ቋንቋችንን ማጎልመስ ውጤቱ በሁሉም ዘርፍ የላቀ ነው – ባንትይሁን ትዕዛዙ

የአንድ አገር የግል ቋንቋው እንደ ገንዘብ ሁሉ ከጥገኝነት የሚያድን፤ በሌሎች ቁጥጥር ስር ከመኖር የሚረዳ፤ የህልውናው መሰረት ነው። ገንዘብን/ዶላሩን ምንዛሬውን በመቀያየር ጥገኞችን እንደሚአሰቃዩ ሁሉ በቋንቋውም ዜጎቻቸውን የበላይነትና ቀዳሚ ዕድል እንዲኖራቸው በማድረግ ሁሌ ዝቅተኛ ህይወትን መምረጥ እንደሆነ በመጀምሪያ ይሰመርበት።

በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ (1)እዚህ ያደረሱንን መሰረታዊ ምክነያቶች ማየት፤ (2)የኢኮኖሚ ሚዛኑን መመርመር፤ (3)የቴክኖሎጂ እድሎችን ማስላት፤ (4)የአገርን ህዝብ ዋና ተግዳሮቶችና በሚቀጥሉት 10ት ዓመታት እምርታ እድገት ላይ በመሳተፍ የት መድረስ እንደምንችል፤ የትስ እንደነበርን ሰፋ አድርጎ መመልከት ይገባል። በዚህ መድረክ ሁሉንም መዘርዘር ስለማያሰልችና ስለማይነበብ በነጥብ መልክ ላቅርብላችሁ። ስለቋንቋና የትምህርት ፕሮግራም በበልጠ መንደርደሪያ ሃሳቦች ለመያዝ “በመሓንዲሳዊ ዘዴ የተቃኝ ሁሉን አቀፍ ዘላቂ ልማት” የሚለውን መጽሃፌን እዩ። በዚህ ረዕስ በኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች ውይይቶች ተካሂደውበታል።

እዚህ ያደረሱንን መሰረታዊ ምክነያቶች

  1. ያረጀ ያፈጀ ያለፈበት የትምህርት ስራት መከተል፤
  2. እንቤት በማይነገር ቋንቋ ልጆችን ማስተማር፤ ለህዝብ በማይደስ ቋንቋ ምርምር ፈጠራ ማካሄድ
  3. ከ10% በታች አገር በሚጠቀመው ቋንቋ ታዳጊዎችን እንዲማሩ ማስገደድ፤ በማይሰራ ሚዛን መነገድ ነው

የኢኮኖሚ ሚዛኑን መመርመር

  1. በአሁኑ ጊዜ ከ50 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚያውቀውን ቋንቋ ትቶ 5ሚሊዮን እንኳን የማይናገረዉን ቋንቋ እናንሳ የሚሉ ሁሉ በአንክሮ እንዲያስቡ እመክራለሁ፤ የማስተማር ጊዜው ወጨው…?
  2. ለማስተማር በስራ ላይ ለማዋል ለ60 ዓመታት የተሞከረው እንግሊዘኛ አሁን ይደረግ ማለት መሳለቂያ ለመሆን ነው።
  3.    ለመሪዎች/ በአለም መድረክ ለሚደራደሩ፤ በምርምር ለሚሳተፉ ከሆነ ከቻይና መማር ይበቃል፡ እንግሊዘኛ ጥቂት ዩንቨርስቲዎች ለዚህ ተብለው ከተመደቡት በስተቀር ሌላው በቻይንኛ ነው
  4. በአሁኑ ጊዜ ዕውቀት ቋንቋ አይወስነውም፤ በአማርኛ ቋንቋ የሚፈለገውን ሁሉ ማግኘት የሚቻልበት ጊዜ እየመጣ ነው
  5. ወጣቶች በናታቸው ቋንቋ ሲያስቡ ፈጣሪ ብሩህ አይምሮ እያጎለመሱ ያድጋሉ፤ ይህም ለውጥ አምጭዎችን ያጎለምሳል
ተጨማሪ ያንብቡ:  ያለፉት ሃያ አንድ ዓመታት ፖለቲካ - ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

የቴክኖሎጂ እድሎችን ማስላት

  1. የምንኮራበት አማርኛ/ግዕዝ ቃላት በዓለም ታላቅ ታሪካዊ ቦታ ያለው ነባር የሰው ልጆች(የዓለም) የሚኮሩበት የሚጠበቅ ሃብት ነው።
  2. ፊደሎቻችን በኮምፒኡተር በስፋት እየተለመዱ፤ ቃላትና ትርጓሜያቸው እየሰፋ በመሄድ ላይ ያለ
  3. የተፍጥሮ ቋንቋዎችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስም (Natural Language Processing) ከፍተኛ ሂደት እየተደረገብት ያለ፤
  4. የጉግል ተርጓሜም በእንግሊዘኛና በሌሎችም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እየተሳለጠ ያለበት ጊዜ ነው። ጉግል ላይ ቋንቋ እሚለውን አማርኛ ብትሉ ብዙ ማየት ትችላላችሁ

የሚቀጥሉት እርምጃዎች

  1. እንደ ጤፍ ዘር ተበትኖ ከእጅ ወዳፍ በሆነ የምርት ዘዴ የሚኖረውን ወገን በህብረት የስራ፤ የሰፈራ፤ ሰፊ የኢኮኖሚ ዘርፎች እንዲሳተፍና ያለውን ወቅታዊ ገቢ ባስር እጥፍ እንዲያሳድግ ብንረባረብ፤ ከመከፋፈል ወደ መከባበርና መተጋገዝ፤ ቋንቋችን ጌጦቻችን በሁሉም አቅጣጫ እየተንከባከብን የምናቆየው ይሆናል። ወረት ማግኛ ዘዴውም ቀላል ሆኗል።
  2. የትምህርቱ መሻሻል በየትኛውም የዕውቀት ደረጃ ያል ተማሪ ሁሉ ትምህርቱን በስራ እየሚከረ እንዲያድግ ሆኖ ይስተካከል።
  3. አሁን በሰፊ እሚነገረው ላይ በመመርኮዝ ለመላው ህዝብ ተዳራሽ የሆነ ያልተጨፈነ አሳታፊ የቋንቋ አጠቃቀም ቢዘረጋ ህዝቡ (በዘረኝነት ያልተወናበደው) ይቅበለዋል። ከኢትዮጵያዊው ወገኔ ፊደላት የቅኝ ገዢው ፊደል ይሻላል የሚል ህዝብ የለም።
  4. የወደፊቱ የኢኮኖሚ ታላቅነት መንገዶችም ሆነ መስፈርቶች ገና እየተፈጠሩ ስለሆነ በህብረት ከተረባረብን እምርታ ዕድገት በማድረግ የራሳችንን ሂደትና መዳረሻ መቀዳጀት እንችላለን።
  5. የበለጠ ተጠቃሚው እየበዛ አሁን 120 ሚልዮን ኢትዮጵያዊ ብሎም 1.3 ቢሊዮን የአፍሪካ ህዝብ ሁሉ  በፊደሎች እየተጠቀመ ሲሄድ ለዓለም ዋና አማራጭ እንደሚሆን አንሳት፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share