አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ አጋር ሀገራት ያስመዘገብናቸውን ከፍተኛ ድሎች ለመመስከር አለመድፈራቸው እንቆቅልሽ ነው- ሙፈሪያት ካሚል

242321284 3028674050708387 5462023528350303105 nየአሜሪካ መንግስትን ጨምሮ አንዳንድ አጋር ሀገራት ከለውጥ ማግስት ያስመዘገብናቸውን ከፍተኛ ድሎች ለመመስከር አለመድፈራቸውና ከተተነበየልን በተቃራኒው በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ኢትዮጵያ ማሸነፏን እውቅና መስጠት አለመድፈራቸው እንቆቅልሽ ነው ሲሉ የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ።

ሚኒሰትሯ የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ካረን ባስ የሚመራ ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል በሀገራችን ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ከምንጩ ለመስማትና ለመረዳት በመምጣታቸው አመስግነው የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ውሳኔ ከማድረጉ በፊት እና በኋላ የሰብዓዊ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የተደረጉ ጥረቶችን በዝርዝር አስረድተዋል።

ሰብዓዊነት አድሎን አይፈልግም ያሉት ሚኒስትሯ፤ በህወሃት ወረራ ምክንያት ለተጎዱ በሁሉም ስፍራ ለሚገኙ ወገኖቻችን ሁሉ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማዳረስ እያደረግን ያለው ጥረት እንደመንግስት አጠናክረን እንቀጥላለን ሰብዓዊ አጋሮችም ይህንኑ እንዲያደርጉ እንጠብቃለን ብለዋል።

ሚኒስትሯ የአሜሪካን መንግስትን ጨምሮ አንዳንድ አጋር ሀገራት ከለውጥ ማግስት ያስመዘገብናቸውን ከፍተኛ ድሎች ለመመስከር አለመድፈራቸውን በተለይም ከተተነበየልን በተቃራኒው በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ኢትዮጵያ ማሸነፏን እውቅና መስጠት አለመድፈር እንቆቅልሽ ነው ብለዋል።

አክለውም አጋሮቻችን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እንዳላየና እንዳልሰማ ለማለፍ ቢሞክሩም አሁንም የተቃጣብንን ወረራ ከመመከት ጎን ለጎን ዜጎቻችንን ከችግርና መፈናቀል ለመታደግ የምናደርገው ጥረት የሰውነት እና የመንግስትነት ግዴታችንን መወጣት በመሆኑ ለአፍታም የምንዘናጋበት ጉዳይ አይደለም ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል።

ሰብዓዊ እርዳታን በፍጥነት ለማድረስ እንዲሟሉ በሰብዓዊ አጋሮች የተጠየቁ ቅድመሁኔታዎችን ሁሉ ብናመቻችም እስከ አሁንም ቢሆን አለም አቀፍ ድርጅቶች በተገቢው መጠንና ፍጥነት ለተጎዱ ወገኖቻችን ለመድረስ እየተንቀሳቀሱ አይደለም ይህም ያሳስበናል ብለዋል።

በአማራ እና አፋር ክልሎች የእለት እርዳታ የሚሹ ወገኖቻችንን ቁጥር ከዕለት ዕለት እየጨመረ በመሆኑ በተለይም መንግስት መድረስ በማይችልባቸው አካባቢዎች የተመረጡ አጋሮች እርዳታን እንዲያደርሱ በተደረገው ስምምነት መሰረት አፋጠኝ ምላሽ እንዲሰጡ መጠየቃቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሰላማዊ ትግል የህዝብ ድምፅ የሚረጋገጠው በምርጫ ነው ብለን እናምናለን - የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.