ለጥምቀት በዓል የወጡ ምዕመናን ቡራዩ ላይ ሁለት ሰዎች ተገደሉ

ለጥምቀት በዓል የወጡ ምዕመናን የማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያምና የሚካኤል ታቦታትን አጅበው ይጓዙ በነበረ ወቅት ከባንዲራ ጋር በተያያዘ ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ሥፍራው ላይ የነበሩ “የዓይን ዕማኝ ነን” ያሉ ሰዎች ተናግረዋል።

ችግሩ የተፈጠረው በቡራዩ አስተዳደር ሥር በሚገኘው አንፎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። የሁለቱን ሰዎች መገደል ያረጋገጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ስለደረሰው ጉዳት “ጥልቅ ኀዘን” ገልጿል። የተፈጠረውን ሁኔታ እንደሚያጣራና በአድራጎቱ ተጠያቂ የሆኑትን ሕግ ፊት እንደሚያቀርብም አስታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአብይ ድብቅ ስብሰባ | አሜሪካ ዱቄቱ ተሽጧል! | አሜሪካ ስለአማራና ኦሮሚያ ተናገረች | የደመቀ፣ይልቃል፣ ዐቢይና ጌታቸው ዝግ ስብሰባ | ጎንደር፣ ራያ አላማጣና ወልቃይት

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share