June 10, 2022
2 mins read

ብርጋዴየር ጀኔራል ተፋራ ማሞ ተፈቱ – DW

Tefera Mano
Tefera Mano
የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጋዴየር ጀኔራል ተፋራ ማሞ ማምሻውን ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸውና ባለቤታቸው ለዶቼቬለ አረጋገጡ፡፡ ብርጋድየር ጀነራል ተፈራ ከእስር የተፈቱት ዛሬ ያስቻለው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ30ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ነው፡፡
በሽብር ተጠርጥረው ጉዳያቸው በባሕር ዳር አማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲታይ በቆየው ክርክር ላይ አቃቤ ህግ ትናንት ግለሰቡ በሽብርና በሌሎች ተደራራቢ ወንጀሎች ስለተጠረጠሩ፣ የፍርድ ውሳኔው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ብለው ስለሚያስቡና ሊሰወሩ ወይም ሊጠፉ ስለሚችሉ ግለሰቡ በዋስ ከእስር እንዳይፈቱ በሚል ተሟግቷል፡፡
የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የማያስከለክል በመሆኑ ደንበኛቸው የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ተከራክረው ነበር፡፡
ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ የተሰየመው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር ተመልክቶ የተጠረጠሩበት ጉዳይ ዋስትና የማያስከለክል ነው በማለት ዋስትናውን ፈቅዷል፡፡
የጀኔራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ወ/ሮ መነን ኃይሌና የተጠርጣሪ ጠበቃ ሸጋው አለበል ጀኔራሉ ከሰዓታት በፊት ከባህር ዳር ማረሚያ ቤት መለቀቃቸውን ለዶይቼ ቬሌ አረጋግጠዋል ሲል አለምነው መኮንን ከባህርዳር ዘግቧል።

2 Comments

  1. ቀድሞውንስ ለምን ታሰሩ? ስንት በደም የታጠበ ወንጀለኛ ባለበት አገር ጥይት በሰውነታቸው ተሸክመው ስላዋጉ ነው? እረ እግዚሃሩን አትናቁት ሃጫሉ ሁንዴሳ፤መለሰ ዘራዊ፤ተስፋዬ ገ/እባብ፤ሳእረ መኮንን፤ስዩም መስፍን እንዲህ በፋክስ ይጠራሉ ብሎ ማን ጠረጠር ስብሃትስ ቢሆን እንደዛ እንዳልነበረ ሁኖ ተይዞ ህዝብ ፊት ይቀርባል?

  2. የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለፍትህ በመቆማቸሁ ከልብ እናመሰግናለን። የክልሉ የበላይ አመራርሞ ከእናንተ ቢማር የአማራን ህዝብ ከዉርደት’ና ከተረኞች ጭፍጨፋ መታደግ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

285464570 324010946589034 2391009015732328825 n
Previous Story

ዋልያዎቹ ወደ ሀገር ቤት እየተመለሱ ነው

287492058 5134694863278458 4473688511808071666 n
Next Story

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራዩ ሕወሃት በታንዛኒያ አሩሻ ከተማ ድርድር ሊጀምሩ እንደሚችሉ ከምንጮች መስማቱን ጠቅሶ የፈረንሳዩ ሊ ሞንድ ጋዜጣ ዘግቧል

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop