May 30, 2022
3 mins read

ዘመነን መያዝ ያልቻለዉ የመንግስት ሰራዊት የእናቱን ቤት በጥይት ደብድቧል። – አስረስ ማረ ዳምጤ

ዘመነ zemene kassie mom 1 225x300 1ራሱን የአማራ ክልል ፀጥታ ምክር ቤት ብሎ የሚጠራው እና በየትኛውም የክልሉ እና የፌደራል ህግጋት የማይታወቀው ህገ-ወጥ ቡድን በዘመነ ካሴ ላይ ያሰማራው እና ዘመነን መያዝ ያልቻለዉ ሰራዊት የእናቱን ቤት በጥይት ደብድቧል። መፅሀፍትን ጨምሮ ያግፕኘውን ቁሳቁስ ተሸክሞ ወስዷል።

በንፁሁ ልጃቸው ላይ እሩምታ ተኩስ ሲከፈት በአይናቸው ያዩት እናት ንቦቻቸውን አስማርተው አፋኙን አዋክበውታል።

ከተኩስ ልውውጡ በኋላ አፋኙ እንደ ምርኮኛ የያዛቸው የዘሜ ወላጅ እናት የሆኑት የ80 ዓመት መነኩሴ እማሆይ የኔአለሽ ሙጨ ለማዳበሪያ መግዣ ያጠራቀሙትን ብር 6000.00 ከመቀነታቸው በሰራዊቱ አባላት።

በየ ቦታው ተመሳሳይ ድርጊቶች እንደሚኖሩ ይገመታል። በርግጥ የብአዴን ሰወች ድሮዉንም ኃላፊነት አይሰማቸውም፥ ከሰሞኑ ግን ለይቶላቸው ያበዱ ይመስላሉ። ከሁሉም የሚገርመኝ ግን ለስንት ብሔራዊ ጉዳይ “የምንተማመንባቸው” ጀነራሎች የዚህ አሳፋሪ ታሪክ አካል መሆናቸው ነው።

የተጀመረው የእብደት አካሄድ ቆሞ ህዝቡ ሰላሙን ያገኝ ዘንድ ሁሉም በየፊናው የሚችለውን ይወጣ!!!

ሕዝብን ማሸነፍ አይቻልም!!

Via አስረስ ማረ ዳምጤ

“ቤት ንብረታችንን አውድመው የ85 ዓመት እናታችንን አንገላተዋል” የዘመነ ካሴ ወንድም ፋኖ ንብረት ካሴ!!

%E1%8B%98%E1%88%98%E1%8A%90 zemene kassie momየአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) ሰብሳቢ የሆነውን አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን ለማጥቃት ከሰሞኑ ወደ ምዕራብ ጎጃም፤ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፤ መርዓዊና በአካባቢ ባሉ ጫካዎች የተሰማራው የአገዛዙ ሰራዊት በዘመነ ካሴ ቤተሰቦች ብሎም በመርዓዊ ንፁሃን ኗሪዎች ላይ በርካታ ግፎችን እንደተፈፀመ ተዘገበ።

የአርበኛ ዘመነ ወንድም ፋኖ ንብረቱ ካሴ ለኢትዮ 360 ሚዲያ እንዳረጋገጠው፣ በዚሁ ጥቃት ከሕዝብ ወገን 4 ሰዎች በጥይት ተመተዋል። ከእነዚህ መካከል 3ቱ ተሰውተዋል፤ አንዱ በከፍተኛ ደረጃ ቆስሎ በሕክምና ላይ ናቸዉ። ወታደሮቹ ስናይፐር፣ ብሬን እና መትረየስ የታጠቁ ናቸው።

“የዘመነ ካሴ የ85 ዓመት እናት ቤት በከባድ መሳሪያ ተደብድቦ፣ ከመቀነቷ የቋጠሩትን ገንዘብ ወስደውባቸዋል” ብሏል ፋኖ ንብረቱ።

የአካቢቢው ኗሪ በየቤቱ ፋኖዎችን አሳልፎ ላለመስጠት አፋኙን ቡድን ተዋግቷል። በተለይም ከአጎራባቹ ይልማና ዴንሳ ወረዳ በፍጥነት የደረሱ ፋኖዎችና ሌሎች ኗሪዎች በርካቶች እንዲነሱ ምክንያት ሆነዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop