በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 448ሺህ 550 የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ

መስከረም 11/2014 (ኢዜአ) በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 448ሺህ 550 የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ዳሽን ቢራ በመጫን መነሻውን ከአማራ ክልል ደብረብርሃን ከተማ ያደረገው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-26981 ኢት.ተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪ አዲስ አበባ ከተማ ከደረሰ በኋላ ወደ ሀረር ከተማ በማቅናት ላይ እያለ ዛሬ ቃሊቲ ኬላ ላይ በተደረገበት ፍተሻ አሽከርካሪው በህገወጥ መንገድ ሲያጓጉዘው ከነበረ አራት መቶ አርባ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ የአሜሪካ ዶላር ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረው ዶላር በቁጥጥር ስር የዋለው ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ ባደረገው ጥብቅ ክትትልና ፍተሻ አሽከርካሪው ዶላሩን በቢራ ሳጥን ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር

በኢትዮጵያ የፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

በወንጀሉ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለው አሽከርካሪ ከነ ዶላሩ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተላልፎ ጉዳዩ በምርመራ ሂደት ላይ መሆኑም ታውቋል።

አሸባሪው የህወሃት ቡድን ቀድሞ በዘረጋቸው ኔትዎርኮች በንግድ ተቋማት የሚሰበሰብ ዶላርን በሀገወጥ መንገድ በውድ ዋጋ እየገዛ ከሀገር እንዲወጣ እና በሀገር ውስጥ የዶላር እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ አንዱና ዋነኛ ምክንያት መሆኑም ነው የተገለጸው።

አሸባሪው ከዚህ የሚያገኘውን ገቢ ለሽብር ተግባር መፈፀሚያ የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ እንዲያገለግለው ሲሰራ መቆየቱን ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት መግለጹን አስታውሷል።

ይህንን ለመከላከል ፖሊስ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመቀናጀት ባካሄደው ኦፕሬሽን በጥቁር ገበያ ላይ የሚንቀሳቀሰው ህገወጥ የዶላር ምንዛሪ እየቀነሰ መምጣቱን አንዳንድ የሚዲያ ተቋማት ባካሄዱት የዳሰሳ ጥናት ማረጋገጣቸውንም ነው የተገለጸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መኢአድና አንድነት ውህደታቸውን ለማራዘም መገደዳቸውን ገለፁ

በአሸባሪው የህወሃት ቡድን አባልነት የሚጠረጠሩ አንዳንድ ግለሰቦች አሁንም ከድርጊታቸው ያልተቆጠቡ መሆኑን በተደረገው ክትትል መረጋገጡን የገለጸው ፖሊስ፤ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳሰቅ የነበረው ዶላር በቃሊቲ ኬላ የተያዘው በህብረተሰቡ ትብብር መሆኑንም አስታውቋል።

ኮሚሽኑ መረጃውን ላደረሱ ግለሰቦች ምስጋና በማቅረብ፤ በቀጣይም ህብረተሰቡ ተመሳሳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ከህግ አስከባሪዎች ጎን በመሰለፍ፣ ጥቆማ በመስጠትና መሰል ህገወጥ ተግባራትን በማጋለጥ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

