“የሰሜን ዕዝ ከጀርባው በህወሃት እንደተወጋው ሁሉ፤ ኢዜማ ለውጥ ያስፈልገዋል ያልን ሀይሎችም በዶክትር ብርሃኑ ነጋ ደጋፊዎች ከጀርባችን ተወግተናል።” – ሀብታሙ ኪታባ ገመቹ

ብርሃኑ ነጋ እንዲመረጥ የሚፈልጉ ቡድኖች ቀደም ብለው የምርጫ መከታተያ ቅፅ አዘጋጅተው ጉባኤውን ለመጥለፍ ሲሰሩ ይዘናቸዋል። እነዚህን ሰዎች እንዲታገዱ ብናደርግም፣ የታገዱትን ጨምሮ ባዘጋጁት ቅፅ በዝርዝር የብርሃኑ ነጋ ቡድኖች ብለው በስምና በፎቶ የጠቀሷቸው ሰዎች በኢዜማ ጉባኤ ተመርጠዋል።

በኢዜማ ጉባኤ ከመንግስት ጋር በመስራታችን ያጣነው ተቀባይነት ዙሪያ ሪፖርት እንዲቀርብ ጠይቄ ነበር። ነገር ግን ብርሃኑ ነጋ በጉባኤው ስለ ትምህርት ሚንስቴር ሪፎርም እና ስለ ህወሃት ብቻ ዝርዝር ሪፖርት በማቅረብ ጊዜው እንዲሄድ አደረገ። በዚህም ስለ ኢዜማ ችግሮች ሳንመክር ጉባኤው ተዘጋ።

በርካታ የኢዜማ ሰዎች ከኢዜማ ስም በፍቅር የወደቁ ይመስለኛል። ኢዜማ በስሙ ሳይሆን፣ በተግባሩ ነው ልንመዝነው የሚገባ። በስም ብቻ ለውጥ ማምጣት ቢቻል ኑሮ እንደ ብልፅግና መልካም ስም የያዘ የለም ነበር።

ብልፅግና የብሄር ፖለቲካን በማከም ለውጥ አመጣለሁ የሚል የብሄር ፓርቲ ነው። ኦሮሚያ ክልል ሲሄድ ለኦሮሞ የሚመቸውን፣ አማራ ክልል ሲሄድ ለአማራ የሚመቸውን በመናገር እድሜ ለማስረዘም የሚጥር የብሄር ፓርቲ ነው። እንዴት እንደሆነ ባላውቅም አሁን ላይ አዲስ አበባ ኦሮሞ ትራፊክ ፖሊሶች በዝተዋል። ጥፋት አጥፍቸ ይዘውኝ፣ መንጃ ፈቃዴን ስሰጣቸው ስሜ ሀብታሙ ኪታባ ገመቹ ስለሚል ሳይቀጡ ያልፉኛል። ከባድ ጊዜ ላይ ደርሰናል።

ለአዲስ የፖለቲካ ባህል ብለን ትተነው እንጂ፣ የሰሜን ዕዝ ከጀርባው በህወሃት እንደተወጋው ሁሉ፤ ኢዜማ ለውጥ ያስፈልገዋል ያልን ሀይሎችም በዶክትር ብርሃኑ ነጋ ደጋፊዎች ከጀርባችን ተወግተናል።

(ሀብታሙ ኪታባ ገመቹ – የኢዜማ ስራ አስፈፃሚ)
ፈለገ ግዮን

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሁልጊዜ ወገንተኝነታችን ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ጋር ይሁን!

6 Comments

  1. I do not think this kind of cry baby politics makes sense as long as you have terribly failed and keep failing to beak your silence and to go with the politics of making true democratic change possible! Are you now telling us that you became aware of the existence of mistrust and betrayal among yourselves just recently?? Was it not clearly and plainly self-evident that you were in a very terrible political situation when your leaders declared that they hundred percent trust one of most politically idiots and morally bankrupt politicians of our time, prime minster Abyi Ahmed?
    So, if you are serious enough about the need to correct the very stupid and serious mistakes you have made for four years of total and general diester, get out of the political game that is being played in a very deep and wide bloodbath of innocent people!!! Mere politics of crying and barking will never make any sense!!

