ለማመን የሚከብዱ – ዓባይነህ ካሤ

June 15, 2022
abiyጠሚሩ ሪፎርሙ ለማመን የሚከብዱ ውጤቶች እያመጣ ነው። ለእናንተ አይደለም ለእኔ ለራሴ ሲሉ ፓርላማ ላይ ተናግረዋል።
ከዚሀ በፊት የደነገጡት ሰውዬ ዛሬ ደግሞ ለማመን ከበዳቸው። መፍትሔ አለው ቅዠት ላይ ስለኾኑ ጠበል መረጨት።
ለማመን የሚከብዱ እነዚህስ?
፩. ለማመን የሚከብድ የጋዜጠኞች፣ አንቂዎች እና ሕፃናት እስራት
፪. ለማመን የሚከብድ የሀገር ውስጥ መፈናቀል
፫. ለማመን የሚከብድ ረሀብ
፬. ለማመን የሚከብድ የኑሮ ውድነት
፭. ለማመን የሚከብድ የዘር ፍጅት
፮. ለማመን የሚከብድ መንግሥታዊ ውሸት
፯. ለማመን የሚከብድ ተረኝነት
፰. ለማመን የሚከብድ የዋጋ ግሸበት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት
፱. ለማመን የሚከብድ አጋች ታጋች ኩነት
፲. ለማመን የሚከብድ ጽንፈኝነት . . .

2 Comments

  1. ውድ ወንድሜ የግሪክ ፈላስፎች የሚሉት አንድ ቁም ነገር አለ። ጭንቅላት ካላየ ዐይንም ማየት አይችልም ይላሉ። ዛሬ በአገራችን ምድር ስልጣን ላይ ቁጥጥ ያሉት ሰዎች ለምን ስልጣን ላይ እንደተቀመጡ የማይገነዘቡ ስለሆነ በምድር ላይ ያለውና በዐይን የሚታየው ነገር ሁሉ ለእነሱ የሚታያቸው አይደለም። አቢይና ግብረአበሮቹ የልጣንን ማማ ከያዙ ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ እፎይ ብሎ አያውቅም። መፈናቀል፣ መጤ እየተባለ መባረር፣ የገነባው ከተማዎችና መንደሮች መፈራረስ፣ ጦርነት በየቦታው እየተካሄደ ዝም ብሎ ማየት ወይም ተጠያቂዎችን እየያዙ አለመቅጣትና ሌሎችም አያሌ ለጭንቅላት የሚዘገንኑ ነገሮች በሙሉ እጣው ሆነዋል። ገበሬው እፎይ ብሎ እንዳያርስ በማሳው ላይ ሸነግ ኦኔ የሚባል ቡድን ነገር ግን ደግሞ በመንግስት የሚታጠቅና የሚደገፍ ጦርነት በማካሄድ ስራ እንዲተጓጎል ለማድረግ ችሏል። ከብቶች ይገደላሉ፣ ሰብልም ይዘረፋል። ኦሮሚያ በሚባለው አርቲፊሻል ክልል ውስጥ የሰፈሩ ስንትና ስንት ትውልድን ያስቆጠሩ የአገሪቱ ዜጋዎች አማራዎች ናችሁ በመባል ይገደላሉ፣ አሊያም ይፈናቀላሉ። በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ እንዴት አድርጎ ምርትን ማሳደግና ሰፊውን ህዝብ መመገብ ይቻቻል። ለዛሬው በአገራችን ምድር ለሚታየው የዋጋ መናር አንደኛው ምክንያት ከህዝብ ቁጥር ጋር የሚስተካከል የምርት ዕድገት አለመኖር ሳይሆን፣ ከዚህም ባሻገር አገዛዙ ከድሮው የወያኔ የኢኮኖሚ ፖሊሲ አለመላቀቁና በየጊዜውም የኢትዮጵያ ብር ከዶላር ጋር ሲወዳደር ዝቅ እንዲል በመደረጉ ነው። የአቢይ አገዛዝ የሚከተለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምን እንደሆነ የገባው አይደለም። እኛ የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ብለን የምንጠራውና ጥቂቱን የሚያበለጽግ ሰፊውን ህዝብ ደግሞ ወደ ድህነት የሚገፋ ነው። በአጭሩ አቢይ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ ከወያኔ የአይ ኤምፍና የዓለም ባንክ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በፍጹም አልተላቀቀም። ይህ ዐይነቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው ለዋጋ ግሽበት ዋናው ምክንያት የሆነው።
    በከተማዎች ውስጥ ደግም፣ በተለይም በአዲስ አበባ ውስጥ ከገጠር የመጡ ቄሮዎች በሌብነትና በማጅራት መችነት በመሰማራት በህዝብ ዘንድ ፍርሃት እንዲነግስ ለማድረግ ችለዋል። በየመስሪያቤት ውስጥ ደግሞ የተሰገሰጉት ምንም ዕውቀትና ችሎታ የሌላቸው ቄርዎች በመሆናቸው ስራን በስርዓት መስራትና ህዝቡ የሚፈልገውን ግልጋሎት መስጠት በፍጹ አይቻልም። ታዲይ በእንደዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ እንዴት ጤናማ ነገር መስራት ይቻላል፤ አገርንም በሁሉም አቅጣጫ እንዴት መገንባት ይቻላል። በህብረተሰብ ግንባታ ታሪክ ውስጥ ለአግር ግንባታ ዋናው መሰረት በአንድ አገር ውስጥ የተሟላ ሰላም ማስፈን ነው። ህዝቡ እርግጠኛ እንዲሆን ማድረግ ነው። የአንድ መንግስትና አገዛዝም ኃላፊነትና ግዴታ ስላምን ማስፈን ነው። አቢይና ግብረ-አበሮቹ ግን ይህንን ማድረግ በፍጹም የቻሉ አይደሉም። በከፍተኛ ደረጃ በመሳሪያ በመታጠቅና ተቃዋሚ ነኝ የሚለውን በማፈን አገር ማስተዳደር የሚችሉ መስሏቸዋል። ህዝብን እያስፈራሩና ጦርነትን እንዲለምደው በማድረግ ጤናማ ስራ እንዳይሰራ እያደረጉ ነው።

    ፈቃዱ በቀለ

  2. ወንድማችን በፍቃዱ በቀለ እንደእናንተ አይነት የአንድነት ሃይሎች የምትጽፉትን በፍልስፍና እና በኢኮኖሚክስ እውቀት የነጠር ጽሁፍ ከብዶትም ይሆን እምነት በማጣት ጊዜ ወስዶ ሊያየው አይወድም። አካባቢው የተሰበስቡት ደናቁርት ዘመንና አሻግሮ የሚያይ ተፈጥሮ የላቸውም። አካባቢውን አጥረው የያዙት አባዱላ ገመዳ፤ወርቅነህ ገበየሁ፤ታየ ደንዳ፤ታከለ ኡማ፤ሽመልስ አብዲሳ፤ዲማ ነገዎ፤ሌንጮ ለታና ባቲ፤ ከጥንቆላ ተቀራራቢነት ያላቸው ጴንጤዎች፤አባ ገዳዎች ክብር የሌላቸው ተገለባባጭ ፖለቲከኞች (አረጋዊ በርሄ፤ብርሃኑ ነጋ፤አንዳርጋቸው ጽጌን የመሳሰሉት ናቸው። እኔ ያለሁበት አገር የአብይን ጠላቶች አጥፋለት እያሉ ሲጸልዩ ሰምቻለሁ ጠላቶቹ የሚሏቸው ተቃዋሚ የፖሊቲካ ፓርቲዎችን ነው። እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ሰው ቢገደል ቢፈናቀል የተማሪዎች ውጤት ቢደመሰስ ምን ይገርማል? ኢኒጅነር ስለሺን አንስቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን የአባይ ተደራዳሪ ማለት ምን የሚሉት ነው? ስለ ሃይለማርያም የተደራዳሪነት አቅም አንተ አገር የሚኖር መሰለኝ ቲም ሰባስቲያን ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ተመልከተው ኢትዮጵያ በእሱና በትግሬዎች ዘመን አለመፍረሷም ተአምር ነው።
    ነገር ተበላሽቷል በጸሎት መበርታት ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

abiy diskur
Previous Story

ምዕራብ ጎጃም ጸጉራሙ ውሻ (ይሁኔ አየለ)

288355688 3735167846709687 873404198634158269 n
Next Story

“አንተነህ” – ብዙአየሁ ደስታ

Go toTop