ጀነራል አበባው ታደሰ በወሎ ግንባር በሰሜን ወሎ ግምባር September 19, 2021 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email የኢፌዴሪ መከላከያ ምክትል ጠ/ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ በሰሜን ወሎ ግምባር ተገኝተው ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በግዳጅ አፈፃፀም ዙሪያ ተወያዩ። በግምባሩ የተገኙት ም/ጠ/ኢታማዦር ሹሙ ፣ ለምንም የማይበገረው ሠራዊታችን ከቀደምት የኢትዮጵያ ታሪክ በመነሳት ለህይወቱ ሳይሳሳ በሀገሪቱ ህልውና ላይ የተጋረጠውን አሸባሪ ሀይል ለመደምሰስ እያደረገ ያለውን ስኬታማ ኦፕሬሽን አድንቀዋል። ጀነራል አበባው ፣ ሠራዊታችን በተደጋጋሚ የሚያስመዘግባቸው ድሎች የሽብርተኛውን ሀይል ለመደምሰስ አስተማማኝ ቁመና ላይ በመሆኑ ለላቀ ግዳጅ አፈፃፀምም የወትሮ ዝግጁነት አቅም የመፍጠሩ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ በበኩላቸው ፣ ሰራዊታችን ህዝባዊነት ባህሪውን አስጠብቆ አሸባሪውን ሀይል አንገት እያስደፋ የወረራቸውን አንዳንድ ቦታዎች በማስለቀቅ አኩሪ ታሪክ እየሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል ፡፡ አሸባሪው የትህነግ ቡድን በህዝብ ላይ እያሳደረ ያለውን ግፍና በደል በመገንዘብ በአጭር ጊዜ እርምጃ በመውሰድ የተፈናቀለውን ማህበረሰባችን ወደ ቀየው እንዲመለስ ለማድረግ ግምባር ላይ ያለው ሀይላችን የጠላትን ቅስም እየሠበረ ነው ብለዋል። ተቋሙም በአሁኑ ሠዓት ብቁ ሠራዊትን በማፍራት አስተማማኝ የዝግጁነት ምዕራፍ ማጠናቀቁንም ተናግረዋል።(ኢፌድሪ መከላከያ) –(ኢፌድሪ መከላከያ) Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ አጋር ሀገራት ያስመዘገብናቸውን ከፍተኛ ድሎች ለመመስከር አለመድፈራቸው እንቆቅልሽ ነው- ሙፈሪያት ካሚል Next Story የሁለት ደብዳቤዎች ወግ ከአዲስ አበባ እና ከመቀሌ – መሳይ መኮነን