰብኩት የሃገርን የምልክአ ምድር አከላለል (Geographical makeup) መሪዎቻችን ለመወሰን እና ለማስወሰን የሚሄዱበትን ርቀት ምን ያህል ዕፀፅ እንዳለበት፣ ለሃገርም መርዝና የሚፈነዳ ቦንብ ለትውልድ እያስታቀፉና እየለኮሱ እንደሚያልፉ ለማሳየት፣ ለማስተማርና “አረ ተው፣ ካለፉት መሪዎች ተማሩ” ለማለት ነው።

ጓድ መንግስቱ ኃይለማሪያም ከሰሩት ትልቅ ሃገራዊ ስህተት “ የቆጡን አውርድ ብላ የብብቷን ጣለች” እንዲሉ ጅቡቲ በፈረንሳይ መንግስት ስር ለመቶ ዓመት ከቆየች በኋላ ወደ እናት ሃገሯ እድትቀላቀል ሲጠየቁ “እኛ የራሳችን አንሰጥም ፣ የሰውም እንፈልግም “ በማለት የራሳቸውን ስሜትና አዕምሯቸው የነገራቸውን አስተሳሰብ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት አማካሪዎችን ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ ሳያማክሩ በራሳቸው ፍቃድ ብቻ ጂቡቲ እራሷን የቻለች ሃገር እድትሆን ምክንያት ሁነዋል። በዚህም የተነሳ የጂቡቲ ወደብ ባሌቤትነታችን ከማጣታችን ባሻገር አሁን ፣ አሁን ጂቡቲ ለሃገረ ኢትዮጵያ ተገዳዳሪና በሃገረ ኢትዮጵያ ስር የነበረች ምድር መሆኗን ረስታ ማንጓጠጧንና ማስፈራራቱን ስራየ ብላ ተያይዛዋለች።

ጓድ መንግሥቱ ኃይለማሪያም  “አይመጣንም ትተህ ይመጣልን ሃስብ” የሚለውን አነጋገር ሳያገናዝቡ በጦር ኃይላችው በመታበይ “ኤርትራ” የትም አትሄድም ብለው ነበር ። ይህን ውሳኔ በለበ ሙሉነት ይወስኑት ፣ በልባቸው ፈቃድ ቢሆንም ። ነገሩ ግን የተገላቢጦሽ ሆነ።

የህወሃት ትግራይ /ኢሕአዴግ/ ስርዓት የኢትዮጵያ እንገት/መሰረት ኤርትራን ያሳጣን ገቢር፣

የደርግ መንግስት በህወሃት ትግራይ ሰራዊት በ1983 ዓ.ም. ባልጠበቀ ሁኔታ ሲገረሰስ ከጓድ መንግስቱ ኃይለማርያም ትምህርት መውሰድ ባለመቻሉ ድጋሚ ሃገራዊ ክህደትና ስህተት ፈፀመ።

ኤርትራ የጥንታዊዋ ኢትዮጵያ መሰርትና እንገት ከምሆኗ ባሻገር በተለይ በዘመነ አክሱማዊያን መንግሥታት አንደ አዱሊስ፣ ምፅዋ፣ አኒሽ ፣ መሰል ደሴቶችንና ቀይ ባህርን አቅፋ የያዘች በመሆኗ  የንግድ ማእከል ሁና ለሃገረ ኢትዮጵያ ስትራጀቲክ ጠቀሞታዋ ከፍ ያለ እንደነበር ልብ ይሏል።

የኮሎኒያሊዝም ጠባሳ ባመጣው ጣጣ ኤርትራ ለተወሰነ ጊዜ በጣሊያን ስር ስትተዳደር ቆይታለች። ከዛም ጊዜው ደርሶ በሕዝቡ መልካም ፈቃድና በሪፍረደም ወደ እናት ሃገሯ ተቀላቅላ እንደ አንድ ክፍለ ሃገር ተቆጥራ ትተዳደር ነበር።

ከዛም የኤርትራ ሕዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ፍላጎቱ በመነፈጉ ይመስላል አመፅ እየተቀሰቀሰ እነ “ጀህባ” ከዚያም “ሻቢያ” የሚባሉ አማፂ ቡድን መስርተው ወደ ለየለት የነፃነት ትጥቅ ትግል ውስጥ ገቡ ።

ከዚያም ህውሃትም “_ማን ከምን ያንሳል” በሚል ህሳቤ ታላቂቱን ትግራይ እንገነባለን በሚል ህሳቤ ነፍጥ አነሳ። ከዚያም “በለስ ቀናቸውና” ታላቅዋን ኢትዮጵያ ለመምራት በቁ።