1 Comment

  1. ሥራው ማለፊያ ነው። ግን ትክክለኛ ጥቁማ በመስጠት ወንጀልን ለባለስልጣናት እያመላከቱ እንዲቆም የሚያደርጉ የህቡዕና የግልጽ ወገኖች መሸለም አለባቸው። ይህ ደግሞ ለቀጣይ ሥራ ያዘጋጃቸዋል። መንግስት ብቻውን ሁሉን ማየትና መስማት አይችልም። ግን ህዝብ በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመርኩዘው አጥፊና ሃገር ከፋፋይ ወንበዴዎችንና ተባባሪዎቻቸውን ለሃገሪቱ የጸጥታ መዋቅር ማጋለጣቸው የዜግነት ግዴታ ነው። ወያኔ መሰሪና እንደ ፍልፈል አፈር ቆፍሮ የሚገባና በቆፈረው ጉድጓድ እልፎችን የከተተ ሃገር ሺያጭ በትግራይ ህዝብ የሚነግድ ስብስብ ነው። አቶ ስዬ አብርሃ አሁን በአሜሪካ ተቀምጠው ወደ ሱዳን እየተመላለሱ የሚሰሩት ተግባር የሚያሳየው ይህኑ የቀደመ የከረፋ ተግባራቸውን ነው። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአሜሪካውን የስለላ ድርጅት ሲያገለግሉ የነበሩት የወያኔ የቀድሞ ዲፕሎማቶችና ጄኔራል ተብየዎች ንብረታቸውን፤ ቤተሰባቸውን በውጭ ሃገር ሸጉጠው ነው ሌላውን የትግራይ ወጣት ወደ እሳት እየገፉ በወገኑ ላይ ይህ ነው የማይባል ሰቆቃ እንዲፈጽም የሚያደርጉት።
    ዛሬ በተመድ ስብሰባ ላይ ዲስኩር ያሰሙት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በቁም ያንቀላፉ፤ ከእውነት የራቁ፤ ያለፈን ታሪክ ያላገናዘቡ ዛሬም ትላንትም ለሰላም ለእድገት አለምን በቀዳሚነት እንመራለን ብለው ሲናገሩ ያሳፍራል። በሚክሲኮ ድንበር በኩል እልፍ ሰው ስደተኛ ሆኖ ይግባ እየተባለና ከአፍጋኒስታን ሳይቀር ሰው እያጓጓዘ ያለው የአሜሪካ መንግስት የሄቲ ስደተኞች መጡ ሲባል ፈረሰኛ ሰዶ በማሰባሰብ በአውሮፕላን በመጫን ወደ ሃገራቸው እንደመለሳቸው አመላካች ዜናዎች እየወጡ ነው። አሜሪካ የጥቁር ህዝቦች ጥላቻ የነገሰባት ሃገር ናት፡ በተለይም ደቡባዊው ክፍል በዚህ የተለከፈ ነው። ለዛ ነው ዶናልድ ትራምፕ ለምን ከኖሮዌ ወይም ከስዊድን ሰው አይመጣም እኔ ጥቁር አልፈልግም በማለት በግልጽ ለካቢኔው የተናገረው። ይህ የውጭና የውስጥ የተሳከረ የአሜሪካ ፓሊሲ ሃገሮችን አፍርሷል፤ አሁንም እያፈረሰ ነው ወደፊትም አይቆምም። የሚገርመው የመንና ኢትዮጵያን በአንድ አረፍተ ነገር በንግግራቸው ላይ መጠቀሳቸው ነው። የመን ሰላም እንዳታገኝ ያደረጋት ራሱ አሜሪካ አይደለም እንዴ? ሳዊዲዎች እኮ የአሜሪካን ተልዕኮ ነው የሚፈጽሙት። ዛሬ በሱዳን ተሞከረ የተባለው የመንግስት ግልበጣ ግብጽ ከርሞ በተመለሰ አንድ ወታደራዊ ጄኔራል እንደ ተመራ ያመለክታል። ይህ ሰው የአሜሪካው የስለላ መረብ ከግብጽ ጋር በመቀናጀት ያዘጋጀው ይሆን? አይሆንም ብሎ ለማመን አይቻልም። የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች እንደሚባለው ሱዳን ዛሬ በአሜሪካና በወያኔ ግፊት የሰሜን ጦር በወያኔ በተጠቃ ማግስት የኢትዮጵያን ግዛት ዘልቃ መያዟ የአሜሪካ አይዞታ እንዳለበት ጥርጥር የለውም። በዚህ ሁሉ የሸፍጥ ፓለቲካ ነው ለአለም ሰላምና ለህዝቦች እኩልነት እንሰራለን የሚባለው። በሰሜንኛው አማርኛ ይህ ንግግር “መዛበር” ይባላል። ፍሬ ፈርስኪ ዲስኩር።
    ወያኔ የውሸት ገንዘብ የሚያትም፤ የውሸት ዶላር የሚያባዛና ሰው የሚያታልል፤ በተወሳሰበ የሃዋላና የንግድ ተቋሙ የዋህ የሆኑ ኢትዮጵያውንና ኤርትራዊያንን እናንተ ላኩ እንጂ እኛ የኢትዮጵያ ባንክ ከሚሰጠው የበለጠ መንዝረን ለዘመዶቻቹሁ እናሳቅፋለን በማለት ሲያሞኙን ኖረዋል። ያ ገንዘብ ዞሮ ተመልሶ የህዝባችን ሰቆቃ ያባብሰዋል። የብር ለውጡ 40 ሆነ 100 እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ከእነዚህ ሾተሎች በመራቅ በቀጥታ በዌስተርን ዪኒየንና በሌሎችም ህጋዊ በሆኑ መንገዶች መላክ ይኖርበታል። አሁን ደግሞ ወያኔዎች የሚጠቀሙበት ዘዴ ” እኛ ኤርትራዊ ነን” በማለት ነው። አዎን ልብ ላለውና አብሮ መኖር ለሚሻ ሃበሻ ሃበሻ ነበር። ግን በዘሩና በቋንቋው ለሰከረ ቡድን ደግሞ እንደ ድር አራዊት በዘሩ ተሰላፊ ነው። ግራም ነፈሰ ቀኝ እነርሱ ትግሬም ሆኑ ኤርትራዊ የማጭበርበሪያ መንገዳቸው አሸን ነው። አንድ ሲደፈን ሌላ ጉድጓድ ይምሳሉ። የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን የሞት መልዕክተኞች ነቅቶ መጠበቅ አለበት። ጊዜው ለወያኔ እየጨለመ ነው። አሁን እንሆ በእነርሱ የሚነዳው የኦነግ ሸኔው መሪ የአባ ገዳዎችን ምክር ሰምቶ በሰላም በሃገሩ ለመኖር መግባቱ ወያኔን ያለ ልክ ያበሳጨዋል። ዶሮም የምናውቀው የኦሮሞ ህዝብ ሰላምን እንጂ ጦር መዛዥ ህዝብ አይደለም። ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ ለአንተ የሚበጅህን እናውቅልሃለን የሚሉ የኦሮሞ የፓለቲካ ሙታኖች ናቸው ክፋትን ያሳዪት። የሃገሪቱ የወደፊት እድል ፈንታ ብሩህ እንዲሆን ክተፈለገ ወያኔ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለበት። እናስብ ህሊናውን ለደም የሸጠው ጌታቸው ረዳ በግብጽ የመገናኛ ብዙሃን ላይ የተናገረውን። ሞት ለወያኔ ደም መጣጮች።በቅርቡ በገጣሚ የሺወርቅ ተጫነ ታትሞ በወጣው የግጥም ስብስብ ” ክረምት እንታረቅ” ከተሰኘው ስብስብ ባገኘሁት አንዲት ግጥም ልሰናበታችሁ።
    ነጻ ነን |2| ብለን ብናውጅም
    ነጻ መሆን ብቻ ነጻነት አይሰጥም። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share