“እኛ ሐዘን ስንቀመጥ፣ ሌላው ዓለም ለሜዳሊያ ይፎካከራል” – ጎልዳሜየር

በሙኒክ ኦሎምፒክ እስራኤላውያን ስፖርተኞች በማንነታቸው ተመርጠው ሲገደሉ፣ የተረፉት ደግሞ አቋርጠው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። የእስራኤል ሕዝብ ማቅ ለብሶ ለሐዘን ሲቀመጥ፣ ሌላው ዓለም የኦሎምፒክ ጨዋታውን ቀጥሎ የሰበሰቡትን ሜዳሊያ ይቆጥራሉ።

ያኔ የእስራኤል ዐራተኛዋ ጠቅላይ ሚንስትር ጎልዳሜር እንዲህ አለች። “እኛ የትም ብንሄድ ተመርጠን እንገደላለን። የኦሎምፒክ ወርቅ እንዲያመጡ የላክናቸው ልጆቻችን ተለይተው ተገደሉ። እኛ ሐዘን ስንቀመጥ፣ ሌላው ዓለም ለሜዳሊያ ይፎካከራል። ብቻችንን እንደቆምን ልናውቀው ይገባል። መፍትሔውም ራሳችን አጠንክረን፣ ሕዝባችንን ማስከበር ብቻ ነው” አለች።
ከዚያች እለት ጀምሮም የጥቁር መስከረም አባላቱን በዓለም ጥግ ተዟዙረው በቀል ወሰዱባቸው።

በዚህች ሀገርም ተመሳሳይ ነገር ሆኗል። ዐማራ ተመርጦ ይገደላል። ሌላው ቀርቶ ማልቀስ ተከልክለናል። ዐማራ በሕይወት ስለመኖር ሲጨነቅ፣ ሌላው ህዝብ ስለ ጥቅል ጎመን ይጨነቃል። በሕዝብ ተወካዮች መድረክ እውነተኛ የዐማራ ተወካዮች በዐማራ ላይ የሚደርሰው ሽብር እንዲቆም ሲታገሉ፣ የሌላው ህዝብ ተወካይ ስለ መንገድ ጥገና አብዝተው ይሟገቱ ነበር።
ዐዲሲቷ ኢትዮጵያ ማለት ይህች ነት። እውነታው ይሄ ነው። የዐማራ ሞት ለአቅመ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ማለት እንኳን አልበቃም። ታዲያ አንዳንዶች ስለ የትኛዋ ሀገር ነው የምትጨነቁት? ነው plato ስላሰባት “ideal state” ነው የምታወሩት?

በግሌ ገዳዮቻችን ሐዘን ምን እንደሚመስል እንዲያዩት እፈልጋለሁ። በግሌ ገዳዮቻችን በገጀራ ተጨፍጭፎ መሞት እንዴት አስከፊ እኔደሆነ እንዲረዱት እፈልጋለሁ። በግሌ ገዳዮቻችን ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው በእሳት መቃጠል እንዴት እንደሚጠዘጥዝ እንዲቀምሱት እፈልጋለሁ። በግሌ ገዳዮቻችን የዐሥራ አምስት ቀን ልጅ ከፊታቸው መገደል እንዴት ልብ እኔደሚሰብር እንዲያውቁት እፈልጋለሁ።

በግሌ ገዳዮቻችን ሀገር ጥቁር ሸማ እንዳታለብሳቸው እፈልጋለሁ። ፈርሳም ቢሆን።
ዐማራ በሕይወት የመኖር መብቱን ተቀምቶ ሲብሰከሰክ፣ ሌላው ሕዝብ ስለ ጎመን ሲጨነቅ ማየት አልፈልግም። ጉዳታችን ካልተሰማቸው፣ በመጎዳት እኩል እንሁን እላለሁ። በአንድ ሀገር እየኖርን ተመርጠን ከተገደልን፣ የእኛ ሐዘንም ካልተሰማቸው ስለየትኛው አብሮነት ነው የምትጨነቁት? በግድ ነው እንዴ?
ሥር ነቀል ሕዝባዊ የዐማራ አብዮት ለዐማራ ህልውና

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ 26.2 ሚሊዮን ህዝብ የስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ይፈልጋል፣በድርቁ 1.7 ሚሊዮን እንሰሳት ሞተዋል!

