ሲፈልግ አልደራደርም፣ ሲፈልግ እደራደራለሁ የሚል አወናባጅ/ዉሸታም መሪ – ግርማ ካሳ

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሕወሃት ጋር በአፍሪካ ኅብረት አመቻችነት የሚደራደርለትን ቡድን ማቋቋሙን የመንግሥት ዜና አውታሮች ማምሻውን ዘግበዋል። የተደራዳሪ ቡድኑ ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ሲሆን፣ በአባልነት ደሞ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ሰዎች እንደተካተቱ ተገልጧል።
1፤ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ፍትህ ሚንስትር)
2፤ ተመስገን ጥሩነህ (የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር)
3፤፤ ሀሰን አብዱልቃድር (አምባሳደር)
4፤ ሬድዋን ሁሴን (የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ)
5፤ ብርሃኑ በቀለ (ሌ/ጀኔራል)
6፤ ጌታቸው ጀምበር (የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር)
[ዋዜማ ራዲዮ]

የአፋኙ፣ የጨፍጫፊውና የግጭት ጠማቂው የኦህዴድ መሪ አብይ አህመድ፣ “ሕወሃት ለሕግ ሳይቀርብ፣ አናርፍም፣ ድርድር የለም ወዘተ” ሲል ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በሚስጥር ከሕወሃት ጋር መደራደር ብቻ ሳይሆን፣ ሲያደርግ የነበረውን ሚስጥራዊው ድርድርም በድርጅት ደረጃ ይፋ አድርጎታል፡፡

በሰሜን ያለውን ችግር በተመለከተ፣ በአንድ በኩል አብይ አህመድ መብራት፣ ኔትዎርክ፣ የባንክ አገልግሎት አቋርጦ ሕዝቡን ለመከራ ዳርጎታል፡፡ በሌላው በኩል ወያኔዎች በጥጋባቸው ምክንያት በሚያደርጓቸው ውጤት አልባ ጦርነቶች የውጭ የምግብ እርዳታ እንደሚገባው ወደ ህዝቡ መድረስ አልቻለም፡፡ በሕወሃትም በነ አብይ አህመድ የትግራይ ሕዝብ እየተሰቃየ ነው፡፡

ከዚህም የተነሳ ወያኔ በህዝቡ ዘንድም ተቃውሞ እየተነሳባት ናት፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁመት ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ትግራይ ውስጥ እየሆነባት ነው፡፡ ፋታ ማግኘት ትፈልጋለች፡፡ የወያኔ መሪዎች በአብይ አህመድ ላይ፣ ክዶናል በሚል፣ እጅግ በጣም ያመረረ የበቀል ስሜት ቢኖራቸውም፣ ለራሳቸው ሲሉ ለጊዜው ከአብይ አህመድ ጋር ከመስማማት ውጭ አማራጭ እንደሌላቸው ተረድተዋል፡፡

አብይ አህመድና ኦህዴዶችም ከህወሃት የበለጠ እንደ ጠላት የሚያዩት አማራውን ማሀብረሰብ ስለሆነ፣ በወለጋ የታየው ጭፍጨፋም በድጋሚ በጎላ መልኩ እንዳሳየው፣ ከሕወሃት ጋር መደራደር፣ እነርሱም ለጊዜው አስፈላጊ ሆኖ ስላገኙት እየተደራደሩ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ‹‹ከኮሎኔሉ ወደ ኮሎኔሉ!!!›› ብዕረኞች እልፍ ጠመንጃን የማረኩባት ሃገር !!!

ለኦህዴዶች በፊት ስጋት የነበረው ሕወሃትና የትግራይ ኃይሎች ነበሩ፡፡ የአማራ ኃይሎችን በመጠቀም፣ የነርሱ ጦር እያሸሹ፣ ብዙ የአማራ ወጣቶች መስዋትነት በመክፈላቸው፣ በህወሃት አንገታቸው ተንጠልጥሎ ከመያዝ ተረፉ፡፡ ህወሃትም ተዳከመች፡፡፡ አሁን የኃይል ሚዛኑን ሲያዩት፣ ከህወሃት ይልቅ፣ ትላንት ያዳኗቸው የአማራ ኃይሎች ስጋት ሆነው ታዩአቸው፡፡ ፊታቸውን ከሕወሃት አዙረው የአማራ ኃይሎች ላይ አነጣጠሩ፡፡፡ በአሁኑ ወቅት የፌዴራል የአብይ ጦር ውጊያ እያደረገ ያለው ከሕወሃት ጋር ሳይሆን በዋናነት በጎጃም ከፋኖዎች ጋር ነው፡፡

የህወሃትና የኦህዴዶች ለጊዜውም ቢሆን አብሮ መደነስ ፣ ለድርድር ደፍ ደፍ ማለት በዘላቂነት የሚያመጣው ሰላምም ሆነ መረጋጋት አይኖርም፡፡