  2. ተው ህብታሙ። አልተመርጥክም! አንዷለም አራጌ “እንክዋን ደስ አልዎት” ብሎ የለ እንዴ? በዚያ ላይ የፓርቲህን ጉዳይ እዚያው ያዘው። ያውም ሥራ አስፈጻሚ ሆነህ? ለነገሩ እንደ ድሮ ቢሆን “አንጃ” ይፈጠርና እርስበርስ መገዳደል ይኖር ነበር። እንደ እነ “ጓድ ህ እና ለ” ማለት ነው። ከዚያ መውጣቱም ትልቅ እድገት ነው። ወጣት ነህ ተስፋ አትቁረጥ። ወይም ፓርቲውን መልቀቅህን በይፋ አሳውቅ። ምንም ይሁን ያለድርጅት ክፖለቲከኛነት ወደ ተቺነት/አክቲቪስትነት መቀየር እንደሆነ እንጂ የትም አያደርስም።

  3. አቶ ሃብታሙ ኪታባ በመጀመሪያ ደረጃ ብርሃኑ ጋር በሃቅ ተወዳድሬ ሃቅን አገኛለሁ ማለት ስለ ብርሃኑ ነጋ ሆነ ብሎ አውቆ የተሳሳተ ግ ንዛቤን ለራስ ማስጨበጥ ነው፡፡ ብርሃኑ በዚህ አሰራር ጥርሱን የነቀለበት ነው ይህን አስመልክተን ወደ ዉድድሩ ስትገቡ ልዩ ጥንቃቄ እንድታደርጉ አሳስበን ነበር፡፡ ብርሃኑ የጥልፍልፍ ኔት ዎርክ አለው በእኛው ገንዘብ አገራችንን እንዲያጠፋ ያቋቋምነው እሳት የሚባል የሚዲያ ተቋምንም በአንዳርጋቸው ጽጌ አማካኝነት የግሉ አድርጎታል፡፡ እንደምታውቀው አንዷለም አራጌን ኢሳት ላይ ጋብዘውት በማይሆን፤ባልተያያዘ፤ባልተገባ፤በመሪ ጥያቄ እንደማይሆን ሲያደርጉት ብርሃኑን ግ ን አልጠሩትም ይህ ሁሉ ሸር ነው አንዷለምም ወደ ኢሳት ስቱዲዮ መሄድ አልነበረበትም፡፡ ከኢሳት ይልቅ ቤቲ ታፈሰ የሚገባውን ክብር ሰጥታ አስተናግዳዋለች፡፡ የብርሃኑ የጥልፍልፍ መረብ ከዲስ እስከ አዲስ አበባ ተዘርግቷል ሰውዬው አብይ መሃመድ ሆነ እንጂ ብርሃኑና አረጋዊ እስከ አሁን ገዝግዘው በጣሉት ነበር፡፡ ሲጀመር እነ አንዷለም እንደ ጥጃ ሲታሰሩና ሲፈቱ የኖሩ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች እያሉ ብርሃኑ በምን መስፈርት ነው የኢዜማ መሪ የሆነው በዚህ ነገር የናንተም ሃላፊነት አለበት ያስጠይቃችኋል፡፡ ብርሃኑ ከኢሃፓ እስከ ቅንጅት ቀስተዳመና ዛሬ ደግሞ ኢዜማ ስራው እንዲህ ነው፡፡ እሱን አስመልክቶ የተለያዩ ወገኖች አስተያየት ቢሰጡም ብሬ ክፉ ጊዜን ጎምበስ ብሎና ባለ ስልጣንን ተጠግቶ ማለፍ ነው በሚል ዘይቤው እስከ አሁን ቀጥሏል፡፡ ድርጅቱን ጥላችሁ ካልወጣችሁ እረፍት የሚሰጣችሁ ሰው አይደለም፡፡ አገር ቤትም በጥልፍልፍ ልምዱ እንደ ዲሲ ግብረ ሃይል የአዲስ አበባም ግብረ ሃይል ለመቋቋም የሞራል ልጓም ስለሌለው ለህይወትም ማሰብ ጥሩ ነው፡፡ ሰውየው ስሙ ይሁን የትምህርት ማእረጉ ፕሮፌሰር በሚለው ማእረግ ተኮፍሶ እራሱን እላይ ሰቅሎ የሚኖር ሰው ነው፡፡ ሲጽፍ፤ፖሊሲን ይዞ ሲከራከር ሲያሳምን ታይቶ አይታወቅም ብቻ ጠበቅ ያለ ጥያቄ ሲጠይቁት መቆጣት ጠበቅ አድርገው ከሚጠይቁ ጋዜጠኞች እራሱን ማራቅ አንዱ የትግል ስልቱ ነው፡፡
    እንዴት ነው ከሊቃውንት በላይ ሊቃውንት ነኝ የሚል አንድ ተማሪው ከሆነው ከልደቱ አያሌው ጋር ቀርቦ በተለያዩ የሃገሪቱ ትኩሳቶች ላይ ውይይት ማድረግ የሚቸገረው? አንተ የሩቁን ትላለህ እዚህ ለብሽሽቅ የተመደቡ የሱ ሰራዊቶችን እነ ዳሹሬን አታይም? ግለሰቡ አንዳንድ ጥቅማ ጥቅሞችና ዳረጎት ቦታም እንደ ሰጡት ከዚህ በፊት ማብራሪያ ሲሰጥ አድምጠናል፡፡ የጩሉሌው ብሬ ጉዳይ ይህን ይመስላል መርካቶ ማደግ ጥቅሙ ለዚህ ለዚህ ነው፡፡ ከርሱ መገላገልህም እረፍት ስለሆነ በደረሰበት አትድረሱ፡፡ ግለሰቡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እዳ እንደሆነ መቀጠሉ አይቀርም በውርደት እስኪጠናቀቅ፡፡