ዘፋኒያህ ዓለሙ

1 Comment

  1. ጎልዳሚየር ይህን ስትናገር የገማው አለም ለአይሁዶች ያለውን ጥላቻ ጠንቅቃ ከመረዳት ነው። የዛሬ 50 ዓመት ገደማ እስራኤልን ወክለው በጀርመኗ ከተማ ሙኒክ ላይ የተገደሉትን ዜጎቿን አስባ ነው። ጎልዳሜር ለሞሳድ በሰጠችው ጥብቅ ትዕዛዝ ሁሉም ገዳዪች ሲገደሉ የቀረው አንድ ነው። እሱንም የሞሳድ የስለላ መረብ ደርሶበት በሚነዳው መኪና የተጠመደው ቦንብ ወንድሙ ቀድሞ መኪናውን በማንቀሳቀሱ ወንድምዬው ሞቶ ተፈላጊው ሳይሞት ቀረ። ዛሬም ግን ፍለጋው ቀጥሏል።
    Mossad: The Greatest Missions of the Israeli and Rise and Kill First: The Secret History of Israel’s Targeted Assassinations እነዚህን ሁለት መጽሃፍ ላነበበ የቱን ያህል የስለላ መረባቸው ለህልውናቸው ፍቱን መድሃኒት እንደሆነ ያመላክታል። አሁን ከቁራሽ ተርፋ በብሄርና በቋንቋ ሰልፍ የምትናወጠው የሃበሻዋ ምድር እንኳን በግፍ የተገደሉ ወገኖችን ደም መበቀል ቀርቶ ድረሱልን እያሉ ኡኡታ ለሚያሰሙትም መልሳቸው ” ከበላይ አካል አልታዘዝንም” ነው። በሻሸመኔ፤ በወለጋ፤ በቤኒሻንጉልና በሌሎች ከተሞች የሆነው ይህ ነው። ጉራ ራት ይሆን ይመስል ሁሌ ተዘጋጅተናል፤ ተጠናክረናል፤ የሃገሪቱን ዳር ድንበር አናስነካም እየተባለ ይደነፋልናል። ግን የራሱ ቤት ሲቃጠል ማጥፋት የተሳነው መንግስት ምንም ቢደሰኩር ሰሚ የለውም። በቅርቡ ከወለጋው እልቂት ተርፈው ሆለታ (ገነት) ላይ በታጣቂዎች ወደ መጡበት እንዲመለሱ የተደረጉት ወገኖች እንባ ፈጣሪ የሚባለው አለ እንዴ እስከ ማለት ያደርሳል። ሌላው ቀርቶ ከተሳፈሩበት መኪና እንኳን እንዳይወርድ ነበር የተደረገው። ግፍ ማቆሚያ በለሌበት ምድር ላይ ተቀምጦ የሰላም ሚኒስቴር መሾም ምን የሚሉት ቀልድ ነው?
    አሁን ወያኔ ከሱዳን፤ ከቅማንት፤ ከኦነግ ሸኔና ከሌሎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሚያዛቸው ጋር አብሮ ጦርነት ከፍቷል። ችግሩ ያለው ከትግራይ ነው። ሱዳን የትግራይ ጉዳይ አስፈጻሚ ናት። የጠ/ሚሩ የናይሮቢ የሰላም ጥሪና ከአምባገነኑ የሱዳን መሪ ጋር መነጋገሩ ለፎቶ እንጂ ሱዳን በፊትም አሁንም ለኢትዮጵያ መከራና ችግር አዝናቢ ናት። የሱዳን ህዝብ ጦርነት ከኢትዮጵያ ጋር አይፈልግም። ዳቦ አሮበታል፡፤ ሁለት ችጋራም ሃገሮች ቢቆራቆሱ ሌላው ዓለም ይስቅብናል እንጂ የምናተርፈው ነገር አይኖርም። ግን ከጀርባው አይዞህ የሚለው የሚያስታጥቀው መንግስትና ሰራዊት ወይም አጥፊ ቡድን በራሱ አስቦ የመኖር መብቱን ተቀምቷል። በመሰረቱ የሱዳን መሪ አል ሲሲ ነው። የሱዳኑ ጄኔራል እሱና አሜሪካ አርግ ያሉትን ነው የሚያደርገው። በዚህ ላይ ወያኔ ደግሞ በሰረቀውና ከውጭ በሚሰበስበው ገንዘብ የሱዳን ሰራዊትን ይገዛበታል። ሰው እንዲያፍኑ፤ ሰው እንዲገሉ፤ ሰው ከሃገር እንዲያባርሩ፤ በፓርት ሱዳን ትጥቅና ስንቅ እንዲገባላቸውና በተመድ መጠለያ ከገቡት የትግራይ ተወላጆች መካከል በግልጽ ወታደራዊ ምልመላ እንዲደረግ እንዲፈቅድ ያደርጋል። ኢትዮጵያ የታጠረችው በውጭና በውስጥ ተንኮል ነው። ሁሉም ወሬ ያናፍሳል፤ የተለጠጠ፤ የፈጠራ፤ እውነት ጥቂት ያለበት በዚህም በዚያም ይዘራል። እውነቱ ግን በየጥሻው ወድቆ ቀርቷል። ወታደር ሆኖ ሃገሩን መጠበቅ የማይፈልግ ወጣት ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ቢለፈልፍ ዋጋ ቢስ ነው። ውጊያው የቃል ሳይሆን የተግባር ነው። ፍትጊያው የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው። እስራኤሎች በአረቦች ተከበው እስከ ዛሬ ድረስ ሃገር ሆነው ሊኖሩ የቻሉት በቁርጠኝነታቸው ነው። እኛስ? መቼ ነው በውስጥና በውጭ ህዝባችን የሚያሸብሩትን አጥፍተን እፎይ የምንለው? ለእኔ አይታየኝም። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share