ይህን አተታ ለመንደርደሪያ አቀረብኩት እንጂ ፣ የተፈፀመውን ታሪካዊ ስህተት ማንም ያውቀዋል። ከዚያም የታላቂቱ  ትግራይ ምስረታ በህውሃት ጋሻ ጃግሬነት ኤርትራን በማስገንጠል ቀጠለ። የኢትዮጵያ አምላክ አይተኛምና አስገጣዮችና ተገጣዮች “ የኢትዮጵያን ሃብት እንደቅርጫ ሲከፋፈሉ ‘ የአንተ በዛ የእኔ እነሰ በሚል ‘ ውዝግብ ተፋለሱ፣ ደም ተቃቡ” ። ከዚህ ክስተት የማይማር መሪና ቡድን ካለ ፣ “ነግ ለኔ ነውና” እረጋ ብሎ ቢያስብ ይሻላል እንላለን።

የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ “የአፍ ወለምታ፣ አቋም የለሽና የተዘበራረቁ ህሳቤዎች

መቸም ኢትዮጵያ ሃገራችን እደአለመታደል ሆኖ ቀደምት መልካም መሪዎችን እስከ ክብራቸው እያወደስን፣ ከአፄ ምኒሊክ እና ከአፄ ኃይለስላሴ ወዲህ አስተዋይ፣ጥበበኛና አርቆ አሳቢ መሪ አላገኘችም። የቅርቦቹ መሪዎቻችን በተተረከላቸው ተጨባጭ ባልሆነ ትርክት ተበርዘው ፣ ቂም አዝለውና ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለተወለዱበት ዘር በመወገንና በዘረኝነት በመነውለል ሃገረ እትዮጵያን እዳትረጋጋ፣ ህዝቡም በመከራና በሰቆቃ ኑሮውን እንዲገፋ እያደረጉት ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በብልጠትም ሆነ በታሃምር ህወሃትን ከስልጣን መንበሩ አሽቀንጥረው ወደ ነበረበት “ደደቢት፣” በርሃ ከወረወሩት በኋላ ሃገረ ኢትዮጵያን በማቆለባበሳቸው “ሙሴው መሪያችን መጣልን፣ አገኘን” ተብለው ተዚሞላቸዋል፣ ቅኔም ተዘርፎላቸው ነበር።

ነገር ግን ሰሞነኛው ቅጥ ያጣ ንግግራቸው፣ የአቋም ማፈግፈግ እሳቢያቸውና መጡበት ለሚባለው ብሄራቸው ማሸርገዳቸው እንደ ቀደምት መሪዎቻችን ጓድ መንግሥቱ ኃይለማሪያም ስህተት ፣ እንደ ህወሃት ሥልጣን ኮረቻ ላይ ነኝ በሚል ህሳቤ ተኩራርተውና እቅለቢስ ሆነው “ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይን የምትመስል ኢትዮጵያ ለመስራትና ያልነበረ መልክአ ምድራዊ አወቃቀር እና ታሪክ  ለመንደፍ ከሞከሩ አንደኛ ለስልጣናቸው መንሸራተት ምክንያት እንደሚሆን ባንጠራጠርም ፣ ከወዲሁ “ከድጡ ወደማጡ “ እንዳይሆንባቸው “ያስቡበት” እንላለን።

ሰሞኑን በ16ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብስባ ላይ “ወልቃይትን” አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ “ሕገ መንግሥቱን መሰረት በማድረግ በማያዳግም መልኩ በህዝብ ውሳኔ የወልቃይትን ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመጭው ትውልድ ጥያቄ በማያስነሳ መልኩ እንፈታዋለን” ብለዋል።

መልካም ነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ። የሚያዋጣወትን እርስዎ ያውቃሉ። በእኛ በኢትዮጵያኖች፣ እልፍ ሲል አማሮች ፣ ጎንደሮችና ወልቃይቴዎች የወልቃይት ጉዳይ የአለቀና ምላሽ ያገኘ ጉዳይ ነው” እንላለን።

ልቡ የተነፋው የህውሃት ግልገል በጉልበት ፣ ያለ ሕግ አግባብ ሊነጥቅ ያሰበውን ወልቃይት ፣ ጠገዴና የሰቲት ሁመራን እፅመ እርስታችን በአምላክ እርዳታ አስመልሰናል።

ከእንግዲህ በኋላ “ፍየል ወዲህ ጥምዝምዝ ወዲያ” ማለቱ ከላይ እደጠቀስናቸው የሃገር ጠንቅ ታሪካዊ ስህተቶችን እንዳይደግሙ የብልፅግና ፓርቲን እና ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን በጥብቅ እንመክራለን።

አሰብና ጂቡቲን እሳልፎ በመስጠት ኢትዮጵያን ያለወደብ ማስቀረት ምንኛ እንደጎዳት ልብ ይሏል። ይህን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያን ድንበር ወልቃይትን ለማይመለከታቸው፣ እርስታቸው ላልሆነ ቡድኖች ለመቸር የታሰበ አጉል ህሳቤና መደራደር መሞከር  ከክፋቶቹ ሁሉ የከፋ ከሃዲነትም ነው።

የወልቃይት ፣ ጠገዴና ሰቲት ሁመራ ጉዳይ የሚመለከተው የአማራ ፣ ጎንደርና ወልቃይቴው ብቻ ሳይሆን መላ ኢትዮጵያዊ ነው እንላለን ።

ኢትዮጵያ እንገቷን ኤርትራን አሳጣችሁ። ጉሮሮዋን ጅቡቲን እሳልፋችሁ ሰጣችሁ ፣ እሁን ደግሞ ወልቃይት የልብ ትርታዋን፣ የኢኮኖሚ መሰርቷንና ደንበሯን ለህውሃት ተገንጣይ ከዛም አልፎ ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት መሞዳሞዱ አይበጅም። መሪዎችን ብቻ ሳይሆን የዚህ ህሳቤ ያላቸውን ቡድኖች ሁሉ ያስጠይቃል፣ ለደም መፋሰሰም ምክንያት እንደሚሆን እትጠራጠሩ።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ “ የተናገሩት ከሚጠፋ ምን ያሉት ይጥፋ” እንዲሉ በተደጋጋሚ ወልቃይት፣ ጠገዴ ፣ሰቲት ሁመራ የኢትዮጵያ ፣ የአማራና የጎንደር ነው ፣ ባህሉ አማራዊ ፣ ቋንቋው አማረኛ ነው በማለት ደጋገግመው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት መስክረዋል። ክዚያም አልፎ አማራው ጎንደሬው ወልቃይትን” ህወሃት በኃይል ሊወሰድ እንደሞከረው ወቅቱ ደርሶ ወልቃይቴዎች በኃይል እርስታቸውን አስመልሰዋል” በሚል ደጋግመው ለሕዝበ ኢትዮጵያዊው አስረግጠው ተናግረዋል። ይህን ውሳኔዎትን በሕግ ማእቀፍ ማረጋገጥ ከቻሉ እሰየው የሚያሰኝ ነው። ነገርግን የታሪክን ፣ የቱፊትን እና እውነታን ሸሽተው” በሕገ -መንግስት ፣ በሕዝብ ውሳኔ ገለመሌ ፣ ገለመሌ የወልቃይት ጉዳይ ይፈታል” ማለቱ አሁን ልነንነግረወ ባይገባን ፣” እቺ ሸሸት ፣ ሸሸት ለምን?” የሚል መልስ ስላለን በይደር እናስቀምጣት ብለናል።

ከዚህ ባሻገር ወልቃይት ተጉዘው መቸም ጭዋታ አዋቂ ነወትና ፣ “ ከጎንደር አማራ ጋር ተጋብቸ ፣ ጥሎሽ ወስጃለሁ “ ብለዋል ፣ እኛ አማራዎች ፣ አማችዎት ነን ፣ ልጆችዎም በአንድ ወገን አማራ ናቸው። ይህን በጥሎሽ ያገኙትን የኢትዮጵያ፣ የአማራ፣ የጎንደር ከዚያም አልፎ የልጆችዎን ውርስ ጠብቀው የማኖር ግዴታ አለብዎት እንላለን።

አንድ መሪ የተናገረውን ቃል ሳይንሸራተት መጠበቅ፣ ታሪክን ፣ቱፉትንና እውነታን ተመርኩዞ ውሳኔ መስጠትና ማሰጠት ግዴታውና የሚጠበቅበዎት ኃላፊነት ነው።

“ምከረው ምከረው ካልሆነ መከራ ይምከረው” የሚሉው ጥቅስ ለሚመለከተው ይድረስ እንላለን።

 

ከተዘራ አሰጉ ። ክምድረ እንግሊዝ።

https://youtu.be/SMVpLbQZ3PY

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop