“ስልጣን መጋራት ብቸኛው አማራጭ ነው ብሎ ከሚያስብ አጎብዳጅ ፓርቲ ጋር አባል ሆኜ መቀጠል አልፈልግም” – ክቡር ገና

ኢዜማ እንደ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ ለህዝብ የገባውን ቃል እና የተቋቋመበትን ዋነኛ አላማ እና ግብከማሳካት ይልቅ፣ ከገዢው ፓርቲ ጋር በመለጠፍ መስመሩን መሳቱ እጅግ የሚያሳስበኝ ጉዳይ ነው።
በመሆኑም ከዚህ በሗላ ስልጣን መጋራት ብቸኛው አማራጭ ነው ብሎ የሚያስብና ለመታረመም ለመቃናትም ዝግጁ ያልሆነ አጎብዳጅ ፓርቲ ጋር አባል ሆኜ መቀጠል አልፈልግም።
እምነት ጥዬ የገባሁበት ፓርቲ አላማውን ስቶ ወደ ገባበት የቁልቁለት ጉዞ አብሬ ለመግባትና የታሪክ ተወቃሽ ለመሆን ህሌናዬ አይፈቅድልኝም። በመሆኑም ከኢዜማ አባልነቴ በፈቃዴ ለቅቂያለሁ።
(ክቡር ገና – የኢዜማ ከፍተኛ አመራርና ለአዲስ አበባ ከንቲባነት የተወዳደረ ከመልቀቂያ ደብዳቤው ላይ የተወሰደ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  "አሸባሪው ህወሓት ለኢትዮጵያ ደህንነት አደጋ በማይሆን ደረጃ እስኪደርስ ይመታል" -ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም

3 Comments

  1. ስለነ ብርሃኑ ነጋ ተጨማሪ ምስጢሮች፤
    እነ ብርሃኑ ነጋ ህብረትን አፍርሰዉ ቅንጅትን መስርተዉ ወደ97ቱ የዉሸት ምርጫ ዉስጥ የተሳተፉት በገንዘብ ስለተገዙ ነዉ የሚባል ምስጢር አለ፤ ብርሃኑ 50 ሚሊዮን፤ ሃይሉ ሻወል 70 ሚሊዮን በብድር መልክ እንደተቀበሉ ይሰማል። ብርሃኑ ሆቴሎቹን ሲያስፋፋ ሀይሉ ደግሞ በልጁ ስም የምህንድስና ኩባኒያ እኢነደከፈተ ይነገራል። ታዲያ አሁን ችግር ቢፈጥሩ ብድሩን መልሱ ስለሚባሉ ሊሆን ይችላል መንግሥትን በጭፍን የሚደግፉት።

  2. ብሪም ሃብታም ነው ይባላል አልጠገብ ብሎ እጁን ሌላ ነገር ውስጥ ካልከተተ ኢንጂነር ሃይሉ ሻዉል ግን ስርቆት አለአግባብ የህዝብ ንብረት መዝረፍ ስብእናቸው አይደለም እራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት አትወቀሳቸው ሰውየው የጠገቡ ጌታ ከስው የማይፈልጉ መሆናቸውን በ ቪኦኤ ከሰለሞን ክፍሌ ጋር ያደረጉትን ቃለ መልልስ ማዳማጥም ይጠቅማል።

  3. ክቡር ወክቡር ገና
    ስምን መልአክ ያወጣዋል በትትክል ጋሼ ክቡር ላንተ ያለማጋንን ይሰራል ::ገና ከጥንት ሃገር ቤት በቢዝነስ ሙያ ሳለሁ ጀምሮ የማደንቅህ የሃገራችን የእርስ በርስ እልቂት እንዳይከሰት ለባላንጦች የላክህውን መልክት ሳነብ ለማውቃቸው ሳካፍል በጣም አከበርኩህ ::ዛሬ ደግሞ ወቅታዊ ተገቢ መለየት ስታደርግ ልድገመው:: ሳገኝህ ጋሼ ሃይማኖት አለሙ ክቡር ዶ/ር ሃዲስ አለማየሁን ጉልበት እንደሳመው ላደርገው ዘንድ ፈጣሪ ይርዳኝ::

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share