መንግሥት በወሰደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን በቄለም ወለጋ ዞን የጊዳሚ ወረዳ ከአሸባሪው ሸኔ ነፃ መውጣቱን በኦሮሚያ ክልል የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ። የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር ተወካይና የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሣ በሻ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በጊዳሚ ወረዳ አሸባሪው ሸኔ ዘግናኝ ግድያዎችንና የንብረት ውድመት ፈጽሟል።
በወረዳው በተለያዩ ቦታዎች 81 ሰዎችን እንዲሁም በጅምላ ተገድለው አስከሬናቸው አንድ ቦታ የተገኙ 87 ሰዎችን በድምሩ168 ንጹሐን መገደላቸውን ገልጸዋል።
አሸባሪው ሸኔ በወረዳው በቆየበት ጊዜ 30 የመንግሥት ተቋማትን ንብረቶችን ማውደሙንና ዝርፊያ መፈጸሙን አስታውቀዋል።
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎች ፣ኮምፒውተሮችና ሰነዶች ዝርፊያና ውድመት ደርሶባቸዋል።
የወረዳው አስተዳደር ጽህፈት ቤት፣ ከተማ ማዘጋጃ ቤትና ፖሊስ ጣቢያንም ማቃጠሉን ገልጸዋል።
የሽብር ቡድኑ በትምህርት ዘርፉና በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። በወረዳው የሚገኙ 45 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ አራት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና በስድስት ጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች…
(ኢ ፕ ድ)