June 21, 2022
10 mins read

የጭራቅ አሕመድ የሰቆቃ ዘመን ለምን ረዘመ? – መስፍን አረጋ

289285121 10227470904989036 6954061164950453653 nጭራቅ አሕመድ ስልጣን በያዘ ባንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በአማራ ሕዝብ ላይ የፈጸማቸው ወንጀሎች የሞት ፍርድ ቢቀርለት እንኳን ዓለም በቃኝ ሊያስወረውሩት ከበቂ በላይ ነበሩ፡፡  በተቃራኒው ግን ጭራቅ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ወንጀል ይበልጥና ይበልጥ እያከበደ፣ በአማራ ሕዝብ ላይ ይበልጥና ይበልጥ ጭራቅ እየሆነ አምስት ዓመታት ለመድፈን ተቃረበ፡፡  ስለዚህም ዋናውና አንገጋቢው ጥያቄ የጭራቅ አሕመድ የሰቆቃ ዘመን ከስድስት ወራት በላይ ለምን ረዘመ የሚለው ነው፡፡

ኢትዮጵያዊነትን ለማታለያነት እየሰበከ የመጣውን ጭራቅ አሕመድን ሆ ብሎ ቤተመንግስት ያስገባው የኦሮሞ ወይም የትግሬ ሕዝብ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያዊነቱን ከአማራነቱ በላይ የሚያስቀድመው የአማራ ሕዝብ ነው፡፡  ስለዚህም ጭራቅ አሕመድን ከቤተመንግስት ሆ ብሎ የሚያስወጣው የኦሮሞ ወይም የትግሬ ሕዝብ ሳይሆን የአማራ ሕዝብ ነው፡፡  በመሆኑም  የጭራቅ አሕመድ የሰቆቃ ዘመን ለምን ረዘመ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የአማራን ሕዝብ ስነልቦና መረዳት ያስፈልጋል፡፡

የአማራን ሕዝብ ከቀሩት ኢትዮጵውያን ጋር በተለይም ደግሞ ከአሮሞና ከትግሬ ጋር የሚለየው አንድ ትልቅ ቁምነገር አለ፡፡  ይሄውም፣ አማራ ቅድሚያ የሚሰጠው ላመራር እንጅ ለዘር አለመሆኑ ነው፡፡  ኦሮሞ በኦሮሞነቱ ዙርያ ሊሰባሰብ ይችላል፡፡  ትግሬም በትግሬነቱ ዙርያ ሊሰባሰብ ይችላል፡፡  አማራ ግን በአማራነቱ ዙርያ ለመሰባሰብ እጅግ በጣም ይከብደዋል፣ ምንም እንኳን ሳይወድ በግዱ እንዲሰባሰብ እየተደረገ ቢሆንም፡፡

የአማራ ሕዝብ የረጅም ዘመን መመርያ ተመልከት ዓላማህን ተከተል አለቃህን ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ያንድን ግለሰብ አመራር እስከወደደው ድረስ የግለሰቡ ዘር ዴንታ አይሰጠውም፡፡  የአማራ ሕዝብ ተዋረዳዊ አደረጃጀት የተዋኸደው ሕዝብ በመሆኑ ምክኒያት፣  መሪ በአማራ ሕዝብ ዘንድ ያለው ቦታ፣ በኦሮሞ ወይም በትግሬ ሕዝብ ዘንድ ካለው ቦታ እጅግ የበለጠ ብቻ ሳይሆን ወሳኝ ነው፡፡  ከኦሮሞና ከትግሬ ሕዝብ በተለየ ሁኔታ የአማራ ሕዝብ የሚነሳውም የሚወድቀውም በመሪ ነው፡፡

በዚህ ረገድ የአማራ ሕዝብ በንብ ሊመሰል ይችላል፡፡  እያንዳንዷ ንብ ብርቱ ተናዳፊ ብትሆንም፣ ንብን ንብ የሚያደርጋት አውራዋ ነው፡፡  በተመሳሳይ መንገድ እያንዳንዱ አማራም ብርቱ ነፍጠኛ ቢሆንም፣ አማራን አማራ የሚያደርገው መሪው ነው፡፡  የኦሮሞንና የትግሬን ሕዝብ በግብታዊነት ሆ ብሎ እንዲነሳ ማድረግ እንደሚቻለው፣ የአማራን ሕዝብ በግብታዊነት ሆ ብሎ እንዲነሳ ማድረግ አይቻልም ባይባልም በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ሆ ብሎ በመነሳት ጭራቅ አሕመድን ከጫንቃው ላይ አውርዶ አሽቀንጥሮ እንዲጥለው ለማድረግ ሆ ብሎ የሚያስነሳው መሪ የግድ ያስፈልገዋል፡፡

ጭራቅ አሕመድ እስከመጣበት ጊዜ ድረስ፣ የአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያን እወዳለሁ ወይም ኢትዮጵያ ሱሴ ናት የሚልን ሁሉ በንግግሩ ብቻ የሚወድ የዋህ ሕዝብ ነበር፡፡  ጭራቅ አሕመድ ግን የአማራ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ያለውን ስስ ልብ፣ አማራን ለማታለያነት ተጠቀመበት፡፡  በዚህም የአማራ ሕዝብ ለኢትዮጵያዊነት የነበረውን የዋህነት ድምጥማጡን አጠፋው፡፡  በንግግር ብቻ ተደልሎ አደባባዮችን ያጨናንቅ የነበረው የአማራ ሕዝብ በተግባር ካላሳያችሁኝ ብሎ በየቤቱ አደፈጠ፡፡  ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያየ እያሉ በመስበክና በመዝፈን ብቻ የአማራን ሕዘብ በነቂስ ማስነሳት ከጭራቅ አሕመድ በኋላ አከተመ፡፡

አምላኩን የኢትዮጵያ አምላክ የሚለው፣ ኢትዮጵያዊነት ሐይማኖቱ የሆነው የአማራ ሕዝብ፣ ጭራቅ አሕመድን በመሳሰሉ፣ አማራን ለማታለል ሲሉ ብቻ ኢትዮጵያዊነትን በሚሰብኩ አያሌ ሐሳዊ ሰባኪወች ላያሌ ግዜ ተክዷል፡፡  ስለዚህም ካሁን በኋላ ለኢትዮጵያ (ስለሆነም ለአማራ) ቁሚያለሁ የሚልን ማናቸውንም ግለሰብ ወይም ቡድን የአማራ ሕዝብ የሚያምነው እውነትም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት መቆሙን በተግባር ካረጋገጠ ብቻ ነው፡፡

ለአማራ ሕዝብ በመቆም ለኢትዮጵያዊነት መቆምን በተግባር ማረጋገጥ የሚቻለው ደግሞ የአማራን ሕዝብ በሚጨፈጭፉትና በሚያስጨፈጭፉት የጭራቅ አሕመድ ኦነጎችና ብአዴኖች ላይ  በተለይም ደግሞ በቀንደኛወቹ ላይ ርምጃ በመውሰድና ለርምጃው ሃላፊነትን በይፋ በመውሰድ ነው፡፡  ይህን የሚያደርግን መሪ ወይም ቡድን የአማራ ሕዝብ በነቂስ እንደሚከተለው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡  የአማራን ሕዝብ ሆ ብሎ እንዲነሳ በማድረግ የጭራቅ አሕመድን የሰቆቃ ዘመን ማሳጠር የሚቻለው በዚህና በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡

መስፍን አረጋ

[email protected]

287540960 2142912072535037 2820595780965891535 n

23m 
288254446 2953709348107611 865240875631964894 nቴዲ አፍሮ ይህን ብሏል። ትችላለህ ንጉሱ!!!
“ዘውግ ያወረው ድንበር:- መሃላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በዕልፍ አዕላፍ ሬሳ።”
አዎ አብይ አሕመድ እናቶች ይጸልዩልኛል ብሎ ነበር። ምሃላውን እረስቶ እናቶችን ያሳረደ መሪ።
ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከደቂቃዎች በፊት የለቀቀውን ‘ናዕት’ የተሰኘውን ሃገራዊ ዜማ
“መታሰቢያነቱ ላለፉት አራት አመታት በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች አላግባብ በግፍ ለተገደሉ ፣ አካላቸው ለጎደለ እና ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ንፁሃን ዜጎች በሙሉ ይሁን”ሲል ገልፆል
????????❤️????
Teddy Afro
እያመመው መጣ ቁጥር ሁለት /ቴዲ አፍሮ/
ዶፍ ዶፍ…
ግርም እያለ ጊዜ ሆነ ሰዓቱ
በዳንኪራው ደምቆ በምቱ
ለደቂቃም አይቆይ በስልቱ
ቦግ እልም እያለ መብራቱ
ኡኡ ሬጌ ናዕት
ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ
ማን ሊታደም ከድግሱ
ብልጭልጭ ቢሆን ድንኳን
አይለውጥ ጎግ የእውነት መልኳን
ቢጋርድ ሀሳብ አርጎ ሜዳን ገደል
እም አእላፍ ስቃይ ጭንቀት ቢደረደር
የነፍስ ሕላዊ መሻት ዋዌ ሳይገባቸው
ስንቶች በዘር ተዘፍቀው ታዘብናቸው
ዘውግ ያወረው ድንበር መኃላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አዕላፍ እሬሳ
እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ
ና ታደም ይለኛል ደሞ በነ ኡኡ ሬጌ
ኡኡ…ሬጌ ናዕት…
ኡኡ ሬጌ ናዕት
ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ
ማን ሊታደም ከድግሱ…?

 

288260848 409921887817787 7803507190733768857 n

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop