የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራዩ ሕወሃት በታንዛኒያ አሩሻ ከተማ ድርድር ሊጀምሩ እንደሚችሉ ከምንጮች መስማቱን ጠቅሶ የፈረንሳዩ ሊ ሞንድ ጋዜጣ ዘግቧል

ጋዜጣው የአፍሪካ እና ምዕራባዊያን አገራት ዲፕሎማቶች የሁለቱ ወገኖች ድርድሩን ከሰኔ ወር ማለቂያ በፊት ሊጀምሩ እንደሚችሉ ነግረውኛል ብሏል። ምዕራባዊያን ዲፕሎማቶች ሕወሃት የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች በሚቆጣጠሩት ወልቃይት ግዛት ላይ ያለውን የይገባኛል ጥያቄ ቀስ በቀስ እየተወው እንደሆነ ጥቆማ መስጠታቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጧል። ከመጋረጃው ጀርባ በሚደረገው ድርድር ከሁለቱ ወገኖች ከእያንዳንዳቸው አምስት አባላት ያሏቸው ተደራዳሪዎች ሊሳተፉበት እንደሚችሉም ዘገባው ጠቅሷል።

[ዋዜማ ራዲዮ]

https://zehabesha.com/in-ethiopia-negotiations-are-organized-behind-the-scenes-between-the-government-and-the-rebels-of-tigray/

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወላሂ ኢትዮጵያን ከልቤ እወዳታለሁ - የአፋሯ ልዩ ኃይል ሐዋ መሀመድ

2 Comments

  1. ይገርማል የትግሬዎችን ጉልበት ለመሳም ጂነራል ተፈራን፤ተመስገን ደሳለኝ፤መስከረም አበራን ማሰር ድረሱልኝ ያላቸውን ፋኖዎች መግደል ማሳደድ ለምን አስፈለገ፡፡ ይህ ጠ/ሚኒስተር ካሁን በኋላ የኢትዮጵያን መከላከያ ሃይል ማዘዝ ይችላል ወይ? በላካቸው ቦታ አሳርዷቸው ዛሬ ምንም እንዳልሆን ልደራደር ነው ይለናል፡፡ የከበቡት ከእሱ የማይሻሉ ከልምድና ወኔ ይልቅ በአስማት ኑሮውን ያደረገ ሰው ነው፡፡ ትንሽ እፍረት የለውም ስብሃት ነጋን ፈትቶ አቶ ታዲዮስ ታንቱን ሲያስር? ካሁን በኋላስ ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀለኛ ይታሰራል ወይ?

  2. እነ ዲና ሙፍቴ ምን ይሉ ይሆን? ይሄን ሰውዩ አምነው ድርድር የለም ብለው የተናገሩትን እንዴት ይዋጡት?ትግሬ አማራን በልቶ ኦሮሞን ሲተወው ይታያል ያውቀዋል ከዚህ በፊት ቆዳውን እንደገፈፈው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share