አቤቱታችንን ለሚመለከተው አድርሱልን?

https://youtu.be/xjTfumFPu0Y

ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዋና ጽሕፈት ቤት:

አዲስ አበባ

ጉዳዩ: ፍትህ ስለመጠየቅ:

እንደሚታወቀው በተማሪዎች የተጀመረው አብዮት በጉልበተኛ ወታደሮች ተቀልብሶ ሀገሪቱ በርካታ ወጣቶችን አታለች::

የሚያሳዝነውና የብዙዎቻችንን ልብ  እስከ አሁን ድረስ እያደማ ያለው ጉዳይ ደግሞ በሰፊው ሕዝብ ምሬትና ጥላቻ ምክንያት ደርግ በወደቀ ማግሥት በእስርና በጫካ ውስጥ ሲንገላቱ ቆይተው ለትግል ያቁዋረጡትን ትምህርት እንደ ገና ገብተው ከጨረሱና ተመርቀው ሕዝቡን በማገልገል ላይ የነበሩትን የኢሕአፓ አባላትን እነ ታምራት ላይኔና በረከት ስሞን ከመሪያቸው መለስ ጋር በመሆን ለድርጅትዋ ከነበራቸው ፍራቻ የተነሳ ከየቦታው በማደንና በማሳፈን በርካቶችን ዳብዛቸው እንዲጠፋ ያደረጉ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ቁርጡን የሚነግራቸው ጠፍቶ ቤተ ሰቦቻቸው እያለቀሱ የሚገኙ መሆኑን ይህ ከዚህ በላይ በሊንኩ ላይ ያለው ቃለ መጠየቅ በቂ መረጃ ይሆናል ብለን እናምናለን:: (please click the link to watch)

ከእነዚህም መካከል:

1) አበበ ዓይነኩሉ (የደ/ማ ልጅ)
2) አለሁበል (የባሶ ሊበን ልጅ)
3) ድሉ ገበየሁ (የደጀን ልጅ)
4) ጌታቸው አበበ (የይቦቅላ ቁይ ልጅ)
5) ተሾመ ቢምረው (ምናልባት የቢቸና)
6) ወዘተ

የተባሉት ወንድሞቻችን ከአዲስ አበባ! ከባህዳርና ከሚሠሩበት መ/ቤት ታፍነው በመወሰድ ይገደሉ ወይም ይታሰሩ እስከ እሁን ድረስ ባለመታወቁ ይሄው በቃለ ምልልሱ ላይ እንደምትሰሙት (ወንድም) ቤተ ሰብ ያለቅሳል::

የሚገርመው ግን ጋይም (የኢሕአሠ መሪ የነበረው) ሳሪስ አካባቢ በድንገት ሲገሉት አለሁበል ከአደጋው አምልጦ እንደነበረና ከዚያ በሁዋላ ኮተቤ አካባቢ ከሁለት ልጃገረዶች ጋር በዲኤክስ መኪና ውስጥ እንደነበረ እንዳፈኑትና ወደ ሰባተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከሴቶቹ ጋር እንደወሰዱትና ወዲያውኑ ታምራት ላይኔ ተደንቆ በመምጣት እንዳየውና እንደዛተበት ሁለቱ ልጃገረዶች ሲፈቱ ተናግረዋል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  "እኔ ግን አልሞትኩም" - አላሙዲ

ጋይም ከሞተ በሁላ ግን (የሚጠሉት የአድዋ ልጅ ቢሆንም) በዘመዶቹ አሳሳቢነት አስከሬኑ አደዋ ተወስዶ በክብር በመቀበሩ ምክንያትዘመዶቹ እርማቸውን ያወጡ ሲሆን ከዚህ በላይ ስማቸው የተጠቀሱትና የሌሎች በርካታ የኢሕአፓ አባላት ነበሩ ተብለው የተጠረጠሩ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ቤተ ሰቦች እስከ አሁን ድረስ እያለቀሱ ይገኛሉ::

ስለዚህ የእነዚህን እና የሌሎች መሰል ወገኖቻችን አያያዝና የት እንደደረሱ! በማን እንደተያዙና የት ተወስደው እንደተገደሉ (ይኖራሉ ተብሎ ጭራሽ ስለማይገመት):-

ሀ) አቶ ታምራት ላይኔ
ለ) አቶ በረከት ስሞን
ሐ) አቶ ታደሰ ጥንቅሹ
መ) በወቅቱ በተያዙበት ክልልና በሀገር ደረጃ በዚያን ጊዜ ስልጣን ላይ የነበሩ ሰዎች ተጠይቀው ትክክለኛው መረጃ ለቤተሰቦቻቸው ተነግሮ ከልቅሶ እንዲያርፉ ይደረግ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን::

ግልባጭ:

ለሰላም ሚ/ርጽ/ቤት
ለሰባዊ ኮሚሽን ጽ/ቤት
ለኢሰመጉ ጽ/ቤት
ለኢሕአፓ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ

ለአማራ ክልል አስተዳደር ጽ/ቤት
ባህርዳር

ጉዋደኞቻቸው ከእያለንበት

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share