May 30, 2022
14 mins read

“ፋኖ ማለት በየትኛውም የሀገራችን አካባቢ የሚኖር የሀገር ባለውለታ ማለት ነው” ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ

"ሀገርን የሚረግመው ሽማግሌ ብቻ አይደለም! ለሀገሩ መስዋዕት የከፈለ ወጣትም ተገቢውን ዋጋ ካላገኘ ይረግማል።"

281879168 312962384358060 5362106728364363354 nሰሞኑን ፋኖ ትጥቅ ይፍታ ተብሏል ተብሎ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው ውጅንብር በሕዝቡ መረበሽን ፈጥሮ፥ ውጥረትን አንግሦ፤ የውጅንብሩ ማጀቢያም በጥርጣሬ በሚያዙ ሕዝብ ባለውለታችን ናቸው ብሎ ከሚፈርጃቸው የሚመደቡ አንዳንድ መሪዎች ጭምር የተያዙበት አግባብና የተጠረጠሩበት ምክንያት በመንግሥት ሚዲያ አለመገለጹ ሰውን የመረጠውን መንግሥት ከማመንና ለምን? ብሎ በሥርዓት ከመጠየቅ ይልቅ እንዲመራው ያልመረጠውን ፌስቡክ በማመን ወደ ስጋትና ውጥረት አዝማሚያ እንዲገባ ጫና ፈጥሮበታል። ይህ መጥፎ አዝማሚያ ከተጋረጠበት አካባቢ አንዱ ወልድያ ከተማ ሲሆን፤ መጥፎውን አዝማሚያ ለመቀልበስ “በሀገሩ የማያገባው ባላገር የለም” በማለት ከአዲስ አበባ የቅዱስ ሲኖዶሱን ጉባኤ አቋርጠው ወልድያ የዘለቁት ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሁሉንም አካል የቃኘ እና ላልተበከለ የሠላም አየር መኖር ይበጃል ያሉትን አባታዊ ምክርና ተግሳጽ ለግሰዋል። እኛም ከሞላ ጎደል እንዲህ ከትበነዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊትን፤ ልዩ ኃይልን፤ ፋኖን ለመንቀፍ ቀርቶ ለመገምገም የሚያስችል ማንነት የለንም። ሰው ትርፍ ነገር እየሰጠ ከጀርባ ሆኖ አግዞ ይሆናል። እነሱ ግን የሚሰጡት ሕይወታቸውን ነው። ከፈጣሪ በታች አካባቢያችን፣ ሀገራችን፣ የሠላም አየር እንዲተነፍስበት የሚያደርጉ ናቸው። ምን አልባት በሰማነውና በተረዳነው ልክ በእነሱ ስም የሚነግዱ አንድ አንድ አረሞች ካሉ እንዲወያዩበት ለእነሱ በመጠቆም እራሳቸው ፈጥነው እንዲያርሙት የመጠቆም ያህል ነው የእኛ ድርሻ በማለት አመላክተዋል አቡነ ኤርምያስ።

ሳይመዘገብ የሚሮጥ አትሌት የለም። ይህን ያህል ኪሎ ሜትር እሮጠህ ብታሸነፍ ይህን ያህል ገንዘብ ትሸለማለህ። የወርቅ ሜዳልያ ታጠልቃለህ ተብሎ ነው። ፋኖ ግን የሚሮጠው ሀገሬ በነጻነት መቆየቷ፤ ወገኔ በሠላም መኖሩ ለእኔ ሽልማት ነው ብሎ ነው። ደሙን የሚያፈሰው፥ የሚራበው፥ የሚጠማው በፍፁም ተችዎቻቸው ሳንሆን አክባሪዎቻቸው ነን በማለት በተጠየቃዊ ንፅፅር ጭምር አስረድተዋል ብፁዕነታቸው።

አቡነ ኤርምያስ የግል ማኅበራዊ ሚዲያው ተፅዕኖ የመረጃ መዛባትም ይሁን እርስ በእርስ አለመተማመን መጠራጠር ጋር ተያይዞ ከጊዜ በኋላ መንግሥት አወጣ እየተባለ የሚወራው መመሪያ ፋኖን ይጎዳል የሚለው ሕዝባችንን ግራ እያጋባው፣ እያስጨነቀው ነው። ምንም ይሁን ምንም ግን ወጥ የሆነ የእዝ ሰንሰለት ከሌለን ሀገር የማቆየት አቅም አይኖረንም። ደካሞች ነው የምንሆነው። “እርስ፡ በእርሷ፡ የምትለያይ፡ መንግሥት፥ ትጠፋለች።” ነው መጽሐፍ የሚለው። ሁላችንም በየፊናችን ፈራጅ፣ ፈላጭ ቆራጭ ከሆነ አያሰነብተንም። የእዝ ሰንሰለት መጠበቅ፣ መከተል ይገባል። ተቀራርቦ በግልፅ መነጋገሩ ከውጅንብር ያድናል ሲሉም መክረዋል።

ፋኖ ማለት በየትኛውም የሀገራችን አካባቢ የሚኖር የሀገር ባለውለታ ማለት ነው። ከበርካታዎቹ የኢትዮጵያ ባለውለታዎች መካከል ለማሳያ አንዱን ብንጠቅስ ፋኖ ማለት በላይ ዘለቀ ማለት ነው። በላይ ዘለቀ አባቱ በኃይለ ሥላሴ ባለስልጣናት ተገድሎበት የአባቱን ደም ለመመለስ ከመንግሥት ኮብልሎ በሽፍትነት እየኖረ ሳለ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከሀገር ወጡ፤ ሀገርን፥ ወገንን፥ ታሪክን፣ እምነትን የሚያጠፋ የውጭ ጠላት ገባ ተብሎ ሲነገረው በደል ያደረሰብኝን ሹማምንት ከጠላት ጋር ሆኘ የበቀል ሥራ ልስራ አላለም። በ24 ዓመት ዕድሜው ስንቅ ሳይኖረው፤ አሰልጣኝና አደራጅ ሳይኖረው ያለውን ጥቂት ኃይል አደራጅቶ 5 ዓመት ለጣሊያን ጦር እሳት ረመጥ የሆነ ለሀገር ለወገን ጀግና ባለውለታ ነው ሲሉ ታሪክን በምልሰት በማሳያነት አውስተዋል አቡነ ኤርምያስ።

ታሪክ እንዳስቀመጠው ከ5 ዓመት በዱር በገደል የአርበኝነት የትግል ኑሮ በኋላ ጠላት ወጥቶ አፄ ኃይለ ሥላሴ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ “ጃንሆይ ሀገሩንም፣ ሰራዊቱንም ከእነ መሣሪያው ይረከቡኝ እኔ ተራ ሰው ነኝ አርሼ፣ አምርቼ እበላለሁ።” ነው ያለው በላይ። ትክክለኛ የፋኖ ባህሪም ይህ ነው። መንግሥት ሆኘ ልጋተር አላለም። ጃንሆይም ጀግንነትን ከትህትና፤ ማስተዋልን ከወጣትነትና ከደግነት አጣምሮ የያዘውን አርሶ አደር የቢቼና አስተዳዳሪ ሁን ስምህም ደጃዝማች በላይ ይባል ብለው ሹመውታል በማለት ብፁዕነታቸው አስረድተዋል።

ኋላ ግን መጥፎ ባንዳዎች፣ ምቀኞች፣ ስሙን ያለ ስም አጥፍተውት ያ ትክክለኛ የሀገር ባለ ውለታ ጀግና የማይገባውን አግኝቶ በስቅላት ታንቆ ነው የተገደለው። ከመሰቀያው እንጨት ላይ ከመውጣቱ እና ሕይወቱ ከማለፉ ቀድሞም “ኢጦቢያ አገልግየሽ ከሆነ ወንድ ልጅ አይውጣብሽ፤ ካለገለገልኩሽ ደግሞ ፈጣሪ ነፍሴን አይቀበላት።” ነው ያለው። እንደበላይ ዘለቀና አሁን ስማቸውን ለመጥቀስ ጊዜ የሚገድበን የሱን ዓይነት ተገቢው ዋጋ ያልተሰጣቸው በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ይኖሩ የነበሩ የሀገር ባለውለታዎች እርግማን በኢትዮጵያ ላይ አልደረሰም ብዬ አላምንም። ከዚህ መማር ያለብን ሀገርን የሚረግመው ሽማግሌ ብቻ አይደለም። ለሀገሩ ውለታ መስዋዕት የከፈለ ወጣትም ተገቢውን ዋጋ ካለገኘ ይረግማል እና መልካም፣ ጥሩ ባለውለታዎችን እንዳንጎዳ ልንጠነቀቅ ልናስተውል ይገባል በማለት በአጽንኦት መክረዋል አቡነ ኤርምያስ።

ሕዝብም እንጠንቀቅ መሪን አንተች ሳይሆን መሪ የተባለን ሁሉ መቱን እየሰደብን፣ እየነቀፍን መልካም የሚሰሩ ወጣት መሪዎች እንዳያዝኑብን፤ ከልቡ ባለ አቅሙ ጥሩ ለውጥ ለማምጣት እየጣረ፣ እየደከመ ያለ ወጣት መሪ አዝኖ ከሄደ ይኸ እርግማን የማይደርስ እንዳይመስለን፤ ጥሩ መሪ ያሳጣኝ ብሎ በራስ ላይ መፍረድ ይሆናል ሲሉም አሳስበዋል አቡነ ኤርምያስ።

ሌላው ተባብረን መክረን ልናርመው የሚገባው በየፈርጁ ያለውን ለምድ ለባሽ እና በለው በለው ባይ የመንጋ ባህሪ የያዘውን አካል ነው። በእኛ መጽሐፍ “የበግ ለምድ የለበሱ ሀሳውያን ነቢያት የሚባሉ።” አሉ። በፋኖ ስም የሚነግዱ የፋኖን ለምድ ለባሾች ካሉ መንግሥት ብቻውን አይደለም ማረም ያለበት እራሱ ትክክለኛው ፋኖም ቀዳሚ መሆን አለበት። ፋኖ በባህሪው አይኮፈስም፤ ከእኔ በላይ ጀግና የለም አይልም ልክ እንደ እነ በላይ ዘለቀ ትሁት፣ ባለ ትእግሥት ነው። አሁንም ብዙ በላይ ዘለቀዎች አሉ ከሕይወታቸው ባሻገር የሱቅ ወረታቸውንም ይዘው፣ መኪናቸውንም ሰጥተው የዘመቱ አሉ። እነሱ ለምድ ለባሹን ከሕዝብና ከመንግሥት ጋር ሁነው ሊያርሙና ሊያስተራርሙ ይገባል ሲሉም አስረድተዋል አቡነ ኤርምያስ።

አቡነ ኤርምያስ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ማስከበር፤ የዜጎችን በሠላም የመኖር ዋስትና የማረጋገጥ ኃላፊነቱን አለመወጣቱ ነው ብዙ ጣጣ እያመጣ ያለው። የሕግ የበላይነትን ያስከብር። ፍትህን ያረጋግጥ፣ መረጃ በመስጠትም በግል ማኅበራዊ ሚዲያ አይቀደም። መረጃ በመስጠትም በመቀበልም ይፍጠን ይህ ከሆነ ሕዝቡ በፌስቡክ ዘመቻ ግራ አይጋባም። በዜጎች ላይ አደጋ እንዳይደርስ የመጠበቅ ኃላፊነቱን በትክክል ይወጣ እንጅ ለቅሶ ደራሽ ከመሆን ተግባር ይውጣ። አጥፊን ይጠይቅ ልል አይሁን አጥፊ ሲቀጣ አፉ ባይናገርም አእምሮው አጥፍቼ እኮ ነው ብሎ ማመኑ አይቀርም። ንጹህ ግን ያለጥፋቱ ታስሮ እንዳይማቅቅ ጥንቃቄ ይደረግ በማለት ገልጸዋል።

የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎችም ኃላፊነታችንን በተገቢው መንገድ እንወጣ ያሉት ብፁዕነታቸው፤ አካባቢን፣ ሀገርን የሚያስመሰግን ትውልድ ለመቅረጽ እንትጋ። አሳፋሪ ትውልድ እንዳይበራከት የመስራት ኃላፊነት አለብን ብለዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም ስህተትን በሚዳፈሩ ውሱኖች ዛሬም ሌላ ስህተት እንዳይደገም መጠንቀቅን ያሻል። ፖለቲካ ነገ መቀየሩ የማይቀር ነው። በእኛ ዕድሜ የኢትዮጵያና የኤርትራ ፖለቲካ ተቀይሮ አይተናል። የኢትዮጵያ ሕዝብም የኤርትራ ወገኖቹን ቤት ጠብቆ ያስረከበ ደገኛ፣ መልካም ዜጋ መሆኑን በተግባር አይተናል። ለነገው ሕይወት ከትናንት መማር ነው ያለብን ብለዋል።

መጨረሻም ብፁዕነታቸው በአምስት ወራት የጊዜ ቆይታ ብዙ በአእምሯችን የተሳሉ ለመናገር የሚከብዱ አሰቃቂ ነገሮችን አይተናል። ራበኝ እያለች የምታለቅስ እናት፤ ምን ልቅመስና ልጄን ላጥባ የምትል እመጫት፤ አልደፈርም በማለቷ በጥይት የተመታች እህት ድጋሜ እንዳናይ አደራ ሁላችንም የድርሻችንን በመወጣት የሰላሙ አየር እንዳይበከል እንስራ እንጸልይ ብለዋል።

ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን

ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም

4 Comments

  1. “ፋኖ ማለት በየትኛውም የሀገራችን አካባቢ የሚኖር የሀገር ባለውለታ ማለት ነው።”
    100% agreed. Zerai Deres was a Fanno. Abidsa Aga was a Fanno. Jagama Kello was a Fanno.

    However, this is no time to dilly dally or obfuscate the obvious. If you are in doubt as to the real intent of the eradicate-Fanno operation of the OPDO, just look at the list of names of the truth-speaking የሀገር ባለውለታ journalists thrown in jail. Look also at the manner in which the arrested civilians were abducted illegally. This is just a purely terrorist operation by a government that not only wants to stifle dissent but it is also a bid to crush the resistance of a population to prospective operations of ethnic cleansing and genocide.

  2. አቡነ ኤርሚያስ ስለሃገር ጉዳይ የመናገር ብቃት ያላቸው ወያኔ ወልዲያን በግፍ በተቆጣጠረበት ወቅት ለክርስቲያን ለሙስሊም ሳይሉ ተገቢውን ድጋፍ የሰጡ መንፈሳዊ መሪ ናቸው:: በትክክል ጥንትም ዛሬም ህዝብን የሚታደግን ፋኖን መደገፍና ሲፋቁ ኦነግ ናቸው ፈጣሪያቸው መለስ ዜናዊ ያላቸውን የብልጽግና መሪዎች መንቀፍ ህሊና ያለው ሁሉ ግዴታ ነው:: ህሊና ቢሶች ግን ጥንትም ዛሬም ለሚገዛ ሁሉ ያጨበጭባሉ::

  3. ፋኖ ማለት እኮ ውድ የሆነውን ህይወቱን ሰውቶ ሀገርን ያቆመ የዚች ሃገር ትልቅ ባለ ውለታ ነው ።ብቻ ፈጣሪ እድሜና ጤናን ጨምሮ ጨምሮ ይስጥልን ። በቃ We have a big favor

Leave a Reply

Your email address will not be published.

military
Previous Story

ባለሀብቶችን በማገት እና በማስፈራራት ብር በጠየቁ የሰራዊቱ አባላት ላይ ክስ ተመሠረተ

ዘመነ zemene kassie mom 300x215 1
Next Story

ዘመነን መያዝ ያልቻለዉ የመንግስት ሰራዊት የእናቱን ቤት በጥይት ደብድቧል። – አስረስ ማረ ዳምጤ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop