ለህዝብ ከወገኑ ጋር አብረን እንቁም – ግርማ ካሳ

አብይ አህመድ አቶ ዮሐንስ ቧያሌውን ከስራ አባሯል። በአንድ በኩል ‘እኔን አልታዘዝክም፣ ለኔ ለምን አላጎበደድክም ? ለምን እኔን ቻሌንጅ አደረክ ?” ብሎ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የአማራው ማህበረሰብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ለምን ተነሱ ብሎ ነው።
አቶ ዮሐንስ ቧያሌው እንደነ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ ደመቀ መኮንን፣ ብናልፍ አንዷለም V8 መኪና፣ ጥበቃ ተመድቦለት፣ የተለያዩ ምድራዊ ጥቅማ ጥቅሞች ተሰጥተውት ፣በስልጣን ላይ ስልጣን በሽ በሽ እየተደረገለት መኖር ይችል ነበር።
አቶ ዮሐንስ ቧያሌው የአዴፓ ከፍተኛ አመራር ሆኖ አዴፓ ፈርሶ ብልጽግና እንዲመሰረት ትልቅ አስተዋጾ ያደረገ ነው።፡ያንን ያደረገው አብይ አህመድ ዘር ከፖለቲካችን ይወጣል፣ ትግሬ፣ አማራ መባበል ይቀራል፣ አማራው በሁሉም ክልሎች ውክልና ያገኛል. በኦሮሞ ክልል ውስጥ ብቃት እስካለው ድረስ አመራር ሆኖ መመረጥ ይችላል፣ ሕገ መንግስቱ ይሻሻል “የሚል ተስፋና ቃል ተሰጥቷቸው ስለነበረ ነው። ግን አብይ አህመድ አዴፓን ካፈረሰ በኋላ የለየለት ትልቅ ክህደት ነው በነ አቶ ዮሐንስ ላይ ያደረገው።
አብይ አህመድ፣ አቶ ዮሐንስ ሲያባርር ፣ “እስቲ የት ይሄዳል ? ሲቸገር ልኩን ይገባል” ከሚል ነው። አቶ ዮሐንስ እንደ ሌሎቹ ተራ ደንቆሮ ካድሬ አይደለም። የተማረ ፣ የትም ቦታ ሄዱ ሰርቶ መኖር የሚችል፣ ሲኖርም የነበረ ሰው ነው። አብይ አህመድ ግን መስሎት ነው።
ሌላው ደግሞ በዮሐንስ ቧያሌው ላይ ይሄን የበቀል እርምጃ ሲወስድ፣ የአማራውን ማህበረሰብ ጥያቄ ማንሳት ዋጋ ያስከፍላል ለማለት ነው። ዮሐንስ የተባረረው ለምን የህዝቡን ጥያቄ አነሳህ በሚል። የአብይ አህመድ ችግር በግለሰብ ደረጃ ዮሐንስ ላይ አይደለም፣ ችግሩ ከሕዝቡ መሰረታዊ የፍትህ፣ የእኩልነት ጥያቄ ጋር ነው።
ወገኖች፣ ዮሐንስ ቧያሌው ችግር የለበትም። እግዚአብሄር ይመስገን ሰርቶ መብላት፣ ቤተስቡን ማስተዳደር የሚችል ነው። ነገር ግን “
– ለወሰደው አቋም፣ ለሕዝብ ድምጽ በመሆኑ፣ የሕዝብን ጥያቄ በማንሳቱ፣ ‘እናመሰግንሃለን” ለማለት፣
– አብይ አህመድና ኦህዴዶች ለሕዝብ የቆሙትን በኢኮኖሚ ለመቅጣት፣ ለማዋረድ፣ ለመጣል ሲሞክሩ፣ ለሕዝብ የወገን ግን መቼም እንደማይወድቅ ለማሳየት
የፍቅር ስጦታ ለማበርከት ነው። ለህዝቡ ከወገኑ ጋር አብረን እንቁም።

https://youtu.be/dOLP4GusJWk

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: አንድሬስ ኢንዬሽታ - የዘመኑ የእግር ኳስ ቴክኒሽያን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share