January 22, 2022
14 mins read

የ ፴ ዓመት መከራ – ማላጂ

በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ የተዘራ የጥፋት ዓረም መድብል የሆነዉ ህገ -ኢኃዴግ ( መንግስት) እ.ኤ.አ. 1994 ጀምሮ ከተተከለበት ጀምሮ በኢትዮጵያ አንድነት እና ህልዉና፣ ኢትዮጵያዊነት እና ማንነት መሰረቶች  መናድ ነበር ፤ነዉ ፡፡

ይህም በአለፉት የኢትዮጵያ ስርዓቶች ተፈጽሞ የማያዉቅ በዜጎች ላይ በደል ፤ ማግለል እና መግደል ተዘርቶ እና አጎምርቶ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡

በዚሁ ህገ መንግስት/ ኢህአዴግ  አንቀፅ ፲፩ ፡ የመንግስት እና የኃይማኖት መለያየት-በሚለዉ ድንጋጌ ነዑስ አንቀጽ ስር ፡

፩. መንግስት እና ኃይማኖት የተለያዩ ናቸዉ፣

፪. መንግስት ኃይማኖት አይኖረዉም ፣

፫.መንግስት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም….ይላል ፤ብሎናል ፡፡

ሆኖም ላለአለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ኃይማኖት ተቋማት በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ላይ ያልደረሰ መከራ ፣ስቃይ፣ እንግልት እና ሞት ነበር የሚል ካለ እርሱ የራሱን መተዳደሪያ ደንብ ( ህገ -ኢህዴግ/መንግስት) የራሱ ብቸኛ ጋሻ አድርጎ የሚያስብ ግለኛ አድር ባይ ብቻ ይሆናል፡፡

በየትኛዉም የኢትዮጵያ የመንግስት ስርዓት በቤተ ዕምነት ሞት ቀርቶ አጥር ግቢ መግባት ለማንኛዉም የመንግስት አካል ክልክል ነበር ፡፡ በህገ -ኢህዴግ ግን በቃል የሚነበብ በተግባር ገርበብ የሚደረግ ህገ….. የኃይማት ተቋማት ተደፈረዋል፡፡ እንደ አገራችን የዘመን አቆጣር 1993 ዓ.ም. ዕጉም ያሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ከቅድስት ማርያም ግቢ ባለጊዜ የህወኃት ወታደሮች  በመግባት ተማሪዎችን ገድለዋል ፣ አሳደዋል ፤ደብድበዋል ፤አዋርደዋል፡፡ ለዚህም የዘመኑ የቤ/ ክርስቲያን አስተዳደር እና አባቶች ተባባሪ መሆን ወይም አይቶ እንዳላዩ ማለፍ ለዛሬ የኢትዮጵያዉያን፣ ኢትዮጵያ እና የኃይማኖት ተቋማት ዉርደት እና ሀፍረት መንስዔ ሆነዋል፡፡

ኃይማኖት እና መንግስት ይለያያሉ የሚለዉ ህገ- ኢህዴግ የዕምነት ተቋማት ዉስጥ (ቤተ ክ/ያን እና መስጂድ) ያላደረገዉ ነገር ካለ በመንግስት አስተዳደር መዋቅር ዘርግቶ ፩ ለ፭ እና ፀረ….. እያለ ገቢዉን ለእኔ ማለት ብቻ ነዉ ፡፡

በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት ፣ ማንነት  እና ኃይማኖት ላይ በተደረጉ ተቋማዊ ማሳደድ እና ማስወገድ በተለይም የኃይማኖት ተቋማት ኃላፊነትን ፤ መንግስት እና ጥፋተኞች ተጠያቂነትን እንዲወስዱ ቢሆን አሁን እና እና አገሪቷ የደረስንበት እጂግ አሳዛኝ እና ዉስብስብ ችግር ላይ ባልተገኘን ነበር ፡፡

ዛሬ በግል እና በወል ነጻነት፣ በአገር አንድነት እና ሉዓላዊነት ፣ በማህበራዊ ኑሮ ምስቅልቅል የምንገኘዉ ህዝብን እና አገርን እንደ ቀዳሚ እና ዘላለማዊ ኗሪ አድርጎ የሚገባዉን ክብር፣ ፍቅር እና መስተጋብር በመንሳታችን ነዉ ፡፡

የሁሉም ኃይማኖት መነሻ እና መዳረሻ ሠባዊነት እና ዘላለማዊ  ድህነት ሆኖ ሳለ እንደ ፖለቲካ ድርጂቶች ከህዝብ እና አገር በላይ የራሳቸዉን ተድላ እና ጥቅም በማስበለጣቸዉ ለአለፉት ፴ ዓመታት የዕምነት ተከታዮች እና ዕዉነተኛ ዜጎች በአገራቸዉ እና በራሳቸዉ የግል ፣የጋራ እና የዕምነት ጉዳይ የሰማዕትነት ዋጋ እየከፈሉ ሲኖሩ የኃይማኖት መሪዎች አዚህ ግባ የሚባል በአገርእና ዜጎች ላይ ለደረሰዉ እና ለሚደርሰዉ መከራ ኃላፊነት ሲወስዱ አይታዩም፡፡

እዚህ ጋ የእነ አቡነ ጴጥሮስ ፣ ሚካኤል፣ ቴወፍሎስ….እንዲሁም በህይወት ያሉትን እና የምናከብራቸዉን እነ አቡነ ኤርምያስ፣ አቡነ አብርኃም… ተጋድሎ እና አቋም እንኳ የእኛ እና የኢትዮጵያ ህዝብ አቋም ነዉ የሚል የኃይማኖት አባቶች እና ተቋማት ሀሳብ አላየንም፡፡

ይህ ብቻ አይደለም የሠላሳ ዓመቱን ትተን ባለፉት ሶስት ዓመታት ዜጎች እንደወጡ ሲቀሩ ፣ በቤታቸዉ ሲገደሉ ፣ አገር እና ህዝብ ገደል አፋፍ ላይ ቆመዉ  በሞት እና ህይወት ሲቃ ሲገኙ ለዚህ አገር እና ህዝብ የመከራ ምንጭ እና መንስዔ   እንዲሁም መፍትሄ ህገ-ኢሃዴግ ዉስጥ ስላለ እና ይህም የአገር እና የህዝብ ጉዳይ የየትኛዉም ኃይመኖት ጉዳይ መሆኑን እና መስጂድ እና ቤ/ክ የሚገባ ገዳይ ይህን መከታ አድርጎ በኃይማኖት ጣልቃ ገብነት መጠየቅ አለበት አላሉም ፡፡ እናም “ዉሾች ይጮሐሉ…ግመሎችም መጓዛቸዉን ቀጥለዋል ” እንዲሉ ……..፡

እናም ዕዉነተኛ ኃይማኖት ሠባዊነት ሲሆን ሠባዊነትም ፣ ኢትዮጵያዊነትም ሆነ ኃይማኖት ፣ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ባንዲራ  ከመንግስት፣ ከህገ -መንግስት /ኢህዴግ ….ቀዳሚ እና ዘላለማዊ ናቸዉ ፡፡

በዓለም ሆነ በኢትዮጵያ ታሪክ የማንኛዉም ህዝብ ፣ኃይማኖት እና ማንነት ክብር እና ነፃነት መጠበቅ እና መቀጠል ከጥላቻ ተወላጆች እና አዋላጆች መጠበቅ ትልቁ ተደጋጋሚ ዉድቀት ነዉ ፡፡

ድንጊያ መጀመሪያ ሲመታን  ዕንቅፋት ይባላል ፤ ዳግም ቢመታን/ ቢያነቅፈን  የራሳችን ዕንቅፋቶች ነን፡፡

ቤተ ክርስቲያን ሆነ ኢትዮጵያን በስዉር እና በይፋ ተደፍረዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን አጥርግቢ ተደፍሯል፣ የዕምነት ተቋማት በክፋት እና በዕብሪት ወድመዋል፣ መኢመናን የሕይወት እና አካል ጉዳት ዋጋ ከፍለዋል እየከፈሉ ናቸዉ ፡፡

እሳቱን የሚረጩ እና በዕሳቱ የሚነግዱ በኃላፊነት እና ተጠያቂነት መንፈስ አለመዳኘት የመከራ ጅረት ምንጭ የሆነዉን ህገ- ኢኃዴግ ሳይቋረጥ  ዘላቂ ብሄራዊ ደህንነት ፣ ዕርቅ እና የዜጎች ነፃነት እና ማንነት ይረጋገጣል ብሎ ማሰብ ከንቱ ምኞት  እና “ሳል ይዞ ስርቆት ፤ ቂም ይዞ ፀሎት የለም ፡፡ ”

የአገር አንድነት እና የዜጎች ነፃነት በዕዉነተኛ መሰረት ላይ የሚረጋገጠዉ ዕንቅፋት የሆነዉ ድንጊያ ሲፈነቀል፤ ጋሬጣዉ ሲነቀል  እና ሲቃጠል ብቻ ነዉ ፡፡

ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ዳር ድንበር መከበር እና ለዜጎች አንድነት ፣ ህብረት እና ነፃነት ጠንቅ የዘራዉ እና ኃቅ የተደበቀዉ ይህም ለተገልጋዮች ጋሻ እና መላዋሻ ፤ ለአገሪቷ እና ዜጎቿ መንከሻ እና ማንኮላሻ የሆነዉ የአስራ  ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሠባት የልዩነት እና ሞት አዋጂ ሊቀር፤ ሊታገድ ይገባል፡፡ይህን ከቅርባችን ሡዳን የሽግግር መንግስት ከአልበሽር ውድቀት ማግስት በተግባር የታየ ነዉ ፡፡

ከዚህ ዉጭ በሉዓላዊነት ፣ በአገር ዳር ድንበር ፣ ማንነት ፣ ኃይማኖት…..የደረሰዉ እና ዕየደረሰ ያለዉ መከራ ሁሉ በሰሞነኛ ጫጫታ እና ሁካታ ይቆማል ብሎ ማሰብ  ከሰነፍ እርሻ የሚለይበት አንዳችም ምክነየት  የለም፡፡

በተለይ የኢትዮጵያ ቤ/ክ ክፉዎችን እና ስስታሞችን የህዝቤ እና የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል ለዘመናዊት ኢትዮጵያ የመንግስት አስተዳደር እና አገር ምስረታ ምሳሌ  ሆና  እርሾ እና መሰረት የሆነች  የዕምነት ተቋም እና አማኞች ጥቃት በሃላፊነት ሊወስዱ እና ተጠያቂዉን ማንኛዉም አካል ዋጋ መጠየቅ እና ኃላፊነት በማይስድ የቤተ ክርስቲን አስተዳደር እና አመራር ላይም ራስን ከኃላፊነት ማግለል የህዝብን ስልጣን በህዝብ ጫንቃ ተጣብቀዉ እንደ ትኋን ለሚያደሙት ማንኛዉም የአገሪቷ ተቋማት ዕዉነተኛ ኃይማኖታዊ ኃላፊነት ለምድር ዓለም ሳይሆን ለህዝብ እና አገር ሆኖ ዘላለማዊ ሠማያዊ ህይወት መሆኑን እንዲያሳዩን እንሻለን፡፡

ፀሎት እና ምህላም ዞትር የሚደረግ እንጂ  ኮሽ ባለ ቁጥር ዜጎች ዕምነት እና ኃይማኖት በአገር እና በወገን ላይ መሆኑን እና ከርስቶስን /አለሃን መምሰል የሚጀምረዉ ዕምነትን እና ማንነትን (ነጻነት) በማሳጣት ላይ መዘናጋት እንዲኖር መሆን የለበትም ፡፡

ለዘመናት የነበሩ ሰቆቃወች አሁንም ሲቀጥሉ ሁሉም  መንግስት፣ ህገ………ነገሮች ነበሩ  ግን መከራዉ እና አሳሩን እያስተናገዱ የሚገኙት ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በተለይም ማንት ተኮር ስጋት፣ጥቃት እና ሞት በነበሩበት እንዲቀጥሉ ሆኗል፡፡

“ጠላትን ይቅር ማለት ዕንጂ መርሳትም ሆነ ማመን ሠባዊነትም ፤ዕምነትም አይደለም ፡፡”

“አገርን እና ህዝብን በሚጎዳ ነገር መሳተፍ  በምድርም ሆነ በሰማይ የማይሰረዝ ዠላለማዊ ዕዳ ነዉ ”

“አልፋ እና ኦሜጋ የሆኑት  ኢትዮጵያ እና ህዝቧ  እንደ ሠማይ ክዋክብት   በዝተዉ፤ እንደንጋት ኮከብ ደምቀዉ ፣ እንደ አሳ ነባሪ ገዝፈዉ ፤ እንደዋርካ  ተስፋፍተዉ ለዝንተ ዓለም ይኖራሉ ”፡፡

 ጠላቶች  በጫሩት እና ባዳፈኑት የጥላቻ እና በታችነት  ረመጥ  ይጠፋሉ  ፡፡

በየትኛዉም ዓለም እና ዘመን ነፃነት ዕዉን የሚሆነዉ አንድነት እና ህብረት በማፅናት በተባበረ ክንድ እንጂ ከማንም ምንም በመጠበቅ ዐይደለም፡፡

“አንድነት ኃይል ፤ ኃይልም  ፍኖተ-ድል ነዉ!”

 

ማላጂ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop