May 27, 2022
4 mins read

በዘረኝነት የሚናጠው የመጅሊስ ቢሮን ለመቆጣጠር የኦሮሚያ መጅሊስ ሃጂ ሙፍቲን ከስልጣን አባረርኩ አለ

284645151 5774506125898316 1627422399044441130 n

በርካታ ሙስሊሙች ሃይማኖታችን በዘርና በፖለቲካ እየተዋቀረብን ነው ሲሉ አቤቱታ ያሰማሉ። በሱፊና ሰለፊ ቅርቃር ውስጥ የገባው የፖለቲካ ተልዕኮ ያለው የሸራተኑ ጉባዬ ለዲናችን አደጋ ነው ሲሉ አምርረው ይናገራሉ። በአሁናዊ ፖለቲካ መጅሊሳችን ተጠልፏል ሲሉ ይገልጻሉ። በመንግስት ስልጣን ላይ ባሉ ውሃቢዬዎች የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እና በዘረኝነት የሚናጠው የመጅሊስ ቢሮን ለመቆጣጠር የኦሮሚያ መጅሊስ በሸራተን ተሰብስቦ ሙፍቲውን ማባረሩን መግለጫ ሰቷል። የውሃቢየዎች ቡድን እነደሆነ የሚነገርለትና በሃገሪቱ ሰላም መደፍረስ ተጠያቂ የሆነው የአሕመዲን ጀበል የውሃብዬ ቡድን ሙፍቲህ ሃጂ ኡመር እንድሪስ አማራ ስለሆኑ ከስልጣን ይውረዱ በማለት ጫና እያደረገ መቆየቱ ይታወሳል።

284645151 5774506125898316 1627422399044441130 nኦሮሞዎች ስልጣን ይቆጣተሩ የሚለው የፖለቲካ መፈክር ያነገበው የውሃብዬው ቡድን በሸራተን አዲስ ሙፍቲውንና አማሮቹን ያገለለ ስብሰባ ማድረጉ ይታወቃል። ኡለሞች የነብዮች ወራሾች ናቸው። ስለዚህ የመጅሊስ ስልጣን ባለቤት ህዝብ ሳይሆን ኡለሞች ናቸው። መጅሊሱ በኡለሞችና በሹራ ይመራል። ኡለሞች መጅሊሱን ዲኑ በሚፈቅደው መልኩ ያዋቅራሉ ያስተዳድራሉ። መጅሊሱ በሸራተኑ ጉባዔ ከገባበት የሱፊ ሰለፊ ቅርቃር ወጥቶ ወደ ቀድሞ ሐጅ መሐመድ ሳኒ ሃቢብ ወዳዋቀሩት ማንነቱ ይመለስ እና የReform ስራ ይሰራ። ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

ኢዙና አሕመድ የተባሉ አንድ ሙስሊም እንዲህ ብለዋል። «አገር ሲያረጅ ጃርት ያበቅላል» ይባላል። ከዛሬው የፌክ ምርጫ ብዙ ትሩፋቶች እየታየኝ ነው። ከትሩፋቶቹ ውስጥ የመጅሊሱ ጉዳይ የጥቂቶች ነበር። አሁን ግን እርስ በራሳቸው ተመራርጠው የሁሉም አድርገውታል። ከዚህ በኋላ በጭምብል ማንነት መንቀሳቀስ እንደማይቻልም አንዳንዶች ስውር ማንነታቸውን ገልጠው አሳይተውናል። መንግሥት ህግ በማስከበር ሂደት ላይ የራሱን ሚና ካልተጫወተ ተረኝነቱን ያሳብቅበታል። በነገራችን ላይ በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ሙስሊም ወክለን መርጠናል ያሉ ሰዎች ምርጫው በውይይት መድረክ እንደማያወጣ ካወቁና ከተረቱ በኋላ ነው። ከዚያ ወደ ሚመቻቸው ማለትም ተረኝነትን፣ ኢ―አቂዳዊነት፣ ኢ―መዝሃባዊነትን፣ ዘረኝነትን… አዳቅለው ምርጫ አካሂደዋል። ለእኔ ሰዎቹ ሩቅ ሳይሄዱ ገድፈዋል። ምክንያቱም ኢስላም ከጠቀስኳቸው ነገሮች የፀዳ ነው። የስልጣን ባለቤትነት የሚሰጠው ከየትም ተጠረቃቅመው ለመጡ ጉባኤተኞች ሳይሆን «ለኡለሞች» ነው። መፍትሔው ከዚህ በፊት ሸራተን የተካሄደውን የጉባኤ ውሳኔ ሰርዞ መጅሊሱ በፊት ወደ ነበረበት ቦታ መመለስ ነው። የታሪክ ሙሁሩ ጋሽ ተሾመ ብርሃኑ ባልተገኘበት እና ባልተሳተፈበት የተካሄደው ምርጫ እንደማይቀል ገልጿል። ፕሮፌሰር ናሲር ዲኖም የስብሰባውን አላማ ካወቀ በኋላ ትቶ ወጥቷል።

i (ምንሊክ ሳልሳዊ)

 

 

1 Comment

  1. አህመዲን ጀበል ሙፍቲ ተብሎ በብልጽግና ካልተሾም ህዝበ ሙስሊሙ ጤና የሚያገኝ አይመስለኝም ከሳውዲና ከቱርክ በሚያገኘው ድጎማ እኝህን ሰው ጤና እየነሳቸው ነው ለአህመዲን ጀበል፤ለጁዋር መሃመድ፤ለአቡ ሀይደር፤ ለአቡበከር ሃይማኖቱ ገንዘብ ማግኛ ነው ለኝህ ምስኪን አባት ግን ከፈጣሪ የሚያገናኛቸው ድልድይ ነው። እንግዲህ ጥጋባቸውን የሚያበርድላቸው ካልመጣ የሚደርሳቸው ገንዘብ ካልተቋረጠ ረብሻውና ጥጋባቸው ይቀጥላል። ህዝቡንም አንዴ ሲያሳርዱ አንዴ ከወሃቢ ወደ ሱኒ ከሱኒ ወደ ሽያ እየለጉ መላቅጡን ያሳጡታል።ህዝቡንስ ምን ነካው በቃችሁ ማለት ምኑ ከበደው? ነው የመንግስት እገዛ አላቸው?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Ethiopia 713x350 1
Previous Story

መጥፎው ታሪካችን እንዳይደመር ፤ ጥያቄዎቼ በአግባቡ ና በአፋጣኝ ይመለሱ – ሲና  ዘ ሙሴ

Fano
Next Story

አስቸኳይ ጥሪ የዐማራውን ህልውና ለማስጠበቅ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop