December 18, 2021
10 mins read

አጭር ቅኝት: የኦሮሙማ አፈግፍጉ ሴራ እስከ ግማሽ ነጻ መውጣትና ለድርድር እስከ መሞዳሞድ ድረስ (እውነቱ ቢሆን)

በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ ያለህ፡፤

ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአማራና አፋር ልዩ ሀይሎችና ከፋኖ ጋር ሆኖ በጦርነቱ እየተገኙ ላሉት ድሎች ታላቅ ክብርና ምስጋና ይገባዋል፡፡ ዱሮም ቢሆንኮ እንዳይሆን ሆን ተብሎ ሴራ ተሰርቶ ነው እንጅ ወያኔ ኮረምን አልፎ ሊመጣ ፈጽሞ አይችልም ነበር፡፡ የሆነው ሆነና ነገሩ በዚህ ደረጃ እያለ ገና ወልዳያና መርሳ ነጻ ወጡ ተብሎ “የአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጣ” በማለት በመንግስት ኮሙኒኬሽን ሀላፊው መነገሩ (በዚህ ቪድዮ 4፡42 ደቂቃ ላይ ያገኙታል https://www.youtube.com/watch?v=PVE9tQs7F1k) ስህተት ብቻ  ሳይሆን ሆን ተብሎና ታስቦበት በአማራው ላይ እየተሰራ ያለው ደባና ተንኮል ቅጥያ ስለሆነ አንቀበለውም፡፡

ሲሆን ሲሆን መንግስት ተብየው የኦሮሙማ ስብስብ በፓርላማው “ሽብርተኛ” ተብሎ የተሰየመውንና የአገር አውዳሚ ጠላት የሆነውን ወያኔን ከምድረ ገጽ አጥፍቶ የትግራይንም ሆነ መላው የኢትዮጵያን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከወያኔ ስጋት መገላገል ሲገባው የትግራይ ህዝብ በወያኔ እንደታፈነና ይባስ ብሎም የተያዙ የአማራ መሬቶች ሙሉ በሙሉ ነጻ ሳይወጡ ከወያኔ ጋር ለድርድር መሞዳመድ እጅግ አሳፋሪና ዘላቂ ዉጤት የማያመጣ ወራዳ ተግባር ነው፡፡

ሰሜን ወሎ ማለት ወልዳያና መርሳ ቆቦ ብቻ ነውን? በዚያ መስመር በወረራው ስር ያሉት ቆቦ ሮቢት፣ ቆቦ፣ ዋጃ፣ አለማጣ፣ ኮረም ….ወዘተ የትግራይ መሬቶች ናቸው ለማለት ነውን? መንግስት ተብየው “ሰሜን ወሎ ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል” የሚለው የቱና የቱ መሬትና ህዝብ ነው ነጻ የወጣው??  በቦታው ያለው ህዝብስ ምን ይል ይሆን? መንግስት አለኝ ይል ይሆን?? ኢትዮጵያዊ ነኝ ይል ይሆን?? እንዳው በሞቴ ህዝቡ ምን ይሰማው ይሆን?? መንግስትንስ ይህ ያዋጣዋልን?? የአብይ አህመድ ኦሮሙማ መንግስት አካሄድ ሽወዳ መሆኑ ቢገባንም እኛ አማራወች ይህ የግለሰቡ አይን ያወጣ ብልጣብልጥነት አይዋጥልንምና መሞዳሞዱ መዘዝ ክማምጣቱ በፊት ተገቢው እርማት ተደርጎበት የአማራ መሬቶች ሙሉ በሙሉ ከወረራሪው የወያኔ ጦር በአስተማማኝ ሁኔታ ነጻ እስከሚወጡ ድረስ ዉጊያው መቀጠል አለበት የሚል ጽኑ አቋም ይዘናል፡፡

ይህም ማለት በወረራው የተያዙ የአማራ መሬቶች ማለትም ወያኔ “ምእራብ ትግራይ” በሚል ስም ወደ ትግራይ ያካለላቸው የጠገዴ፣ ወልቃይት፣ ማይጠምሪ፣ አዲርቀይ፣ ዳንሻ፣ መተማ፣ ማይካድራ ሁመራና ጠለምት የአማራ መሬቶች እንደዚሁም ወያኔ “ደቡብ ትግራይ” ብሎ አካልሎ እስካሁን ድረስ በወረራ የያዛቸው ቆቦ ሮቢት፣ ቆቦ፣ ዋጃ፣ ራያ ዘቦ፣ ጨርጨር፣ ሰቆጣ ኮረም፣ አለማጣ፣ ዋግ፣ ኦፍላ ሙሉ በሙሉ ነጻ እስካልወጡ ድረስ ” ነጻ ወጥተዋል” ተብሎ መነገሩ ከአንድ አገር “መንግስት ነኝ” ከሚል ሀይል የማይጠበቅ አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡

የአማራ ጠላቶችም ወዳጆችም ማወቅ ያለባቸው አንድ እውነታ አለ፡፤ ይሄውም አማራ ነጻነቱንና መብቱን ተገፍፎ፤ ርስቱንና መሬቱን አስወርሮ ዝም ብሎ የሚቀመጥ ህዝብ አይደለም፡፤ ሁሉም ማንነቱን ፣ ጀግንነቱን፣ ታሪኩንና ነፍጠኛነቱን ጠንቅቀው ያውቁታልና የጊዜ ጉዳይ እንጅ ጠላቶቹን በሙሉ ድባቅ መትቶ ነጻነቱን ማስጠበቅ የሚችል ህዝብ ነው፡፤ ለዚህ ምስክሩ አለም ያወቀው ደማቅና የውጭ ወራሪወችን ድባቅ የመታበት(ከመሰል ወንድም የኢትዮጵያ ጀግኖች ጋር በጋራ) የጀግንነት ታሪኩ ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ወቅትም በአይን የሚታዩ ተግባራቱና የአርበኛነት ውሎወቹ በቂ ማረጋገጫወች ናቸው፡፤የወያኔ ምርኮኞችም እጃችንን ለመከላከያ ሰራዊቱ እንጅ ለአማራ ልዩ ሀይል ወይንም ለፋኖ አንሰጥም ማለታቸው የነፍጠኛ አማራን የየዉጊያ ውሎ ምን አይነት እንደሆነ ማንም ተራ ሰው ይረዳዋል፡፡ የመንግስት ተብየው ብልሹ አካሄድ በዚህ ከቀጠለ የአማራው ህዝብ ቀጣዩ ተጋድሎ ከየት ጀምሮ እንዴት መቀጠል እንዳለበት የአማራው ዝባዊ ሀይል  ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ከውስጡ ከበቀሉ ሆዳሞች ሌላ አማራው እስካሁን የተሸነፈው “ለኢትዮጵያ ሲባል፣ ለአገር አንዲነት ሲባል” የሚሉ ማታለያወችን በጠላቶቹ ሲጋት በመቆየቱ ብቻ ነበር፡፤ አሁን ላይ ግን ጠላቶቹ ይህንኑ ቅጥፈት ሊግቱት የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፤ አማራው አሁን ላይ እንኳን የጠላቶቹን ቅጥፈት ለመጋት ቀርቶ ውሎ ለማደር እንዳይችል አሁን ላይ የደረሰበት የመጨረሻው የህልውና አደጋ ውስጥ ስለገባ ከወደቀበት ሰመመን ነቅቶ በጀግኖቹ  ልጆቹ ማለትም ፋኖወችና ልዩ ሀይሉየጎበዝ አለቃ እንዳው በጥቅሉ በአማራ ህዝባዊ ሀይል አማካይነት ህዝቡ ነቅንቆ በቁጣ በመነሳቱ ህልውናውን ለማረጋገጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ከሁሉ አስቀድሞ  የመኖር ዋስትና የነሱትን ጠላቶቹን በቁርጠኝነት በመደምሰስ በቅድሚያ ራሱን ነጻ ካወጣ  በኋላ ቀጥሎም ለሚወዳት እናት አገሩ በኢትዮጵያ አንዲነትና ጠንካራ አገርነት ከሚያምኑ መሰል ሀይሎች ጋር ጠንክሮ በጋራ ለመቆም ቆርጦ ተነስቷል፡፡

የአብይ አህመድ የኦሮሙማ ተረኛ መንግስት በሁለት እግሩ ያልቆመ መንግስት ነው፡፡ በዚሁ ላይ የሚሰራው ስራ ሁሉ አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ እንዲሆን እያደረገው ነው፡፡ አማራን ለመጉዳት ብሎ “በአፈግፍጉ ፖለቲካ” እስከደብረ በርሀን ድረስ አማራው እንዲደቅቅ ያስደረገው የአብይ አህመድ መንግስት ገና ተቆፍሮ የሚወጣ ብዙ ጉድ አለበት፡፤ አሁን ለጊዜውም ቢሆን መንግስት ቆሞ ያለው ሌላ በማንም ሳይሆን በሆዳም አማራወች ትከሻ ላይ ብቻ ነው፡፡ ከአማራው ህዝብ አብራክ ወጥተውና ለሆዳቸው ተሽጠው አብይን ተሸክመው በማገልገል ላይ ባሉት በእነደመቀ መኮንን ትከሻ በአንድ እግሩ ብቻ ተንጠጥሎ የሚገኘው የአብይ አህመድ ኦሮሙማ ስብስብ ቆም ብሎ ቢያስብና ወደ እውነታው ቢመለስ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ህይወቱን ማራዘም ይችል ይሆናል፡፡ አለበለዚያ የአማራ ህዝብን እንዲህ ሜዳ ላይ አስጥቶ የስልጣኑ መረማመጃ ለማድረግ በዚሁ ከቀጠለና በዚሁ መነሾም ይህችው አንድ እግሩ ካንዳለጠችው አለቀለት ማለት ነው፡፤ ከዚያ በኋላ መነሻም መፈወሻም መንገድ የለውም፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop