የበረከት ስምዖን ገመና ሲጋለጥ! – ኮሉኔል አስፋው እጅጉ

  •  የድርጅቱ ትርፍና ንብረት በእንግሊዝ አገር በነ አቶ ታደሰ ካሳ ጥንቅሹና በረከት ስምኦን ወይም በእንግሊዞች አጠራር የኢትዮጵያ የንጉስ ቤተሰቦች ንብረት በሚባለው
  •  ገነት ፈንቴ(የበረከት ሚስት፣ የአሰፉ ፈንቴ እህት ወይም የታደሰ ጥንቅሹ ሚስት፣ የነጻነት አበራ የአክስት ልጅ)ና የገነት ፈንቴ ባል ፣ አቶ መሰረት ተስፉ(በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ማሰተርስ እያለው ከህግ ዉጭ ሌላ ማስተርስ እንዲማር በበረከት አስገዳጅነት ወደ እንግሊዝ አገር ንብረቱን እንዲያስተዳድር የተላከና በዚያው እንደከዳ ተደርጎ ተመቻችቶለት የቀረ) ይህንን ሃብት በማስተዳደር ይገኛሉ፡፡
ለመሆኑ የድርጅቱን ሃብት እንዴት ወደ እንግሊዝ አገር ወዳለው ድርጅቶቻቸው ያዞሩታል የሚለውን ከዚህ በታች በዝርዝር እናየዋለን፡፡
አለ የምንለው ጥረት ግን የለሌው ገመና ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡፡
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
1.ዳሸን ቢራ የማነው፤ዳሸን ቢራ ብዞቻችን የጥረት ይመስለናል ነገር ግን በነ አቶ ታደሰ ካሳ ጥንቅሹና በረከት ስምኦን ዱየት ለተባለ ለእንግሊዝ ድርጅት ተሽጧል።
56 ፐርሰንት ድረሻው በዚህ ድርጅት ስም ተመዝግቦ ሲገኝ፤ቀሪው ገንዘብ በብድር መልክ ለጥረት እንደተሰጠ ተደርጎ ዳሸን ሙሉ ለሙሉ ለዱየት ተላልፏል፡፡
* የሚገርመው መሸጡ ሳይሆን የተሸጠበት ገንዘብ በእንግሊዝ አገር በነካሳ ቤተሰብ ወደሚተዳደር ድርጅት አካውን ገብቶ ቀርቷል፡፡
2.አቶ በረከት ከ500 መኪና በላይ በድርጅቱ ይገኛል ብሎ በአደባባይ የዋሸን ጉድ በጥቁር አባይ ትራንስፖርት የሚተዳደሩ 37 መኪኖች ብቻ በስራ ላይ ያሉና 133 ከጥቅም ዉጭ የሆኑ ናቸው፡፡በከርቻ ላይም 13 መኪኖች ብቻ ናቸው ያሉት።
* እንግዲህ በድምሩ በ27 አመት ዉስጥ 50 መኪኖች ብቻ ነው ያሉት ሌላው መኪና በኪራይ እየገባ የሚሰራበት እንጅ የጥረት ንብረት አይደለም፡፡ታድያ አቶ በረከት 500 ያሉን አንድ ዜሮ መጨመር ችግር የለውም ብለው ይሆን?
3.በድርጅቱ የተቀጠረው ሰው በሙሉ ቤተሰብ ስለሆነ በደምወዝና ጥቅማጥቅም ምክንያት ወደራሳቸው አዙረውታል፡፡
> ለምሳሌ የቀን አበል በቀን 22,000 ሃያ ሁለት ሽህ ለአንድ ሰው ይሰጣል(ቀልድ ይመስላል አይደል?) በሁለት ፔሮል አንዱ እንደ ዉጭ አገር ዜጋ የነበረከት ቤተሰቦች በዶላር በፈረጅ አቆጣጠርና በኢትዮጵያ አቆጣጠር አንድ ሰራተኛ በወር ሁለት ግዜ ደምወዝ ይወስዳል፡፡
4.ደሴ ዉሃ ለማምረት ተብሎ ከደሴ ከተማ በ10 ኪ.ሜ በምትርቅ በደዶ በተባለች የገጠር ከተማ 9 ሚሊዮን የተገመተን ፋብሪካ 20 ሚሊዮን በማድረግ 11 ሚለሊዮኑ ወደነ በረከት አካውንት በእንግሊዝ አገር እንዲገባ ተደርጓል፡፡
5.ጁቨንቲስ የተባለ የእንግሊዝ ድርጅት አብሬ እሰራለሁ ብሎ እንዲመጣ በማድረግ ያለምንም መያዣና ምንም ስራ ሳይጀምር፤በኢትዮጵያም በንግድ ሳይመዘገብ 50 ሚሊዮን ዶላር ወይም 150 ቢልዮን ብር ወደነ ታደሰ አካውንት ከድርጅቱ ወጥቶ ገቢ ተደርጓል፡፡
6.በጌዳ ዲተርጀንት ተብሎ የሚጠራው ድርጅት የነታደሰ ቤተሰብ በጋራ እሰራለሁ ብሎ ያለምንም መያዣ 90 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎ ተሰጥቶት ኮሚሽኑን ወስዶ ቀሪውን ወደነ ታደሰ አካውንት ገቢ አድርጎታል፡፡
7.የትመን ጅብሰም የተባለ ድርጅት በተመሳሳይ የነታደሰ ቤተሰብ በጋራ እሰራለሁ ብሎ ያለምንም መያዣ 90 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎ ተሰጥቶት ኮሚሽኑን ወስዶ ቀሪውን ወደነ ታደሰ አካውንት ገቢ አድርጎታል፡፡
8.ባህርዳር ላይ ከዶክተር በቀለ የተገዛ መሬት ለዶክተር በቀለ ለልብ ሆስፒታል መገንቢያ እንዲሆነው በማለት በነጻ ከሰጡ በኋላ በ3ሚሊዮን የተገመተውን መሬት 40 ሚሊዮን እንዲገዛ በማድረግ ዶክተሩ ለራሱ የሚገባውን ወስዶ ቀሪውን ለነ በረከት ገቢ አድርጓል፡፡
ቦታውም በአማራ ለልብ ህመም ለሚሰቃዩ ሆስፒታል ይሰራበታል የተባለውን ቦታ ለመቸርቸሪያ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡
9. በደሴ ከተማ ሊገነባ የነበረውን የወሎ ተርሸሪ ሆስፒታል የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ታደሰ ጥንቅሹ ከኅዝብ የተዋጣውን ገንዘብ እንዲሁም ከጥረት ለሆስፒታሉ ማሰርያ ተብሎ ወጭ የሆነው ገንዘብ ወደ እንግሊዝ አገር አሸሽቶታል፡፡
10. የወረቀትና ፐልፕ ፋብሪካ ጭስ አባይ ላይ በጥረት ሊገነባ የነበረውን ጥረት ልስገነባ ነው ብሎ ገንዘብ ወጭ በማድረግ ወደ እንግሊዝ አገር በተመሳሳይ ሁኔታ አሸሽቶታል፡፡ ፋብሪካውም የዉሃ ሽታ ሆኗል፡፡ ለአማራ እንዴት ጠላቶቹ ፋብሪካ ይሰሩለታል ታድያ!?
* በጥቅሉ አለ የምንለው ግን የሌለው ጥረት ሁሉም ህንጻወች ማለትም የቃሊቲ መጋዘን፥ የባህርዳር ዋናው ቢሮ ያለበት ህንጻ፤በአዲስ አበባ ቦሌ ወሎ ሰፈር የሚገኘው ህንጻ፤የደብረብርሃን ህንጻ፤የጎንደር ማበጠርያ ፋብሪካ፤ያው ዳሸን ወደ እንግሊዞች ተላልፏል ሁሉም በንግድ ባንክ፤በህወሓት ባንክ(ወጋገን)፤በኦሮሞያ ባንክ በእዳ የተያዙ ናቸው፡፡
* እነዚህ አሉ የተባሉት ንብረቶች በረከት እንዳለው 20 ቢሊዮን ሳይሆን 5.1 ቢሊዮን ብቻ እንደሆኑና ይህም በእዳ ወይም ሊያብሊቲ እንጅ የጥረት አንድም አንጡራ ሃብት ወይንም ኦውነር ኢኩቲ(ካፒታል) የለውም፡፡
ለዚህ ነው በረከትና ታደሰ ወደ ትግራይ በመሄድ ከማፍያወ የህወሀተ ቡድን ጋር በመሆን አገሪቱን በወጥቅጥ ወስጥ የአስገቡት ።
ኮሉኔል አስፋው እጅጉ ነኝ ።
ኅዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም።
የበረከት_ስምዖን_ገመና_ሲጋለጥ!
ተጨማሪ ያንብቡ:  Qumneger Megazine # 148

1 Comment

  1. ኮለኔል አስፋው እናመሰግናለን ፍትህ ግን እዚያ ሀገር ከየት ይምጣ? ሲጀመር ላማራው እንደ አገኘሁ ተሻገር፣ተመስገን ጥሩነህ፣ደመቀ መኮነን አይነት ስንኩል ምስለኔዎች ያስቀምጡለታል ለነሱ ኮትና ክራባት ገዝተው ከሰጧቸው ስለ ህዝቡ ጉዳያቸው አይደለም ።በተደጋጋሚ እንደታየው ከጠላታቸው በላይ ጠላት የሆኑት እነዚህ አስተዳዳሪዎች ናቸው።
    አሁንም ህዝቡ ነጻነቱን ሊጠይቅ ይችላል ብለው ስለሰጉ ወረራው ላይ የፊታውራሪነት ሚና የተሰጣቸው አበባው ታደሰ፣ተመስገን ጥሩነህ፣ደመቀ መኮነን በትግሬው አብረሀም በላይ የበላይነት ነው። ይህ የመከራው ጅማሮ እንጅ መጨረሻው አይደለም እነ በረከትም ይለቀቃሉ አማራው እዳውን ሲገፈግፍ ይኖራል። ለአማራው መዳኛው ፋኖ ስለሆነ ፋኖን ካልሸፈነው ተዋራጅነቱ ይቀጥላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share