አንደኛ ሁለቱም ስልጣን ስለሚፈልጉ በአንድ አገር ውስጥ መቀጠል አይችሉም፡፡ አንዱ ካልተሸነፈ በቀር፡፡

ሁለተኛ በተለይም የአማራ ማህበረሰብ የሌለበት ድርድር የሞተ ነው፡፡

ሶስተኛ የኤርትራ ጉዳዩ ነገሩን ያወሳሰበዋል፡፡ ያም የሆነበት ምክንያት በአማራው ኃይሎችና በኤርትራ መካከል እጅግ በጣም የጠነከረ መተሳሰር ስለተፈጠረ ነው፡፡ የአብኑ አመራር ዶር ደሳለኝ ጫኔ ኤርትራም የድርድሩ አካል መሆን አለባት ያለው ፣ መቼም ዝም ብሎ ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ ዶር ደሳለኝ ዘላቂናስ አስተማማኝ ሰላም የሚመጣው እንዴት እንደሆነ ስለገባው ነው፡፡

ድርድር አስፈላጊ ነው፡፡ በኔ እምነት የሰሜኑን ችግር መፍታት በጣም ቀላል ነው፡፡ ላሉ የልዩነቶች ሁሉንም አሸናፊ ያደረገ መፍትሄዎች ማቅረብ ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን

1ኛ መቀደም ያለበት ነገር አለ፡፡ የአብይ አገዛዝ በድርድር እስኪወሰን መጠበቅ የለበትም፣ አሁኑኑ የስልክና የመብራት አገልግሎቶች በትግራይና በወልቃይት መልቀቅ አለበት፡፡ የሴከንድ ጉዳይ ነው፡፡ አብይ አህመድ ልቀቁ ካለ ነገ የትግራይና የወልቃይት ሕዝብ የመብራትና የስልክ አገልግሎት ማግኘት ይችላል፡፡ የባንክ አገልግሎት አሁኑኑ ለማስጀመር አስቸጋሪ ቢሆንም፣ በዚያ ረገድም ስራዎች በአፋጣኝ መሰራት አለባቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕወሓት እና የኢትዮጵያዊነት ገጽታው

2ኛ በስሜን የተፈጠረው ቀውስ በትግራይና በአማራ፣ በትግራይና በአፋር ማህበረሰብ መካከል የተፈጠረ አይደለም፡፡ በኢህአዴግ ቁጥር አንድ (ህወሃት ) እና በኢሕአዴግ ቁጥር 2 (ብልጽግና) መካከል የተፈጠረ ችግር ነው፡፡ ስለሆነም እነዚህ ቡድኖች ለብቻቸው የሚፈቱት ነገር አይኖርም፡፡ በመሆኑም ድርድሩ አካታች መሆን አለበት፡፡ ከሕወሃት ውጭ ያሉ የትግራይ ኃይሎች፣ እነ አረና፣ ሲቪክ ማህበረሰባት፣ ከብልጽግና ውጭ ያሉ እንደ አብን ያሉ ደርጅቶችና የፋኖ መሪዎችን ያካተተ ድርድር መሆን አለበት፡፡

3ኛ ዘላቂ ስምምነት እንዲመጣ የአብይ አህመድ አገዛዝ በአራት ኪሎ፣ የደብረ ጽዮን አገዛዝ በመቀሌ መቀጠሉ እንቅፋት ስለሚሆን፣ አብይ አህመድም ደብረ ጽዪን ገለል መደረግ አለባቸው፡፡

2 Comments

  1. ” የአብይ አህመድ አገዛዝ በአራት ኪሎ፣ የደብረ ጽዮን አገዛዝ በመቀሌ መቀጠሉ እንቅፋት ስለሚሆን፣ አብይ አህመድም ደብረ ጽዪን ገለል መደረግ አለባቸው፡፡”

    Amen,

    Qale hiwot yasemallin!

  2. መቼም ደመቀ መኮንን አቅም የለውም ህወአትን ሲያይ ይበረግጋል እኔ የለሁበትም ለማለት ነው ደመቀ የሚሉት ሰው ዘር ማንዘሩ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖር ከዚህ ነገር መውጣት አለበት ከዚህ በፊት ነገር አበላሽቷል አሁንም እንዳያበላሽ አቅም የለውም ከሆነም እነ ዮሃንስ ቧያለው፤አቶ ገዱ፤ኮለኔል ደመቀ፤ሲሳይ መንግስቴን የመሳሰሉ ቢካተቱበት መልካም ነው ይህ ነገር መቋጫ ወደማይገኝለት ፍጅት ለማምራት ከሆነ አብይ ይቀጥልበት እዚህ ቦታ እሳት ነድዶ ኦሮምያ እሳቱን ከሩቁ ይሞቃል ማለት ዘበት ነው፡፡ ነገር ሲበላሽ ማናቸውም የሉም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share