ኢትዮጵያዊነት እንዲደበዝዝና ለጥቃት እንዲጋለጥ አማራ ላይ ያነጣጠረ ወከባ፣ መፈናቀል፣ ግድያና ፖሊሲ ተቀርፆ ህገ መንግስታዊ ስርዓት ቆሞ ራስን አለመከላከል ህግ ተሰርቶ የጉስቁልና ምሳሌ የሆነ ማንነት እንዲሆን እየተሰራበት ያለ ህዝብ መሆኑን ደግመን ደጋግመን ሞግተናል፤ አስረድተናል፤ አሁንም እየታገልን እንገኛለን።
በመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች ህዝባችን ላይ የተከፈተውን ስርዓታዊ ጥቃት ከማሻሻልና ከተበዳዩ ህዝባችን ጎን ከመቆም ይልቅ ተጨማሪ ያልተነገሩ ትርክቶችን ወደ ፖለቲካ አውድ በማስገባት ንፁሃን ላይ አሁንና ባለፈው ሲደረሰበት የቆየው ሁለንተናዊ ጥቃት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥብቅና ሲቆም ተመልክተናል።
የአሁኑ ባያሰደነብረንም የወደፊቱን ማሰብ አያስፈልግም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ፤ በተለይም አማራ ላይ ያነጣጠረው ሁለንተናዊ ጥቃት የሚታረመው በልምናና በልምምጥ ሳይሆን በመራር ትግልና መስዕዋትነት የዕኩሎች ሀገር ማድረግ የሚያስችል ዕውነተኛ ስርዓታዊ ለውጥ ማምጣት ሲቻል ነው።
NB፦ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ። የንፁሃን ነብስ ከደጋግ አባቶቻችን ጋር ትረፍ።
“አሁንም እናገራለሁ ….
የአንድ ሰው ነፍስ ዋጋ ከአትክልቶችና ከቅጠላ ቅጠሎች በላይ ዋጋ አለው።
የአንድ ሰው ነፍስ ከፓርኮችና ከመናፈሻዎች በላይ ትርጉም አለው።
የአንድ ሰው ነፍስ ከብስክሌትም በለው ከአስፋልት መንገዶች በላይ ዋጋ አለው።
የአንድ ሰው ነፍስ በየትኛውም ሪፎርሜሽን አይተካም።
የአንድ ሰው ነፍስ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ዳግም ወደ ህይወት አይመለስም።
የአንድ ሰው ነፍስ በአጉል ዲስኩር ዳግም ነፍስ አይዘራም!
በቃን!!!”
~ @Firdyawkal Nigussie