“አብረን ከሮጥን እርሱን አስቀድመዋለው”” ሲል ጀግናው የኢትዮጵያ አትሌት ሀይሌ ገብረ ሥላሴ ያወደሰው በዶክተር ጥላሁን ገሠሠ ከፍተኛ የክብር ቦታ የሚሰጠው ተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ “”እውነትን በዜማ የሚናገር የሕዝብ ልጅ”” ሲሉ ብዙሀኖች ያወድሱታል:: ድምጻዊ: የዜናማና
የግጥም ደራሲ በመሆን ተፈጥሮ ሁሉን አሟልታ የሰጠችው የሚባልለት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ “ሰው ገድለሀል ተብሎ በተጠረጠበት “ወንጀል” ቴዲ አፍሮ ጥፋተኛ ተባለ። ፍርዱ ዲሰምበር 5 የሚሰጥ ሲሆን እና የዲሴምበር አንዱን ችሎት በገጽ 3 ላይ ይከታተሉ።
“”የመለስ አስተዳደር ድራማ ሲሰራ አሰራሩን አያውቅበትም”” ነበር ያለችው ችሎቱን የተከታተለች አንዲት ወጣት:: “”ድራማቸው ሁሉ የሕጻናት ስለሆነ ሁልጊዜ ይጋለጣሉ”” የምትለው ይህችው ወጣት ከዲሴምበር አንዱ የቴዲ ችሎት በፊት በሕዝቡ ላይ እየተደረገ የነበረው ነገር ሁሉ በቴዲ ላይ ቀድሞ የተጻፈ ነገር እንደሚፈረድበት ያስታወቀ ነበር ትላለች::
ከጥቂት ቀናት በፊት መሰብሰብ የተከላከለው ሕዝባችን በመስቀል አደባባይ ለታላቁ ሩጫ በተሰበሰበት ወቅት ”ቴዲ ኦባማ; መለስ አሳማ”” እያለ እየዘፈነ ብሶቱን ሲያሰማ የቴዲን ቲሸርት የለበሰ; ስለቴዲ ጮክ ብሎ የተናገረ አይን እና ጆሮ በሌላቸው የፌደራል ፖሊሶች ተወግረው እስር ቤት አድረው; ፈርመው መለቀቃቸው በአንድ ”ሰውን ገጭተሀል ለተባለ እስረኛ” የማይገባ ነገር ነበር::
ድራማው ይህ ነው የምትለው ወጣት ከጥቂት ቀናት በፊት በኢንጂነር ሀይሉ ሻውል የሚመራው የመኢአድ ፓርቲ በአደባባይ በአይሱዙ መኪና የቴዲ አፍሮን ‘ጃ ያስተሰርያል” ሙዚቃ ከፍቶ ስለ ሰላማዊ ትግል በመቀስቀሱ ዘፈኑን ከፍተው መቀስቀስ እንደማይችሉ ፖሊሶች ገልጸው ቅሰቀሳውን ያፈኑ ሲሆን ከቀናት በሗላ ያቺው ለቅስቀሳ የወጣችው አይሱዙ መኪና የቴዲ ዘፈኖች ስለተከፈተና ስለተቀሰቀሰባት ብቻ መኪናው ታስሯል:: እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች እንዲሁም ቴዲ ችሎት በቀረበ ቁጥር ችሎቱን የሚከታተል ሰው ካለፈቃዱ ቪዲዮ መቀረጹ አሁንም በትራፊክ ሕግ መጣስ ለተከሰሰ የማይገባ ነው ትላለች ይህችው ወጣት:: እነዚህ እና ሌሎች ምክንያቶች ተደማምረው በቴዲ ላይ የቀረበው ክስ ሙሉ በሙሉ ፖለቲካዊ ይዘት እንዳላቸው ትናገራለች::
ዲሴምበር 1 በዋለው ችሎት ላይ የሕወሐት አባሉ ዳኛ አቶ ልኡል ገብረማርያም ካለምንም ማገናዘብ ግልጽ የሆኑ ማስረጃዎችን በቅንነት ባለመተርጎም በአርቲስቱ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ወስነዋል:: እኚህ ዳኛ በቴዲ ላይ ለመፍረድ ከተቀየሩበት ችሎት መምጣታቸው ሌላው ድራማ ሲሆን ዳኛው ከዚህ ቀደም በመንግስት ላይ ጥቂት ተቃውሞ ባላቸው ሰዎች ላይ በአንካሳው ሕግ በመፍረድ ይታወቃሉ:: በውስጥ ገጾች ላይ ይመልከቱ:: አርብ ዲሴምበር 5 ፍርድ የሚጠብቀው ቴዲ በፍርድ ቤቱ የጥፋት ማቅለያ አቅርብ ቢባልም “”በሐቅ ለማይፈርድ ፍርድ ቤት ምንም አይነት የቅጣት ማቀለያ ከዚህ በላይ የለኝም:: እውነት ምንጊዜም ታፍና አትቀርም እኔ ንጹህ ሰው ነኝ’፤ ማንንም ሰው አልገደልኩም’; ብሏል:: በፖሊስ ታጅቦ እየሄደ ባለበት ወቅትም ለተሰበሰበው ሕዝብ ‘ከ እንግዲህ ያላችሁኝ እናንተ እና ፈጣሪ ብቻ ናችሁ” ሲል መናገሩን ሪፖርተራችን ከአ.አ ዘግቧል።ቴዲ አፍሮ ላይ ለመፍረድ በአንካሳው ሕግ የተቀመጡት አቶ ልኡል ጥፋት ማቀለያ ቀረበም አልቀረበም አርብ እለት የተጻፈላቸውን ፍርድ ለቴዲ ማንበባቸው አይቀሬ ነው:: ብዙዎች ቴዲ “”17 መርፌ ብሎ ዘፍኖ 17 ዐመት ሊፈርዱበት ነው”” እያሉ እንደቀልድ ቢጤ ጣል ቢያደርጉም ልጁ በተጠቀሰበት አንቀጽ ከ5 እስከ 15 ዐመት ይፈርዱበታል ተብሎ ይጠበቃል::
የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ያነጋገራቸው የፖለቲካ ምሁራን እንደሚሉት በቴዲ ላይ እየደረሰው ያለው ነገር ነገ ማንም ዘፋኝ ተነስቶ ሰለፖለቲካ እንዳይዘፍን እና መንግስትን በዘፈን እንዳይቃወም ታቅዶ የተደረገ ነው:: ሆኖም ግን ይላሉ እነዚሁ ምሁራን ”ሆኖም ግን በልጁ ላይ የተፈረደው ፍርድ ሕዝቡን የበለጠ በስርአቱ ላይ እንዲነሳና የትግሉን መንፈስ ያጠናክራል”” ይላሉ:: በሌላ በኩል ቴዲ አፍሮ ወንጀሉን ሰርቷል ብለው የሚያምኑ ወገኖች ”የፈሰሰው የደሀ ነፍስ እስከሆነ ድረስ ቴዲም እንደማንኛውም ሰው ፍርዱን መቀበል አለበት::” ይላሉ::
ምስክሮች ሟች ደጉ ይበልጣል አስከሬኑ ለምርመራ ምኒልክ ሆስፒታል በጥቅምት 22 ቀን 1999 ዓ.ም. ገብቶ፣ በጥቅምት 23 ቀን 1999 ዓ.ም. ምርመራ እንደተደረገለት የሚገልጸውን ማስረጃ ቢሰጡም; (አርቲስቱ ከውጭ ሀገር የገባው ጥቅምት 23 ነው) ፖሊስ ሰነዱን በሀይል ደጉ ይበልጣል የሞተው ጥቅምት 23 እንደሆነና የሬሳ ምርመራ የተደረገለትም በ24 እንደሆነ አስደርጎ ሰነዱን ማስቀየሩ በግልጽ በፍርድ ቤት ቢመሰከርም; ዳኛው ልኡል ነውና ጥፋተኛ ነህ ብሎታል:: ቴዲ አፍሮ አርብ የሚፈርድበትን ፍርድ ለማወቅ ወደ ዘ-ሀበሻ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ከአርብ ከሰአት ጀምሮ ብትደውሉ መረጃ እንሰጣችሗለን::
በሌላ በዘገባው አቃቤ ሕጉ ማነው? ዳኛው ልዑል ገ/ማርያምስ ማነው? ከዳኛው የሚጠበቅ ፍርድ ተሰጠ ወይ? የሚሉ ምርጥ እና ወቅታዊ ሁሉን አቀፍ ሚዛናዊ ዘገባ ይዘናል ይከታተሉን::
የቴዲ አፍሮ ክስ አቃቤ ሕግ ማነው?
በሻሸመኔ ከተማ ተወልዶ የመጀመሪያ
ትምህርቱን እዛው አጠናቆ ከ7ኛ
እና 8ኛ ክፍል በሗላ
ወደ አሩሲ ያመራው ይህ ሰው
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአሰላ ከተማ
ተከታትሏል:: ከዛም በ1992 ከአዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት የተመረቀው የቴዲ
አፍሮን ክስ በአቃቢ ሕግነት የሚመራው ፈቃዱ
ጸጋ ነው:: አቃቤ ህጉ የቴዲ አፍሮን
ክስ ማን ነው የሠራው?? በሚል
በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ልዩ ዘጋቢ ለቀረበለት
ጥያቄ ”ክሱን እኔ አላዘጋጀሁትም::
ክስ በፖሊስ ተዘጋጅቶ
ለአቃቤ ሕግ ይቀርባል::
አቃቤ ህግ ያስከስሳል አ
ያስከስስም የሚለውን
መርምሮ ለፍርድ ቤት
ያቀርባል::” ብሏል::
ቴዲ አፍሮ በተከሰ
ሰበት ወንጀል ዓይነት
ከዚህ በፊት ታዋቂው
አትሌት ተስፋዬ
ቶላ በዋስ ተለቆ
ጉዳዩን በውጭ ሆኖ
ሲከታተል ነበር;
አሁን ለምን ቴዲ አፍሮ
ለምን ታስሮ እንዲከታተል
ሆነ? በሚል ለቀረበላቸው
ጥያቄ አቃቤ ህጉ ”በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ተስፋዬ ቶላ መንጃ ፈቃድ ነበረው” በሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል:: ተባባሪ ዘጋቢያችን ለአቃቤ ህጉ ከዚህ በፊት በዚሁ ክስ ቴዲ አፍሮ በ15 ሺህ ብር ዋስ መለቀቁን አስታውሶ ለምን ያን ጊዜ ተለቆ አሁን ይታሰራል? የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር:: አቃቤ ህግ ፈቃደ ጸጋ ”አዎ ከዚህ በፊት በዋስትና ተለቆ ነበር:: ከአሁኑ ጋር ልዩነት አለው:: ያኔ ገና የፖሊስ ምርመራ ላይ ነበር:: ምርመራው ካላለቀና ጉዳዩ ተጠርጣሪውን ያስከስሰዋል ወይስ አያስከስሰውም የሚለው ጥያቄ ገና ካልተወሰነ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጥሮ ይሰጣል:: በዚያ ጊዜ ተጠርጣሪው በዋስትና ይለቀቃል ወይም አይለቀቅም የቴዲ ቁርጥ ቀን… ከገጽ 1 የዞረ
ተብሎም በፍርድ ቤት ይወሰናል:: ጉዳዩ በፖሊስ ነው የሚከናወነው:: በዋስትና ተለቀቀ ማለት ጉዳዩ የሚያስከስስ ሆኖ ከተገኘ ወደ ተከሰሰበት ቦታ እንዲቀርብ ዋስ ጠራ ማለት ነው:: ከዚያ በሗላ ምርመራው አልቆ ወደ አቃቤ ሕግ ይመጣል:: ፖሊሶች በምን እንደሚከሰስ ስለማያውቁት ነው ዋስትና አስጠርተው የሚለቁት:: አቃቤ ህግ ነው ሁሉን መርምሮ ከህግ ጋር አያይዞ የሚከሰው:: በተጠቀሰው አንቀጽም አቃቤ ሕግ ዋስትና እንዲከለከል ይጠይቃል” ብለዋል::
አዲስ የወጣው የኢትዮጵያ የትራፊክ ሕግ ከሁለት ሰው በላይ ገጭቶ በመግደል የተጠረጠረ ወይም በመጠጥ ሀይል ሲያሽከረክር ሰው የገደለ ሰው የዋስትና መብቱ ይከለከላል ይላል:: ቴዲ የተጠረጠረው በአንድ ሰው መግደል ነውና ለምን በዋስ እንዲከታተል አልተደረገም ለሚለው ጥያቄ ”ዋስትና የሚያስከለክለውም የሚፈቅደውም ሕጉ ነው:: እኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን ላይ የጠቀስነው የወንጀል ሕግ 543 ንኡስ ቁጥር 3 ነው:: አራት ነገሮች ተጠቅሰዋል:: ከአንድ በላይ ከገደለ ወይም ግልጽ የሆነ ደንብ ተላለፎ ወንጀሉን ከፈጸመ ወይም የሚያሰክር ነገር ወሶድ ወንጀሉን ከፈጸመ ወይም የሚያፈዙ እጾችን ወስዶ ወንጀሉን ከፈጸመ የሚሉ ናቸው – 4ቱ ነጥቦች:: ከእነዚህ መካከል አንዱን የሚያሟላ ከሆነ ዋስትና ያስከለክላል:: በቴዎድሮስ ላይ የጠቀስነው ወንጀል ግልጽ የሆነ ደንብ ተላልፏል ብለን ነው:: መኪና ለማሽከርከር ከሚመለከተው ባለስልጣን መ/ቤት መንጃ ፈቃድ ሊሰጠው ይገባል:: ግን መንጃፈቃድ አልተሰጠውም ተብለናል:: ስለዚህ ያለመንጃ ፈቃድ ነው የትራፊክን ደንብ በማፍረስ የተከሰሰው:: ይህ ወንጀል ከ5 እስከ 10 ዓመት ያስፈርዳል:: የሰው ሕይወት ያለፈበት ደግሞ እስከ 15 ዓመት ያስቀጣል:: ስለዚህ ዋስትና ያከለከለው ዳኛው; አቃቤ ህጉ አይደሉም:: ህጉ ነው” ሲሉ አብራርተዋል::
ከፍርዱ ቀን አስቀድሞ የቴዲ አፍሮ ፍርድ ደርሷል:: ለመጨረሻ ቀጠሮ ተቀጥሯል ከፍርዱ ምን ይጠብቃሉ የሚል ጥያቄ ለአቃቤ ህጉ ቀርቦላቸዋል:: ”አድናቂዎቹም ሆኖ ሌሎች ሰዎች ማየት ያለባቸው ነገር አለ:: ቴዎድሮስ ታዋቂ ነው; ግን ታዋቂ ሰው ወንጀል አይሰራም የሚል ነገር የለም:: ይሄንን ወንጀል ሆነ ብሎ ፈጽሞታል የተባለ አይደለም; በቸልተኝነት ፈጽሞታል ነው የተባለው:: ቸልተኝነት ደግሞ ከሰው ባህሪይ የሚመጣ ነገር ነው:: ነገር ግን ቸልተኛ ላለመሆን መሞከር ነበረበት ነው; የክሱ ሀሳብ:: በእርግጥ በሁሉም ነገር ቸልተኛ ስለሆነ አይቀጣም ግን በቸልተኝነት ያደረሰው ጉዳት ይታያል:: ዋናው ነገር ቴዎድሮስ ታዋቂ ስለሆነ ወንጀል ሊሰራ አይችልም; ከሰራም ሊጠየቅ አይገባም ማለት ተገቢ አይደለም:: እንደማንኛችንም የሰው ፍጡር ነው ብሎ ማሰብ ነው የሚገባን:: በእኛ በኩል ወንጀሉን ሰርቶ ከሆነ በደጋፊዎቹ እምነት ወንጀሉን አልሰራም ከሆነ ሁሉን ነገር ማስረጃ ነው የሚወስነው” ሲሉ ”የዳኛው መቀየር በፍርዱ ላይ ምን ተጽእኖ ያመጣል; በተለይ ዳኛው አቶ ልኡል የፖለቲካ ሰው ነው ተብሎ ይነገራልና” በሚለው ላይ አስተያየት ለመስጠት እንደማይፈልጉና ተገቢው ፍርድ ይሰጣል፤ ፍርዱንም ማንም መቀበል አለበት ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል::
ዳኛው አቶ ልዑል ገ/ማርያም
በመጨረሻው ሰአት ፍርዱን እንዲሰጡ ከሌላ ቸሎት ተቀይረው የመጡት አቶ ልዑል ከዚህ ቀደም በኦነግ ጉዳይ; በኡጋዴን ነጻ አውጪ ተከሳሾች ላይ; በቅንጅት መሪዎች ላይ; በበርካታ ጋዜጠኞች ላይ እድሜ ልክ እና የረዥም ዓመት ክስ የፈረዱ አንባገነን ዳኛ ናቸው ይሏቸዋል እርሳቸውን የሚያውቁዋቸው:: አቶ ልዑልን የሚያውቋቸው ሰዎች እንደሚናገሩት ገዢው ፓርቲ የሚፈልገውን ሕግን አጣሞ የመፍረድ ሥራ እንዲሰሩ በቦታው ላይ የተቀመጡ ናቸው:: አሁንም በመጨረሻው ሰዓት የቴዲ አፍሮ ክስ እኚሁ ዳኛ እጅ ላይ መውደቁ ትክክለኛ ፍርድ ይሰጣል ተብሎ እንደማይጠበቅ ብዙሀን ይመሰክራሉ::
ከዚህ ቀደም በአቶ ልዑል ዳኝነት 5 ዓመት እስር ቤት ቆይቶ የወጣ አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኛ ‘በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ ሄሊኮፕተር ተመቶ መወድቁን መዘገቡን” ተከትሎ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርቦ ዳኛው “የሄሊኮፕተሩን ስባሪ አምጣ” እንዳሉት ገልጾ; በዚህ የተነሳ 5 ዓመት እስር ቤት ቆይቶ ወጥቷል:: በጣም የሚገርመው ይህ ሂሊኮፕተር መወደቁ እውነት መሆኑንና በጦርነቱ ወቅት አብራሪው በዛብህ ጴጥሮስ (የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ወንድም) እስካሁን በኤርትራ መንግስት እጅ የት እንደተሰወሩ እንደማይታወቅ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን ሁሉ ሲነገር ነበር::
በበርካታ ሀገር ወዳድ ወገኖች ላይ አሰቃቂ ፍርድ የሰጡት አቶ ልኡል በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ አለማየሁ ላይም በትራቸውን አሳልፈዋል:: እኚህ ዳኛ ጋዜጠኛውን በኢትዮጵያ እያለ በሚያሳትመው መዲና ጋዜጣ የተነሳ በጋዜጣው ላይ ‘የደህነንት ሚንስትሩን አቶ ክንፈ ገብረመድህንን እነማን ገደሉት?’ በሚል ባወጣው ምስጢራዊ ዘገባ በዚህ ግድያ ላይም የኢትዮጵያ ገዥ ባለስልጣናት እጅ እንዳለበት በመጻፉና በማጋለጡ ለ3 ቀናት በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ በጨለማ ክፍል ከታሰረ በሗላ በ5ሺህ ብር ዋስትና መለቀቁ; በፍርድ ቤት ቆይታውም የክሱ አዝማሚያ ፖለቲካው ይዘትን እየያዘ በመምጣቱ ከሀገር በዚህ እና በሌሎች 12 ክሶች የተነሳ መውጣቱን ጋዜጠኛው ይናገራል:: በሌላ በኩልም ሔኖክ ከሕወሓት ከተገነጠሉትና እስር ቤት ተወርውረው ከነበሩት ከአቶ ስዬ አብርሃ ጋር በማእከላዊ ምርመራ ማስተባበሪያ በታሰረበት ወቅት እኚህን የቀድሞ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ከ እስር ቤት ቃለ-ምልልስ አድርጎ በጋዜጣው ላይ በማተሙ በተከሰሰበት ክስ አቶ ልኡል ሄኖክን በ5 ሺህ ብር ዋስ አስይዞ ከእስር እንዲወጣ አድርገዋል። አንድን ሰው ኢንተርቪው አድርገሃል በሚል መክሰስና ይህን በሚያህል ብር በዋስ መልቀቅ አሳፋሪም አስገራሚም ነገር ነው። ጨርሶም መክሰስ አይገባም።
አቶ ልዑል የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች በሙሉ ክስ እርሱ በሚቀመጥበት ችሎት እንዲታይ ተደርጎ በየጋዜጠኛው ላይ የቂም በቀል ፍርድ ሲሰጥ የከረመ ሲሆን በዚህም በጋዜጠኞች ዘንድ አንድ ክስ እርሱ ችሎት ከደረሰ ”አለቀልህ” ተብሎ ፍርዱን ቀድሞ ማወቅ እንደሚቻል ይነገራል:: በጋዜጣ ላይ የጋዜጣ ቀን አልጻፍክም ብሎ ካለምንም ማስጠንቀቂያ 2000 ብር የሚፈርደው አቶ ልኡል እጅ የገባ ክስ የፈለገ ማስረጃ ቢቀርብ ነጻ አይወጣም; ይልቁንም ስንት አመት ይፈረድብኝ ይሆን? ብሎ ማሰብ ይቀላል የሚሉ ብዙ ናቸው::
ቴዲ አፍሮ የምስክርነቱን ቃል ሲሰጥ:- ”በጥቅምት 23 ቀን 1999 ዓ.ም. አዲስ አበባ ገባሁ። ምትኩ ግርማ የተባለው ጓደኛዬ ከማናጀሬ ቀጥሎ ጉዳዬን የሚፈጽምልኝ ሲሆን፣ በዕለቱ ከኤርፖርት ከተቀበለኝ በኋላ ሚኪስ ፋሽን የተባለ ልብስ ቤት ሄደን ልብስ ገዛሁ። ምሳ ከበላን በኋላ ወደ ያሲን ቤት ሄድኩ። ከዚያም እዚያ ውለን ወደ አራት ሰዓት አካባቢ ማምሻውን ከያሲን ቤት ወጥተን መስቀል ፍላወር አካባቢ ያለ ቤት አመሸን፣ በኋላ ሳምሶን የተባለ ጓደኛዬ መጥቶ ነበር። ከለሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ ሲሆን ከዛ ወጣን፣ እኔና ሳምሶን ኦሎምፒያ ድረስ አብረን ሄድን፣ እኔ የማሲንቆ ጨዋታ እወድ ስለነበር ወደ ካሳንችስ ይወዳል ቤት እየነዳሁ ሄድኩ። እዚያ ከደረስኩ በኋላ ሃሳቤን ቀየርኩና ወደ ቤቴ ሲ.ኤም.ሲ መንገድ ጀመርኩ፣ ምንግዜም ከውጭ ስመጣ የሄድኩባቸው ሀገራትና የዚህ ሀገር የእንቅልፍ ሰዓት ለማስተካከል ስለሚከብደኝ ነበር ቀኑን ውጭ ያሳለፍኩት። እንደሚታወቀውና ሐኪምም እንደሚለው እንዲህ ዓይነት የእንቅልፍ መዛባት ሲገጥም መኪና መንዳት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል። በዚህ ላይ ውጭ በነበርኩበት ግዜ ተጀምሮ በምኖርበት ሲ.ኤም.ሲ. አካባቢ የመንገድ ኮንስትራክሽን ሥራ ተጀምሮ ስለነበር አባጣና ጎርባጣውን መንገድ አላየሁትም ነበርና ከለሊቱ 9 ሰዓት አካባበቢ ከግዑዝ ነገር ጋር ተጋጨሁ። በሰዓቱ ብዙ ነገሮችን ወደሚረዳኝ ምትኩ ጋር ደወልኩ፣ ስልኩን ሊያነሳልኝ አልቻለም። መኪናዬ ውስጥ ያሉትን ካሴቶቼንና ወረቀቶቼን ሰብስቤ በላስቲክ ካደረኩ በኋላ ሠፈራችን ያለ የፔፕሲ ሠራተኛ አግኝቶኝ በመኪናው ወደ ቤቱ ወሰደኝ። ጠዋት ምትኩ የደወልኩለትን ስልክ አይቶ ደወለለኝ። የደረሰብኝን ነገርኩትና መኪናዋ መንገድ ዘግታ ስለቆመች እንዲያስጎትትልኝ ነገርኩት። በኋላ ላይ መኪናው በትራፊክ ጽሕፈት ቤት ሲያልፍ ታርጋ የለውም ተብሎ መታሠሩን ሰማሁ። ሌላ አንድ ላስገነዝብ የምፈልገው ነገር እኔ ሀገር ውስጥ የገባሁት በጥቅምት 23 ቀን ነው፣ የምኒልክ ሆስፒታል ማስረጃ እንደሚያስረዳው ደግሞ ሟች የሞተው በጥቅምት 22 ቀን ነው።” ብሏል::
አቶ ልዑል የፈለገ ማስረጃ ቢቀርብ ማስረጃውን እንደ እራሱ አመለካከት የሚመለከት እንጂ የሚያገናዝብ እንዳልሆነ በቴዲ አፍሮ ፍርድ ላይ አሳይቶአል የሚሉ ወገኖች አሉ። ዳኛው በተለምዶ እንደታየው ነገሮችን በሙሉ በቅንነት የመተርጎም ባህሪይ የለውም። ዳኛ ለተከሳሽም ለከሳሽም እኩል እንደሆነ የማይገነዘበው ከአቶ ልዑል እጅ መልካም ፍርድ መጠበቅ፤ መለስ ዜናዊ የሚተርትባቸው እነዛ ትላልቅ ግመሎች በመርፌ ቀዳዳ እንዲሾልኩ እንደመጠበቅ ይቆጠራል የሚሉ በርካታ ናቸው።
ከአሁን በሁዋላ ምን ይጠበቃል? በሚለው ጉዳይ ላይ አንድ የሕግ ባለሙያ ፕሮፌሰር ይስሀቅ ኤፍሬም እና አትሌት ሀይሌ ገብረ ሥላሴ አርቲስቱን ከዚህ ቀደም እስር ቤት ድረስ ሄደው ልክ ከዚህ ቀደም በቅንጅት መሪዎች ላይ እንዳደረጉት ማነጋገራቸውን እንደ አንድ ምክንያት; እንዲሁም ዳኛው አቶ ልዑል ገብረማርያም የሕወሓት/ኢሕአዴግ አባል መሆናቸውን በማውሳት ቴዲ ከፍርዱ በሗላ ልክ እንደቅንጅት መሪዎች በይቅርታ ሰበብ ሊፈታ ይችል ይሆናል የሚል ግምታቸውን ሲሰጡ; በርካቶች ቴዲ አፍሮ የአንካሳው ሕግ ሰለባ ሆኖ ፍርዱን ጨርሶ ነጻ ይወጣል የሚል እምነት አላቸው። ይሄው ዳኛ ከ7 ዓመት በፊት በሞት እንዲቀጡ የወሰነባቸው 44 የኦነግ አባላት ሰሞኑን በፕሮፌሰር ይስሃቅ እና ፓስተር ዳንኤል “አማላጅነት” በይቅርታ ሰበብ ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል። እነዚህ የኦነግ አባላት ሁለተኛ ወደፖለቲካ አንገባም ሕዝብንም እንዳይሳሳት እንቀስቅሳለን ብለው በመለስ ዜናዊ ሚዲያ ላይ እየተናገሩ ይገኛሉ።ð
December 3, 2008