  4. … ኪታባ ገመቹ የሚባል ስም ይዘህ ቀድሞዉኑስ ምን አባትክ ልትሠራ ነዉ እነርሱ ጋ የሄድከዉ? እነርሱ ቤት ሀቀኝነት የለም ካልን እነሆ ፩፻፶ ዓመት ሆነ። የሚያለቅስልህ ሰዉ የለም፤ አንተዉ እንደጀመርከዉ ተወጣዉ።

  5. ደመቀ ነውር አይደለም እንዴ ሃጎስ ነህ እንዴ? እንዴት ነው ኪታባ የሚል ስም ይዞ የዜግነት ፖለቲካ እናራምዳለን ካሉት ጋር ለሃገሩ መፍትሄ የማይፈልገው? ሲጀመር ብርሃኑን አምኖ አልነበረም ክብር ያላቸውን እነ አንዱ አለምአራጌን እነ የሽዋስን አምኖ ነው እነ ግርማ ሰይፉን አላልኩም፡፡ መከባበርም መልካም ነው እረ ሰው ተጨካከነ ከዚህ ብርሃኑ ስንል ከዚህ አረጋዊ ይነሳል እንሱን አስታገስን ስንል ጁዋር መሃመድ አህመዲን ጀበል ሽመልስ አብዲሳ ይከተላሉ እኛም እንደ ዘመነ መሳፍንት እሳት ማጥፋት ላይ ተጠመድን፡፡ ኢትዮጵያን ላጠፉበት ሌንጮዎች አረጋዊ በርሄ፤ ዲማ ነጋዎ፤ግደይ ዘራጽዮን ይጦሩበታል፡፡ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚለው ደግሞ አሃዳዊ የጥንት ስርአት ናፋቂ እየተባለ እንደ አውሬ ይታደናል፡፡ ይህ ጊዜ ያልፍ ይሆን?

  6. የሃገራችን ምርጥ ብሂል ለኦበሌሳ ሃብታሙ ኪታባ ይሰራል “ወደሽ ከተደፋሽ ምንአባሽ አገባሽ” ወገኖቼ የጠቀሱት ምርጡ የሃገራችን የፖለቲካ ሴረኛ ብርሃኑ ነጋ የሴራው አርኪቴክት አብዮት አህመድ ዋነኛ ተለጣፊ ሆኖ ያሻግረናል ሲል ውታፍ ነቃይ በነረበበት ወቅት ከውጭ የታዘብነው ያ ሁሉ መሰሪነትን ከውስጥ ሆነህ ስታስተናግድ ከርመህ ዛሬ ተወጋሁ ተጠቃሁ ማለት የራስ ህ ጉዳይ ነው እልሃለሁ ::የሚሻለው ይህን ጥሩ ስያሜ የያዘ የዜግነት ፓርቲያች ሁን የሁሉም የኢትዮጲያ ህዝቦች ያካተተ በማድረግ ከጭራቁ አብዪት አህመድ በመለየት ትግሉን በአዲስ መክል ጀምሩ:: ዳቦዬ ተወሰደ ብሎ በልማደኛ የስልጣን መንታፊዎች ከሚያቅለስ ነሆለል ልጅ ፈጣሪ አይስጠን:: እምቢ ብሎ በውስጥም በውጭም የሚፋለም ልጅ ያበርክትልን:: ያኡሌ ሰረሪቲ ነምኒ ባንዳ ነምኒ ሚቲ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share