አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ዳግም የአማራ ብሎም የኢትዮጵያ ችግር እንዳይሆን ተደርጎ ይቀበራል ሲሉ ተመራቂ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ገለጹ

255467700 1678108785697442 2284034250339695221 nአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በሥልጣን ዘመኑ በኢትዮጵያ በተለይ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አማራዎች ላይ ተነግሮ የማያልቅ ግፍ መፈጸሙን በዞኑ የአማራ ልዩ ኃይል ተመራቂዎች በቁጭት የገለጹት እውነታ ነው። ተመራቂዎቹ እንዳነሱት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ለዓመታት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የአማራ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ ወጣቶችንና ታሪክ የሚያውቁ የሀገር ሽማግሌዎችን እያደነ አጥፍቷል። የአካባቢው ማኅበረሰብ በማንነቱ እንዳይኮራ፣ ቋንቋውን እንዳይናገር በአጠቃላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲሠራ እንደነበር አንስተዋል፡፡
ይህ አልበቃ ብሎት የፈጸማቸው በርካታ ይፋዊ የጅምላ ጭፍጨፋዎች ኹሉም ኢትዮጵያዊ የቡድኑን እኩይ ማንነት በግልጽ እንዲረዳ አድርጎታል፡፡ ይህ የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል የግፍ ግፍ ሊበቃ ይገባል ያሉ እና ቁጥራቸው በርካታ የኾነ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወጣቶች የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን እና የአማራ ልዩ ኃይልን እየተቀላቀሉ ነው፡፡
የአማራ ልዩ ኃይልን ተቀላቅለው በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በባእከር ጊዜያዊ የፖሊስ ማሰልጠኛ ሰልጥነው ትናንት የተመረቁ ወጣቶችም ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል አማራን የማጥፋት ብሎም ኢትዮጵያን የማፍረስ እኩይ ዓላማውን ጨምሮ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር አስተማማኝ ዝግጅት እንዳደረጉ ገልጸዋል።
ኮንስታብል አሰማኸኝ አስገደም ተወልዶ ያደገው በወፍ አርግፍ ከተማ ነው። ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል በሥልጣን ዘመኑ ሲሠራ የነበረውን ግፍ በደንብ ያውቀዋል፡፡ “እኔ ራሴ በአማራነቴ ይደርስብኝ በነበረው ግፍ እና መከራ በስደት ላይ ነበርኩ” ብሏል። ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል በኢትዮጵያ ሕዝብ የተባበረ ክንድ ወደ ዋሻ ከተባረረ በኋላ ኮንስታብል አሰማኸኝ ወደ አካባቢው ተመልሶ ያ ጭቆና እንዳይደገም እየተፋለመ መሆኑን ነግሮናል፡፡
የአማራ ልዩ ኃይልን ለመቀላቀል እድሉን ያገኘው ኮንስታብል አሰማኸኝ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ሲፈጽማቸው የነበሩ ግፎች ፈጽሞ አይደገሙም ብሏል፡፡ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል አሁንም በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች ተለቅሞ መቀበር እንዳለበት እና ዳግም የሕዝብ እና የሀገር ችግር እንዳይሆን ለማጥፋት በቂ ሥልጠና መውሰዱን ገልጿል፡፡
255229665 1678108769030777 6194882390285075436 n
ከማይካድራ የአማራ ልዩ ኃይል አባል በመኾን ትናንት የተመረቀችው ኮንስታብል መሠረት ጫኔ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል በማይካድራ የፈጸመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ከኔ በላይ የዓይን ምስክር የለም ብላለች፡፡ ይህ አረመኔአዊ ድርጊት ዳግም በማንም ላይ እንዳይፈጸም የአማራ ልዩ ኃይል አባል ለመሆን እንደወሰነች ነግራናለች፡፡ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን በአጭር ጊዜ በማጥፋት በስቃይ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለመታደግ አስተማማኝ ሥልጠና መውሰዳቸውን ነው የነገረችን፡፡
“ይኽን አረመኔና ሽብርተኛ የትግራይ ወራሪ ኃይል እንደ እባብ ጭንቅላቱን ለመቀጥቀጥ ወስኜ ነው ሃብትና ንብረቴን ትቼ ለመዝመት የተዘጋጀሁት” ብላለች።
በምርቃቱ ላይ ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይልን ተቀላቅለው የተመረቁ እህትማማቾች፣ ወንድማማቾች፣ አባትና ልጅ፣ ዘመድ እና ሌሎች ሀገር ወዳድ ባለ ታሪኮችንም ተመልክተናል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ- ከሁመራ
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ባሕር ዳር: ሕዳር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.