አግኝተህ ያልኮራህ ጥቅም ያልቀየረህ፣
ለአገርህ ለህዝብህ ንፁህ ፍቅር ያለህ፣
አንተነህ ጀግናችን ፅኑ አላማ ያለህ።
ከፓርላማው መሀል ጎልተህ የምትወጣ፣
ጥያቄህ እውነታ አንጀት የሚያጠጣ፣
ብዙ አመት ኑርልን እኛ አንተን አንጣ።
አንተ የጎጃም ነህ አንተ የወሎ ነህ፣
አንተ የጎንደር ነህ አንተ የሽዋ ነህ፣
አንተ የዋግህምራ አንተ የአዊ ልጅ ነህ፣
ኢትዮጵያዊ ፍቅር አማራ ደም ያለህ።
ከፓርላማው አባል ከተሰበሰበው፣
ከሁሉም አባላት ጎልቶ የሚታው፣
ክርስቲያን ታደለ የእኛ ጀግና እሱ ነው፣
የአገር ፍቅር ያለው አማራ ያፈራው።
ፓርላማው ናፈቀኝ አንተ ያለህበት፣
የአገሪቱን ችግር የጠቃቀስክበት፣
እውነትን መድረክ ላይ የተናገርክበት።
እንቅፋት አይምታህ እሾህ አይውጋህ፣
የአማራ ህዝብ ወኪል ባለአደራ ነህ፣
ህዝብህን አክባሪ ሞትን ያልፈራህ።
መኩራት ካስፈለገ የእሱ እናቱ ትኩራ፣
ወልዳለች ጎበዝ ልጅ አገር የሚያስጠራ።
አብሬህ አልበላሁ በአካል አላውቅህ፣
በጣም ደስ ይለኛል መድረክ ላይ ሳይህ፣
ክርስቲያን ተብለህ ሲጠራ ስምህ።
ስብሰባ ተጠርተው ጥያቄ እንዲያነሱ፣
ጥያቄ እንዲጠይቅ እድል ደርሶት ለእሱ፣
ጣት ተቀሰረበት መልሱን ሲመልሱ፣
ወደ ኋላ ላይል ላይፈራቸው እሱ።
ሀሳብና ተረችት የሁሉም ሰው አለው፣
እሱን የማደንቀው አቀራረቡን ነው።
ለህዝብህ መከታ ለጠላት አስፈሪ፣
ፍርሀት የማታውቅ ደፍሮ ተናጋሪ፣
የአገር ፍቅር ያለህ ታሪክን መርማሪ፣
አንተነህ ያለኸን ለህዝብ ተቆርቋሪ።
አጭበርባሪዎቹ ሌባዎች ፈሩህ፣
ክርስቲያን ተብሎ ቢጣራ ስምህ።
–