ኢትዮጵያ ጠልነቱን በተግባር ያሳየው አሸባሪው ህወሃት በደሴ ሙዚየም ሊተኩ የማይችሉ ቅርሶችን አውድሟል፣ ዘርፏል

268252373 3092428664332925 6264835586055153522 nኢትዮጵያ ጠልነቱን በተግባር ያሳየው አሸባሪው ህወሃት በደሴ ሙዚየም ሊተኩ የማይችሉ ቅርሶችን አውድሟል፣ ዘርፏል።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል ድረስ እንወዳለን ያለበትን እኩይ ህልሙን ለማሳካት ያልወጣው ዳገት፣ ያልወረደው ቁልቁለት፣ ያልፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት፣ ያልሰራው ወንጀል የለም።

በወረራ በገባበት አካባቢ ሁሉ ንጹሀንን ገድሏል፣ ሴት ደፍሯል፣ ሀብትና ንብረት ዘርፏል፣ የተረፈውን ከጥቅም ውጭ አድርጎ አውድሟል።

የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያ እሱ እንዳለው በአንድ ጀምበር ትጠፋ ይመስል የትውልድ መገንቢያ ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎችን፣ የጤና ተቋማትን፣ ኢትዮጵያ ትናንት እንዲህ ነበረች ብለው የሚያስረዱበትን ቅርስ እያወደመ አጥፍቷል።

267985549 3092428794332912 8958570168144829444 n

ከመልካምነት ይልቅ ክፋት፣ ከልማት ይልቅ ጥፋት፣ ከመስራት ይልቅ ማፍረስ የሚቀናቸው የሽብር ቡድኑ የጥፋት እጆች እድሜ ጠገቡን የደሴ ሙዚየም በማውደም ወደ ነበርነት ቀይረውታል።

267497161 3092428964332895 7993649415448730873 n

የደሴ ሙዚየም አስጎብኝ ወጣት ፍሰሀ ፈለቀ እንዳለው ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዓመት በላይ ያስቆጠሩ የአርኪኦሎጂ ግኝቶችን ጨምሮ ውድ የሆኑ የታሪክ ቅርሶችን የያዘ ሙዚየም ነው።

ሙዚየሙ የታሪክ፣ የአርኪኦሎጂ፣ ኢትኖግራፊክ መሳሪያዎች ያሉበት ኢትዮጵያዊ ማንነትን የሚገልጹ በተለይ የወሎን ማህበረሰብ ሁነት የሚያንጸባርቁ ቅርሶች እንደነበሩበት ገልጿል።

 

ይሁን እንጂ ታሪክን በማጥፋት ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳው ሀይል የጥፋት በትሩን በደሴ ሙዚየም ላይ አሳርፏል ብሏል።

ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በ1941 ዓ.ም ከእንግሊዟ ንግስት ኤልዛቤጥ በስጦታ የተበረከተላቸው ከብር የተሰራ ሻሞላ/ሰይፍ እንዲሁም በአድዋ ጦርነት ወቅት ዳግማዊ አፄ ሚኒልክ ይጠቀሙበት የነበረው የጦር ሜዳ መነጽር እንዲሁም ሌሎች ውድ ቅርሶች ተዘርፈዋል፣ የቀሩት ጥቅም እንዳይሰጡ ተደርገው ወድመዋል ብሏል።

269042630 3092428887666236 2907954282241836963 nየደሴ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሰይድ አራጋው የሽብር ቡድኑ የኢትዮጵያን የማንነት መገለጫ የሆኑ ቅርሶችን በማውደም ኢትዮጵያ ጠልነቱን በተግባር አሳይቷል ብለዋል።

በደሴ ሙዚየም ለትውልድ ታሪክ የምናስተላልፍባቸው በገንዘብ የማይተኩ ውድ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ተዘርፈዋል፣ የማይንቀሳቀሱት ከጥቅም ውጭ ሆነዋል ብለዋል።

አሸባሪው ህወሓት ቅርሶቹን ከደበቀበት ቦታ መመለስ ካልተቻለ ሊተኩ አይችሉም ብለዋል።

“ለኢትዮጵያ ፍቅር ለጃንሆይ ክብር” በሚል ከእንግሊዝ ንግስት የተበረከተው ሰይፍ፣ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ አድዋ ላይ የተዋጉበት የጦር ጎራዴ፣ አፄ ቴዎድሮስ ራሳቸውን ያጠፉበት የሚመስል ሽጉጥ ሊተኩ የማይችሉ ቅርሶች ናቸው ብለዋል።

ሌላው የውድመትና ዘረፋ ኢላማ የሆነው በ1938 ዓ.ም የተመሰረተው የአስፋውወሰን ኃይለስላሴ ቤተ መንግስት የነበረውና ደሴ የሚገኘው የመርሆ ቤተ መንግስት ነው።

የመርሆ ቤተ መንግስት አስጎብኚ አቶ መስፍን ሞላ ታሪክን የሚገልጹ ቅርሶች፣ ሰነዶችና ሌሎች ማስረጃዎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ገልጸዋል።

“እኔ በአፄ ኃይለስላሴም በደርግም ኖሬያለሁ እንደዚህ አይነት አስከፊ ውድመት አይቼ አላውቅም” የሚሉት አቶ መስፍን ጎብኝዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ቅርሶች በሙሉ መዘረፋቸውን ገልጸዋል።

የንጉስ ሚካኤል ቤተ መንግስት አስተዳዳሪ አቶ መጂድ ኢማም ቤተ መንግስቱ 1875 ዓ.ም የተሰራ የወሎን ህዝብ ታሪክ የሚያንጸባርቅ የታሪክ ማስረጃና ሀብት ነው ብለዋል።

ይሁን እንጂ ቤተ መንግስቱ በየጊዜው እድሳት ስለሚያስፈልገው ለእድሳት የተገዙ ከአምስት ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ሀብት በቡድኑ አማካኝነት ዘረፋና ውድመት ተፈጽሞባቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የቤተ መንግስቱን በርና መስኮት በመሰባበር ታሪካዊ ይዘቱን እንዲያጣ አድርገውታል ብለዋል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

ታህሳስ 08 ቀን 2014 (ኢዜአ)

3 Comments

  1. Where was the so called EDF, Amhara Leyou Haile and Fano and the mayor? All parties including the PM office the Ethiopian government is responsible for all these mess. You invited a terrorist group to come and loot your country and now you’re crying out loud. I’ll bet you this is the beginning of woyanes strategy to terrorize and destabilize Amhara region. Unless all concerned parties involved to find a solution to this problem, the cycle of violence in Amhara region will continue. Act fast!

  2. ወያኔ ማለት ከዲያብሎስ የከፋ ጸላይ ነው። ለወያኔ የሰው ልጅ ህይወትና ሃብት መጥፋት ምንም አይነት ስሜት አይፈጥርባቸውም። የደነዘዙ፤ የሚያደርጉትን የማያውቁ፤ ለውጭ ሃይሎች ያደሩ፤ ዝምታንና መታገስን እንደ ሽንፈት የሚወስድ የጅል ክምችት ናቸው። ገና ከጅምራቸው ኢትዮጵያዊነትን መጥላትና ማስጠላት የራሳቸው መመሪያ አድርገው የተነሱት የዘር ሰካሪዎቹ ወያኔዎች ከእንስ ሳ ጎን እንጂ ከሰው ተራ የሚሰለፉ አይደሉም። አንድ በአዲስ አበባ የሚኖር የትግራይ ተወላጅ እንባ እየተናነቀው እኔ የትግራይ ልጅ በመሆኔ አፈርኩ፤ አንገታችን በእነዚህ ከይሲዎች ተደፋ በማለት ሲናገር አዳምጫለሁ። ችግሩ ይህ እንደሚመጣ ገና በስልጣን ላይ ወያኔ እያለ ሁሉ ለምን እንዳልታያቸው ነው። የግፍ ጣራ ሰማይ ነክቶ ሰው በሰው ላይ የሚሸናበት፤ የሰው ጥፍር የሚወልቅበት፤ ሶዶማዊው ተግባር የሚፈጸምበት፤ ሰው ታፍኖ ከነ ህይወቱ በትግራይ ምድር የሚቀበርበት (ባዶ ስድስት) ና ሌሎችም ልዪ ልዪ እስር ቤቶች ይህን የትግራይ ወገናችን ሊያነቃው በተገባ ነበር። ያ ግን አልሆነም። አሁን ለይቶላቸው በአሜሪካ ደጋፊነት ሽዋ ድረስ ወረራ ፈጽመው እንደ ቅጠል የሚረግፉት የወያኔ ቡችሎች የዓለምን የፓለቲካ ንፋስ ያላገናዘበ አሜሪካ ብቻ ያዘው ጥለፈው እንደምትልና ለእነርሱ እንደምትደርስላቸው በማሰብ በወገናቸው ላይ ዘምተው ያደረሱትና በማድረስ ላይ ያሉት ሰቆቃ ሰማየ ሰማያትን አልፏል። እነዚህ የቀን ጅቦች ትግራይን ታላቅ እናረጋለን በማለት በሰከረ የፓለቲካ ቱልቱላ የፈጸሙት በደል ዘንተ ዓለም እውነተኛ ለሆነ ኢትዮጵያዊ አይረሳም። የወሎ ህዝብ ሰው አፍቃሪ፤ ሃገሩን የሚወድ በመሆኑ ሆን ተብሎ እንዲፈናቀልና የስነ ልቦና ውድቀት እንዲደርስበት ፋሽሽታዊ ግፍ ተፈጽሞበታል። የአፋር ወገኖቻችን በእሳት ያቃጠለው ወያኔና ግብር አበሮቹ፤ በጎንደር እንጀራ አቅርባ የመገበቻቸውን እናት በመድፈር ብሎ መግደል ምን ያህል የሰው ፍጡሮች እንዳልሆኑ ያሳያል። ለነገሩ በሃሺሽ የደነዘዘው ይህ የወያኔ ገዳይ መንጋ ሊቆም የሚችለው ሲገድል ብቻ መሆኑ አሁን የተገኙ ድሎች ያሳያሉ።
    በምንም ሂሳብ ወያኔና ወያኔ ቀመስ የትግራይ ልጆች አይታመኑም። ላስረዳ። ይህ የመከራ ወያኔ ከተፈጠረ በህዋላ የመጣ መከራ አርጋችሁ የምታዪ ስታችሁሃል። እርግጥ ነው ነገሩ የተጋጋለው ወያኔና ሻቢያ የጣምራ ጦር ሆነው መዋጋት ከጀመሩ በህዋላ ነው። አማራ ጠልነታቸውና ሃገር አፍራሽነታቸው ግን ከዘመናት በፊት የተጀመረ ለመሆኑ መረጃዎች አሉ። ይህን ለማድረግ ይጠቀሙባቸው ከነበሩትና አሁንም ከሚጠቀሙባቸው የዘር ማጥፋት ዘዴዎች አንድ ሰውን መግደል፤ የሃሰት መረጃ በማቀበል እንዲታሰሩና እንዲንገላቱ ማድረግ፤ በትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በውጤታቸው በመጫን የነቁ የአማራ ተማሪዎችን በዚህም በዚያም በማዋከብ ድምጥማጣቸውን ማጥፋት እንደነበር በጭልፋ ከተገኘው ሴራ የተወሰድ ሃሳቦች ያስረዳሉ። ወያኔ የእምነት ቤቶችን ማቃጠሉ፤ ማራከሱ፤ መጽሃፍትን ማውደሙ እንግዳ ነገር አይደለም። እነዚህ እኮ ታቦት የሚሸጡ በአልባኒያ የከሰረ የኮሚኒስት እይታ አይናቸው የተሸፈነ ከራሳቸው ውጭ ሌላው ዓለም ሁሉ የገማ ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው። የትግራይ ቲቪ አሁን የሚያስተላልፈውን ዜናና የፕሮፓጋንዳ ወሬ ላዳመጠ የጀርመኑ ሂትለር ያሰራጭ ከነበረው አይለይም። እየተሸነፉ ጀጋኑ ማለት፤ እየሞተበት ደመሰስን ብሎ መደንፋት፤ መብረቃዊው ጥቃታ አሁን በራሳቸው ላይ የውዥንብርና ዶፍ ሲያወርድባቸው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተፈጸመብን ይላሉ። የሚገርም ነው። የትግራይ ህዝብ ግን ምን አደነዘዘው? ውጭ ያሉትን ደንቆሮዎች እንርሳቸው። እነርሱ ሶፋ ላይ ተቀምጠውና ያማረ ኑሮ እየኖሩ እቃ እቃ ተጫውተው ያልጠገቡ የትግራይ ልጆች እሳት ውስጥ መማገድ ይህ እውነት ለታላቋ ትግራይ ህልመኞች ተስፋ ነውን? ስዬ አብርሃና ወንድሙ አሁን በዚህም በዚያም የጥፋት ሃይሎች እየተደገፉ የትግራይ ልጆችን ወደ እሳት መማገድ ያቀባብራል? አሜሪካ ለትግራይ ህዝብ አይገዳትም። ለእኛ ያልታየን ለእነርሱ ግን ቁልጭ ብሎ የታያቸው አንድ ጥቅም በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ አለ። ያለበለዚያ እግሬ አውጭ ብሎ ከአፍጋኒስታን የፈረጠጠው የአሜሪካ ጦር አሁን ሌላ ግጭት ውስጥ የሚገባበት ጉዳይ የለም። በስመ ዲሞክራሲ፤ በሰው ልጆች መብት ጉዳይ ያገባናል የሚሉት አሜሪካና ተከታዪቿ መቼ ይሆን ቆም ብለው ዓለም እንደተለወጠ የሚረድት? ወያኔ የውጭ ሃይሎች ጆኒያ ተሸካሚ ኩሊ ነው። ተላላኪ። ያን መንግስት ነው አሜሪካኖች መልሰው አዲስ አበባ ለማስገባት በሬ ወለደ ወሬ ሲነዙ የከረሙት። አይ የአሜሪካ ዲሞክራሲ በአፍንጫዬ ይውጣ። ሊቢይ፤ ኢራቅ፤ አፍጋኒስታን፤ የመንና ሶርያ ይመስክሩ። ያፈረሱት እነርሱ ናቸው። አሁን ግልጽ ያልሆነልኝ ነገር ወያኔን ወደ ስልጣን ከመመለስ ባሻገር አሜሪካ ኢትዮጵያ ውስጥ የምታተርፈው ምን ጉድ ይኖር? እንዳለ ግን እርግጠኛ ነኝ።
    ወያኔዎች እናታቸውን ገቢያ አውጥተው ይሸጣሉ። ለዚያም ነው አደይ ኢትዮጵያን ለውጭ ሃሎች በማደር በመናድ ላይ የሚገኙት። አንድ ጊዜ በወያኔ ውስጥ የገባ ጭንቅላቱ የተበረዘ በመሆኑ ለንስሃም ሆነ ለኑዛዜ ጊዜ የለውም። የእሳት ራት ማለት ነው። ተመልሶ መማገድ። እብደት ከዚህ በላይ ምን አለ። አሁን በወገናቸው አስከሬን ላይ የሚጨፍሩት የወያኔ ወታደሮች ከዚህ የእርስ በርስ እልቂት ተርፈው እንኳን ሙሉ ሰው መሆን አይችሉም። የሰው ደም ያፈሰሰ ደሙ ይፈሳል። ተቅበዝባዥ ነው። ለዚያም ተንበርክኮ ተወይኝ፤ ማርልኝ፤ እያለ የተጨፈጨፈ የንጽሃን ደም። እነዚህ የጦር ሜዳ ትራፊዎች ለትግራይ ህዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ አይጠቅሙም። የቅዥትና የመከራ ትራፊዎች ናቸውና። ልባቸው፤ ስነ እይታቸው ተናግቷል። ሰውና እንስሳን ተኩሰው ገለዋል። ምንም አይነት ህክምና አያድናቸውም። የእነዚያ ለህይወታቸው እየለመኑ የተረሸኑት ሰዎች ደም ጆሮአቸው ላይ ያስተጋባል። ህሊና ቢሶች ህሊና እንደጎደላቸው ይሞታሉ። በወሎ፤ በአፋር፤ በጎንደርና በሽዋ የተደረገው በደል ዘጋቢ ያጣ ነው። ብዙ ግፍ ተፈጥሮአል። አሁን እንሆ ተመድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሆነውን እፈትሻለሁ ብሏል። እኮ ሂዶ ማን ምን እንዳደረገ ታያላችሁ። የትግራይ ወራሪ ሃይሎች ጋር ቂጥ ገጥማችሁ ግፍን እንዳላያችሁና እንዳልሰማችሁ አይታችሁ፤ ለእርዳታ የሄድ ካሚዎኖችን እንኳን ጠፉብን ተወሰድብን ሳይመለሱ ቀሩ አለማለታችሁ የሴራውን ጥልቀትና የእናንተን በሰው ደም መነገድ ያሳያል። የምናለቅሰው አብረን ነው። ጣሊያን ኢትዮጵያን ወሮ የመርዝ ጋዝ ሲጠቀም የንጉሱን የድረሱልኝ ጥሪ የናቁት ሃገሮች በጀርመኖች መልካም ክፍያ ተከፍሎአቸዋል። አሁንስ ማን ያውቃል? ሰሜን ኮሪያ፤ በራሽያና በዪክሬን፤ በኢራንና በአሜሪካ/ በእስራኤል፤ በቱርክ በኩልና በሌሎች የፓለቲካ ጭስ በሚጨስባቸው አካባቢዎች እሳቱ ቦግ ይልና የሚልሰውን ልሶ ያልፋል። የጥቁር ህዝቦች እንባና ሁሌ ምጽዋተኛ መሆን የሚያቆምበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። ወያኔ ጸረ ሰው፤ ጸረ እንስሳ፤ ጸረ አማራ ድርጅት ነው። ሰው ነቅቶ ራሱን አድራጅቶ እነዚህን አውሬዎች አሁንም ወደፊትም መፋለም እስካልቻለ ድረስ ወራሪው ሃይል ተመልሶ መምጣቱ አይቀሬ ነው። በዘሩና በቋንቋው የሰከረ እንደ ወያኔ በምድር ላይ ማንም የለም።
    ማሳሰቢያ – የአማራ ክልል መሪዎች በፋኖ ላይ ተጽኖ ማድረጋችሁን አቁሙ። ይልቁን እንዴት አድርጋችሁ ይህን ለመሰዋት ዝግጅ የሆነ ሃይል አሁንና ወደፊት መጠቀም እንደሚቻል የጋራ ስትራተጂ በማውጣት ለዛሬም ሆነ ለወደፊት የሃገሪቱን የመከላከያ ሃይሎች ማገዝ እንደሚችል ማሰብ ተገቢ ነው። ፋኖ የአማራ ህዝብ ደጀን ነው። ማሰልጠን፤ ማስታጠቅ፤ የእዝ ሰንሰለቱን የማጥበቅ፤ የቀጥታና የተጓዳኝ ግንኙነቱን ማጠናከር ሲገባችሁ ማፈንና እርምጃቸውን ማደናቀፍ ወያኔአዊ እይታ ነው። ይቁም። የፋኖ አመራሮችም ለህግ የሚገዙ፤ ደመ ግንፍሎች ሳይሆኑ የሰከኑ፤ በመረጃ ላይ የሚመረኮዙ መሆን አለባቸው። ዝም ብሎ በፈጠራ ወሬ የክልሉንም ሆነ የሃገሪቱን አመራሮች መዘንጠሉ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳት አለው። መረጃ የሁሉ ነገር መዝጊያ ነው። መተባበር እርምጃን ያፈጥናል። ተደማመጡ። በቃኝ!

  3. All of the attributes accorded to the TPLF dragons were well known. Nothing new. So, “Who let the dogs/ dragons out?” should be the intelligent question to ask – once the dragons were holed in the caves of lowland Tembien. And, “Why?”.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.