አስቸኳይ ጥሪ የዐማራውን ህልውና ለማስጠበቅ

May 27, 2022

የዐማራውን ህልውና ለማስጠበቅ የፋኖን ሁለንተናዊ ዐቅም ማጎልበት
(ተገን ለወገን በሰሜን አሜሪካ የፋኖ ድጋፍ አሰባሳቢ ግብረኃይል)

ግንቦት 7 ቀን 2014 ዓም

ዋሽንግተን ዲ.ሲ ዩናይትድ ስቴትስ ፡ “ተገን ለወገን” ከፋኖ ቀጥተኛ ውክልና ያለው የመጀመርያው ድጋፍ አሰባሳቢ ግብረኃይል በሰሜን አሜሪካ ተመሰረተ !!

በአሁኑ ሰዓት የዐማራ ሕዝብ ከፍተኛ የሆነ የውስጥና የውጭ ጠላት ከበባ ውስጥ ይገኛል። አማራው ይህን ዙርያ ገጠም ከበባ ጥሶ ህልውናውን ማስጠበቅ የሚችለው እራሱን በማዘጋጀትና ጠላቶቹን ለይቶ በማወቅ ተደራጅቶና ታጥቆ ወገኑና ማንነቱን ለመከላከል ዝግጁ ሲሆን ነው:: ይህም እውነታ አማራዊ አንድነቱን አጎልብቶ የውስጥና የውጭ ጠላቶቹን ለይቶ በማወቅ በሚገባቸው ቋንቋ መመለስ እና ከተጠቂነት ወጥቶ የአጥቂነት ስነ ልቦናን እንዲላበስ ግድ ይለውል::

ዐማራን እጁን አስሮ የዘር ማጥፋት ሲያስፈጽምበት የኖረው የቀድሞው “ብአዴን/አዴፓ” ስያሜውን እንደ እስስት የሚቀያይረው አሁን ብልጽግና የሚባለው ዐብይ አሕመድ የሚመራው የኦነግ እጅ መሆኑን ዐማራው አጥርቶ ማወቅ አለበት። የዐማራ ህልውና ጉይዳይ ያሳስበኛል የሚል ግለሰብም ሆነ ቡድን “ብልጽግና” የዐማራ ካንሰር መሆኑን በመገንዘብ ለዚህ የሚመጥን ትግል ለማድረግ ዝግጁ መሆን አለበት። የዐማራው የህልውና ትግል ወደ ድል ጎዳና ማቅናት የሚጀምረውም ሆድ አምላኩ የሆነውን የዐማራ ብልጽግና ስብስብ ከጉያው መንቀል ሲጀምር ብቻ ነው። በዚህ ላይ ቁርጥ ያለ አቋም ካልያዝን የዐማራው የህልውና ትግል ካለበት ፈቀቅ ሊል አይችልም::

የህልውና ትግሉን በድል የመወጣትና ያለመወጣት ጉዳይም የሚወሰነው ዐማራ መስለው በመካከሉ የበቀሉትን ሆዳም ዐማሮች ነቅሎ ለመጣል በሚወሰደው እርምጃ መጠን ልክ ነው። ስለሆነም “ያገሩን ሠርዶ ባገሩ በሬ” እንዲሉ ፋኖ በቀበሌ፣ በወረዳና በዞን መደራጀቱን ቀጥሏል። ዐማራ ነኝ የዐማራ ህልውና ማጣት የእኔም ህልውና ማጣት ነው ብሎ የሚያስብ ዐማራ ፋኖን በሁለንተናዊ መልኩ ዐቅሙን እንዲያጐለብት ለመደገፍ ከጎኑ መቆም አለበት። ፋኖን መደገፍ ውዴታው ብቻ ሳይሆን ግዴታውም ጭምር እንደሆነ እያንዳንዱ ዐማራ ሥነልቦናው ሊያደርግ ይገባል::

ፋኖ ደሙንና አጥንቱን ሕይወቱን መስዋዕት አድርጐ የዘረኛው ወያኔን ግሥጋሤ ገቶ የዐቢይ አሕመድንና የሆድ አደሩ ደመቀ መኮንን መንበር ሳይቀር ከወያኔ መንጋጋ ማትረፉ የማይካድ እውነታ ሆኗል። ነገር ግን ፋኖ የወገኑ መገደል፣ መፈናቀል፣ መደፈር፣ መዋረድ፣ መሳደድ አስቆጭቶት ከወያኔ ጋር እየተናነቀ ባለበትም ሰዓት መላው ኢትዮጵያን ከወያኔ መንጋጋ የታደገውን ፋኖን ለማጥፋት ብልጽግና ቀጥተኛ ዘመቻ ከፍቷል። ይህም ቁልጭ አድርጎ የሚያመለክተው ኢሕአዴግ የትሕነግ መገልገያ መሣሪያ እንደነበረ ሁሉ ብልጽግና የተባለው ስብስብም የኦነግ ፍላጎት ማስፈጸሚያ መሆኑን በገሐድ እያዬን ነው:: ሽመልስ አብዲሳም ያረጋገጠልን ይህኑ ነው::

የዐማራ ሕዝብ ሰላም ወዳድና ከሁሉ ጋር በሰላም የኖረ ለመሆኑ ዘመናትን የተሻገሩ ታሪክና ይመሰክራሉ። ዐማራን ለማጥፋት መጀመርያ ፋኖን ማጥፋት ነው ብለው የተነሱት ብልጽግና፣ ወያኔና ግብራበሮቻቸው ከየአቅጣጫው ክንዳቸውን እየዘረጉ እንደሆነ በገሐድ እያዬን ነው። ስለሆነም በውጭ የሚኖር ተቆርቋሪ ነኝ የሚል የዐማራ ማኅበረሰብ ፋኖ ለተያያዘው የህልውና ትግል ማስፈጸሚያ የሚውል ትንሽ ትልቅ ሳይል የሐሳብ፣ የዲፕሎማሲ፣ የሚዲያ፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፋ በተደራጀ መልኩ በተከታታይ እንዲያደርግ ይጠበቃል::

ለዚህ እንዲረዳ “ተገን ለወገን በሰሜን አሜሪካ” በሚል መጠሪያ በውጭ ሀገር ከፋኖ ቀጥተኛ ውክልና ያለው የመጀመርያው ድጋፍ አስተባባሪ አስኳዋል ግብረኀይል ተመሥርቷል:: ስለዚህ በውጭ የሚገኝ ማንኛውም አማራ ይህን ግብረኅይል ተቀላቅሎ ፋኖን በቀጥታ እንዲረዳ ይህ አስቸኳይ ጥሪ ቀርቧል፦ በኢሜይል TegenAmhara@gmail.com ፤ በስልክ 202 656 9767 ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ስንገልጽ በማክበር ነው::

የፋኖ ህዝባዊ ንቅናቄ የመጨረሻው የህልውና ተስፋ መሆኑን አሰተውለው  በሃላፊነት ይመልሱ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

284645151 5774506125898316 1627422399044441130 n
Previous Story

በዘረኝነት የሚናጠው የመጅሊስ ቢሮን ለመቆጣጠር የኦሮሚያ መጅሊስ ሃጂ ሙፍቲን ከስልጣን አባረርኩ አለ

284375734 10227326710984276 7097029380191254601 n
Next Story

ኦህዴድ ዛሬ የያዘዉን ስልጣን ያገኘዉ እጅግ በርካታ ጀግኖች ወያኔን ታግለዉ በህዝባዊ ትግል አስወግደዉት ነዉ

Go toTop