የኤርሚያስና የጃክ ማ ሽርክና አደገኝነትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማብራራት ልሞክር – ካሳ አንበሳው

ሰዋቹ ተሻርከናል የሚሉት አንድን ጫፋ ከሌላኛው ጫፍ የሚያገናኝ የበይነ-መረብ ኤሌክትሮኒክስ ገበያ (end to end e-commerce) ምስረታ ላይ ነው፣ ይህ ማለት ከአምራቹ (ከነጋዴው) ወለል አንስተው ገዥው በር ላይ ያደርሳሉ፣ የክፍያ፣ የመጋዘንና የትራንስፓርት (የባህር፣ አየርና ምድር) ጉዳዬችን እራሳቸው ይጨርሳሉ፣ ይህን አንድ ብለህ ያዝልኝ፣

የሁለቱ ሻርኮሽ ሽርክና የኢትዮጵያን ገበያ ከሌላው አለም ገበያ (በተለይ ከቻይና ጋር) virtually ይቀላቅለዋል፣ ይህን ሁለት ብለህ ያዝና የሀገራችን ድርጅቶች አቅምና የተወዳዳሪነት ደረጃን እያሰላሰልክ ቆይ፣ ንግዱ one way እንደሚሆን ይገለጥልሀል፣

ሻርኮቹ ‘ተሻረክንበት’ የሚሉት አምራችን ከሸማች ያገናኛል የሚባለው የበይነ-መረብ ገበያ (end to end e-commerce) የተለመደው “traditional” ገበያ ውስጥ ያሉትን እንቅፋቶች (barriers) “የት ነበሩ?” እስክንል ድረስ ሙልጭ አድርጎ ያስወግዳቸዋል፣ acid wash ያደርጋቸዋል፣ ይህ ማለት አዲስ አበባ ቁጭ ብለህ ከቻይና አምራች/ነጋዴ መግዛት የሁለት/ሶስት ክሊኮች ጉዳይ ብቻ ይሆናል፣

[በነገራችን ላይ ሀገራት የራሳቸውን አምራቾች ከቻይና ጥቃት የሚከላከሉት ሆን ብለው እንቅፋት (trade barriers) በማብዛትና ከቻይና አምራች/ነጋዴ መግዛት አስቸጋሪና ውድ በማድረግ ነው፣ አንዳንድ ምርቶችን ከነአካቴው ያገዱ (ban ያደረጉም) አሉ]

“ሻርኩ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዋቻችንን ይሰለቅጥብናል፣ ይህን-ወይም-ያን ኢንደስትሪ ይጎዳዋል” እያልን መተንተን ለኛ ቅንጦት ነው፣ ለዛ ቅንጦት ያልደረስን መናጢ ድሆች ነን፣ አሉን የምንላቸውን ጥቂት ፋሪካዋችን አጎዋ አስበርግጓቸዋል፣ ኤርሚያስ እስከወዲያኛው ያሰናብታቸዋል፣ እኔ እየሰጋሁ ያለሁት ለሸማኔው ጭምር ነው፣

ቻይና ተሰርቶ የሚመጣ የሀገር ባህል ልብስ እንዳለ በቅርብ ነው ያወቅኩት፣ የሻርኮቹ ሽርክና ነጠላ ቋጭተህ እንኳን እንዳትበላ ነው የሚያደርግህ፣ ሮቦት እዛው ቻይና ውስጥ ይቋጨዋል፣ ሰፌድ አይቀርም፣

ተጨማሪ ያንብቡ:  የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ቀናት ያደረጉት ውይይት ተጠናቀቀ

ሽርክናው መሬት ላይ ሲወርድ መቶ ወይም ሁለት መቶ ሰራተኞችን ሊቀርጥር ይችላል (ቆየት ሲል በሮቦት መተካታቸው አይቀርም)፣ ትንንሽ አምራች ድርጅቶችንና ቸርቻሪዋች (retail shops) ሲሰለቀጡ ለመታዘብ ግን አምስት ዓመት መጠበቅ ይኖርብሀል፣ በመጀመሪያው አራት አምስት አመት ሸማችና ኤርሚያስ ደስተኞች ናቸው፣ ከአምስት አመት በኃላ ኤርሚያስና ሸሪኩ ብቻ ናቸው ደስተኞች፣

“ህምምም ሲጀመር ሸማቹ የውጭ ምንዛሬ አያገኝም፣ ስለሆነም ጉዳዩ የሚያሳስብ አይደለም የሚል አይጠፋም” እንዲህ ያለ አስተሳሰብ/ግምት ኤርሚያስን ካለማወቅ የሚመነጭ ነው፣ ኤርሚያስ ብልጣ ብልጥነትን ከአርቆ አሳቢነት ጋር የተካነ ኮርማ ነው፣ ያሰላል፣ ያሰላስላል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሬ ጥቁር ገበያ (black market) ትልቅ እንደሆነ ኤርሚያስ አያጣውም፣ እድሉን ካገኝ ከዚህ በላይ ሊሰፋና ሊጠልቅ እንደሚችል ይገባዋል፣ የኤርሚዬስ ታርጌት ያ ነው፣ ሽርክናው እውነት ሁኖ ስራ ላይ ከዋለ በጥቁር ገበያ ውስጥ የሚሽከረከረው የ$፣ £ ወይም € ኖት ሳይሆን የውጭ ሀገር ባንኮች debit/credit card ነው፣

ካሳ አንበሳው

2 Comments

  1. ካሳ ይህ የጸዳ አስተያየትህ ነው? ኤርምያስ አንዱ ችግር ብለህ በጠቀስከው የውጭ ምንዛሪን አስመልክቶ ባለፈው ጥሩ መፍትሄን እንደጠቆመ ትዝ ይለኛል። አሊባባ ኤርምያስን የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ተወካይ ነው ያደረገው ይህ በትልቅ ሀገር እና ካምፓኒ የተደረገና ኢቤይና አማዞንን የሚግደራደር በመሆኑ ካምፓኒው መሰረቱ ኢትዮጵያ በመሆኑ ሀገራችን በትራንዛክሽኑ ተጠቃሚ ትሆናለች። ባለ ብሩህ አእምሮው ኤርምያስም ከሚያገኘው ትርፍ ሀገራችንን ይለውጣል የሚል እምነት አለኝ። ስህተት ሊኖር ይችላል እንኳ ተብሎ ቢገመት ቀድሞ ከመጥለፍ ይልቅ በውስጥ መስመር ስጋትና እርምት የሚደረግባቸውን አሰራሮች መጠቆም በተገባ ነበር። ትግሬዎች በፈላጭ ቆራጭ ዘመናቸው ሲያሹት ከረሙ ቻይናዎች ግን ያለውን ችሎታ በመገመት እንደገና ቢመልሱት እኛ ተቀበልነው እንደው ምን ይሻለን ይሆን?

  2. ምን ጊዜም ንግድ ሲጀመር ስጋተቶች ይኖራሉ፡፡ ስጋትን በመፍራት አለመስራት ደግሞ የሚደገፍ አይደለም፡፡ ስለዚህ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እየፈቱ መቀጠሉ አማራጭ የሌለዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም እንደሚባለዉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share