“በዓለም ላይ ያሉ አሸባሪዎች የሚረሽኑት ሰዎችን ነው፤ ህወሓት ግን ሰዎችን ረሽኗል፤ እንስሳትን ረሽኗል፤ እጽዋትንም ረሽኗል” – ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

“አሸባሪው ህወሓት ላላፉት 27 አመታት የኢትዮጵያዊነትን ስረ መሰረት በመናድ ነበር ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር የኖረው” - ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ በጠ/ሚር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር

daniel

የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች አሸባሪው ህወሓት ያደረሰውን ጉዳት ሰሞኑን ግንባር ድረስ ተጉዘው ተመልክተው ተመልሰዋል። ከዚህ ምልከታ በኋላ በአዲስ አበባ ውይይት አካሂደዋል።

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ “አሸባሪው ህወሓት በዓለም ላይ ካሉ አሸባሪዎች ሁሉ የተለየ ነው” ሲሉ አብራርተዋል።

አሸባሪው ህወሓት በዓለም ላይ ካሉ አሸባሪዎቹ ሁሉ የተለየ ነው ያሉት ዲያቆን ዳንኤል፤ ልዩ ነው ያሉባቸውን ምክንያቶችንም ዘርዝረው አብራርተዋል።

እንደ ዲያቆን ዳንኤል ማብራሪያ፤ በዓለም ላይ ያሉ አሸባሪዎች የሚረሽኑት ሰዎችን ነው። ህወሓት ግን ሶስት ህይወት ያላቸውን ነገሮች እስካሁን ረሽኗል። ሰዎችን ረሽኗል፤ እንስሳትን ረሽኗል፤ እጽዋትንም ረሽኗል። ይሄ በሌላ አገር የአሸባሪ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የህወሓት የአሸባሪነት ታሪክ ነው።

መቄት ላይ፣ ጭና ላይ ዛፎችን ነው የረሸናቸው፤ ከብቶችን ነው የረሸናቸው፤ ዶሮዎችም አልቀሩት” ያሉት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ “ይሄ ኅይል ቢፈቀድለትና የኢትዮጵያ ህዝብ አቅም ቢያጣ ምስራቅ አፍሪካን ብሎም አፍሪካን ከማጥፋት የሚቆም አይደለም፤ ዓለም ያልተረዳው አንዱ ነገር እሱን ነው” ብለዋል።

አሸባሪው ህወሓት የሆነ አንድ የተቃዋሚ ቡድን አይደለም፤ በዓለም ላይ መልካም የተባሉ ነገሮችን በሙሉ ከማጥፋት የማይመለስ አካል ነው ሲሉም ነው አሸባሪ ቡድኑን የገለጹት።

አሸባሪው ቡድን በበጀትና በጊዜ አንድ እንዳንሆን የሰራቸውን ሁሉ ነቅለን መጣል አለብን፤ እየተከታተልን የክፋት ሶንኮፉን መንቀል ይገባናል” ብለዋል ዲያቆን ዳንኤል።

ኢትዮጵያዊያን፤ የሚፈልጓትን ኢትዮጵያ ገንብተው፣ መልካም አስተዳደርን አስፍነው፣ ዴሞክራሲን አበልጽገው ማሳየት መቻል አለባቸው” ሲሉም ነው ዲያቆን ዳንኤል የተናገሩት።

በዚሁ መድረክ ላይ ተሳታፊ የነበሩት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ በበኩላቸው፤ አሸባሪው ህወሓት እሴት ያለው የተረጋጋ ሀገር መፍጠር የሚያስችሉ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የሀይማኖት አባቶችን፣ አርሶ አደሮችን፣ ወጣቶችን፣ ምንም የማያውቁ ህጻናትንም ጭምር መጨፍጨፉን በተግባር አይተናል” ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  "የትግራይ ክልል መንግስት አዝዞ ነው"

ይሄ በጣም አሳዛኝ የዘር ጭፍጨፋ ተብሎ የሚጠቀስና በጦር ወንጀልም ሊያስጠይቅ የሚችል በጣም ዘግናኝ ጭፍጨፋ ነው ያሉት ዶ/ር ቢቂላ፤ የአሸባሪው ቡድንን አገር የማፍረስ እሳቤ በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል።

አሸባሪው ህወሓት ላላፉት 27 አመታት የኢትዮጵያዊነት ስረ መሰረትን በመናድ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር ነበር፤። ይሄ የጥፋት አስተዳደር ስልቱ ሲፈርስበት ተስፋ በመቁረጥና በመብረክረክ ኢትዮጵያን ወደመናድ ገብቷል። ኢትዮጵያዊያን የኢትዮጵያዊነት ስረ መሰረት እንዲገነባ እንዲጠነክር ማድረግ አለብን” ብለዋል ዶ/ር ቢቂላ ።

አመራሮቹ በውይይታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካል አሸባሪው ህወሓት የቃጣውን አደጋ በመቀልበስ የኢትዮጵያን ታላቅነት ማረጋገጥ እንደሚገባ፤ ህዝቡ ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመሰለፍ ያሳየውን ደጀንነት ሚዲያውን ጨምሮ የሚመለከታቸው ሁሉ በስፋት ሊሰሩበት እንደሚገባ በአጽንኦት ተነስቷል።
(ኢ ፕ ድ)

1 Comment

  1. Yes, TPLF was not and is not a holly political entity at all and it must be dealt with in such a way that the political system it created and developed should be eliminated! I do not think this is something mysterious at all! But it must be underscored that it is political and morally nonsensical to blame or curse TPLF as such whereas the very system of deadly ethnocentric political system is fully operational in the very palace of Arat Kilo controlled by a political entity called OPDO/OROMUMA in a much more horrifying manner! And Daniel Kibret is one of the most cynical, hypocritical, conspiratorial and opportunist personalities! what makes Daniel’s political and moral personality much worse is his making of religion the very instrument of a very sinful or criminal political system! I am sorry to say but I have to say that unless we courageously tell these kinds of very cynical and destructive elements of the cancerous political system we are languishing in, forget about the continuation of Ethiopia as one country leave alone the coming into being of Democratic Ethiopia!
    I wish people such as Daniel Kibret could have at least a moral courage of telling the very huge and bitter reality gong on in the country because of the very dirty and dangerous political game being played by the two factions of the same crime-infested political system (EPRDF), one in the northern part of the country and the second controlling the Arat Kilo Palace. Yes, I wish Daniel Kibret could tell us why he chose to be willing to serve the very cynical and of course ruthless faction of of EPRDF led by the very delusional and illusional and unbelievably dishonest prime minister.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share