ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ጥሪ ቀረበ

የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ጥሪ አቀረበ፡፡
የጥሪ ማስታወቂያው ሙሉ ዝርዝርቀጥሎ ቀርቧል፡-
በሃገራችን እየተደረገ ያለውን ሃገርን የማፍረስ ሴራን በማክሸፍ አገርን የማዳን ዘመቻ ላይ ባላቸው እውቀት ልምድ እና አቅም ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ይህ አፍራሽ ሃይል እስኪደመሰስ ድረስ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ባላቸው ተነሳሽነት ከሀገር መከላከያ ጎን በመቆም አቅማቸውና እውቀታቸው የፈቀደውን አስዋፅኦ ለማበርከት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ይህንን ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል አካላዊ ሁኔታ ፣ የጤና ፣ የስነ – አእምሮ ዝግጁነት ፣ እውቀት እና ልምድ ያላቸውን አባላት ከዚህ በታች የተቀመጠውን መስፈርት ለሚያሟሉ የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የወጣ መስፈርት፡፡
1. አጠቃላይ መስፈርቶች
1.1. የኢፊዴሪ ሀገ – መንግስትን የተቀበሉ ፣
1.2. በህዝቦች ሉአላዊነትና አንድነት የሚያምኑ እና በፅናት ለማገልገል
ሙሉ ፍቃደኝነት ያላቸው ፣
1.3. ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ የሆኑ ፣
1.4. በወንጀል ይሁን በፍታብሄር ተከሶ የፍርድ ቤት ክርክር የሌለባቸው፣
1.5. መከላከያ የሚያሰማራቸው የጦር ክፍሎች ሁሉ ተዘዋውረው
ለመስራት ሙሉ ፍቃደኛ የሆኑና የአካል ብቃት ያላቸው ፣
1.6. ለእግረኛ አዋጊ መኮንኖች ፣ ሻለቃ አመራርና ከዚያ በላይ ሃላፊነት
የነበራቸው፣
1.7. በየትኛውም የማዕረግ ደረጃ ላይ በየማሰልጠኛ ማዕከላት አሰልጣኝ
የነበሩ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
1.8. የሜካናይዝድ እና የቡድን መሳሪያ አመራርና ምድብተኛ የነበሩ ፣
1.9. የጤንነት ሁኔታን በተመለከተ
 የአይን ፣ የአፍንጫ ፣ የጆሮ ፣ የጥርስ ፣ የከንፈር ፣ ችግር የሌለባቸው ፣
 ከቲቢ ፣ ከሚጥል በሽታ ፣ ከስኳር ፣ ከደም ግፊት ፣ ከኪንታሮት ፣
ከእንቅርት በሽታዎች ነፃ የሆኑ እና ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ የሆነ
አካላዊ ችግር የሌለባቸው ( የማያነክስ ) ፣
1.10. የትምህርት ሁኔታ ማቀድ ፣ ማሠልጠን ፣ የስልጠና ዶክሜንት
ማዘጋጀት የሚያስችል የትምህርት ዝግጅት ያለው ፣
1.11. በሚመለመልበት አካባቢ ከቀበሌ ፣ ከመስተዳድር እና ከፖሊስ
ከወንጀል ነፃ ስለመሆናቸው የፅሁፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
1.12. የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባል ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ
የሚችሉ ፡፡
2. ዕድሜን በተመለከተ፡-
2.1. ከወታደር እስከ ከፍተኛ የበታች ሹም ያሉ ከ55 ዓመት
ያልበለጡ ፣
2.2. መስመራዊ መኮንኖች ከ60 አመት ያልበለጡ ፣
2.3. ከሻለቃ በላይ ያሉ ከፍተኛ መኮንኖች ከ64 ዓመት ያልበለጡ
መሆን አለባቸው፡፡
3. የምልመላ ቦታና ጊዜ ፡-
 ለአዲስ አበባ ተመዝጋቢዎች በየክፍለ ከተማቸው ሲሆን
 ለክልል ተመዝጋቢዎች በየአካባቢያችሁ ባሉ የቀበሌ ፣ የወረዳ
አስተዳደርና የፀጥታ ወይም ሚሊሻ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ
መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ፣
 የምዝገባ ጊዜው ከህዳር 01 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ ህዳር 15 ቀን 2014 ዓ/
ም ድረስ ይሆናል፡፡
 በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች ዝርዝር መስፈርቶች ተለጥፎ የሚገኙ
መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የአገር መከላከያ ሚኒስቴር
ጥቅምት 2014 ዓ/ም
አዲስ አበባ
ጥቅምት 26/2014 (ዋልታ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  ዩቱብ ኢንተርኔት በሌለባቸው ቦታዎች ቪዲዮዎችን መመልከት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share