ትርጉም እና መግቢያ
አንድ፤ የኢኮኖሚ ጦርነትና የጦርነት ኢኮኖሚ የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው። የጦርነት ወከባ የሚያካሂድ የአገር ውስጥና የውጭ ተቀናቃይ ኃይል ተቀናጅቶ የሚያካሂደው ተዛማጅ ጦርነት ኢላማ የሆነውን አገር፤ እቅድ በተሞላበት ደረጃ፤ የኢኮኖሚውውን፤ የገንዘቡን፤ የውጭ ምንዛሬውን፤ የንግዱን ወዘተ ዘርፍ በማዳከም ብሄራዊውን/አገራዊውን የወታደራዊ ወይንም የመከላከያ ኃይሉንና አቅሙን ማምከን ነው። የብድርና የውጭ እርዳታ እቀባ ሲደረግ (punitive financial sanctions) የኢኮኖሚ ጦርነት አካል ይሆናል። የምእራብ አገሮች ከህወሓት/ወያኔ ጋር በመናበብ የሚያደርጉት እቀባና ጫና በመሰረቱ የተቆላለፈ የማማከን ስልትና መሳሪያ ነው።
ይህ የኢኮኖሚ ጦርነት ስልት ምንም አይነት ርህራሄ በማያሳይ ደረጃ ሲካሄድ ጉዳቱ ከፍ ያለ ነው። ምክንያቱም፤ ጦርነቱ ወረራ ስለሆነ ነው። ወራሪው ኃይል ያገኘውን ዘርፎ፤ የሰረቀውን ሰርቆ፤ የበላውን በልቶ፤ የተሸከመውን ተሸክሞ የቀረውን ግን ያማክነዋል። የሚያማክነበት ዋና ምክንያት ነዋሪው ህዝብ ተመልሶ እንዳያንሰራራ ለማድረግ ነው። የወረራው ዋጋ ከፍ እያለ ሲሄድ አሸናፊ እሆናለሁ፤ ጠላቴን አምበረክከዋለሁ የሚል ስሌት ስላለው ነው። ህወሓት/ወያኔ ከጅምሩ የሚከተለው ዘውግ ተኮር የቂም በቀል እና የከሃዲነት መርህ አሁንም አልተቅየረም። ቂም በቀሉ ትኩረት ያደረገው አሁንም በአማራው፤ በተለይ የትግራይ ኩታ ገጠም በሆነው በጎንደሬውና በወሎዮው ሕዝብ ላይ ነው። በከሃዲነት በኩል ደግሞ ገና ህወሓት/ወያኔ ሥልጣን ሲይዝ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ የባህር በር አያስፈልጋትም ብሎ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ የጻፈው ምስክር ነው። መለስ በስነ ምግባርና በእምነት በኩልም ለተከታታይ ትውልድ ትቶለለት ያለፈው የዘውግ የበላይነት ብቻ ሳይሆን ሌብነትም ጭምር ነው። “ሌባው እስካልተያዘ ድረስ ሌብነትም ስራ ነው (So long as you are not caught red-handed, theft is work too” ያለው ሊረሳ አይችልም። ይህ ደዌ ለኢትዮጵያ ልማት ማነቆ መሆኑን ልንክድ አንችልም። የአስተሳሰብና የባህርይ ለውጥ ያስፈልጋል የምለው ለዚህ ነው።
የወራሪው ክፉትና ጨካኝነት ለአንድ ዘውግ፤ ለምሳሌ ለአማራው ወይንም ለአፋሩ ብቻ አይሆንም። በአገር ደረጃ የሚካሄድ ወረራ ስለሆነ በኢኮኖሚው በኩል የሚያስከትለው አሉታዊ ውጤት ዘውጋዊ ብቻ ሊሆን አይችልም። ብሄራዊ/አገራዊ ነው። ዛሬ ህወሓት/ወያኔ በአማራና በአፋሩ ክልል የሚያደርገው ጭካኔና ውድመት ለመላው ኢትዮጵያ አሉታዊ የኢኮኖሚ ውጤት አለው። ወረራው እኔ ከሞትኩ ማንም ሊበላና ሊኖር አይገባውም የሚል የዜሮ ድምር (Zero Sum) መርህን ያንጸባርቃል። ህወሓትን/ውያኔን አረመኔና ጨካኝ የሚያስብለው አይምሬ በመሆኑ ነው። ተዛማጅ ጉዳቱ ደግሞ ለተራው የትግራይ ሕዝብ ጭምር ነው። ረሃብ መከሰቱ አይቀርም። የወደመውን መልሶ ለመተካት (ለማቋቋም) አስርት አመታት፤ የብዙ ቢሊየን ብር መዋእለንዋይ ፈሰስ ይጠይቃል።
ህወሓት/ወያኔ እንኳን ለሰብአዊ ፍጥረት ቀርቶ ለእንስሳትና ለአዋሳት ጨካኝ ነው። ያልበላውን በሬ ይገድላል። ያልቀማውን ዱቂት ያወድማል። በተደጋጋሚ እንዳሳሰብኩት ህወሓት/ወያኔ መድሃኒት የሌለው ነቀርሳ ነው።
የህወሓት/ወያኔ ርእዮት፤ የዘረጋው የምዝበራና የጭቆና መረብ፤ የመሰረተው የከፋፍለህ ግዛው ሕገ መንግሥትና ተቃርኖን የሚያባብስ የአስተዳደር መሰረት ከስሩና ከመሰረቱ ካልተቀረፈ በስተቀር ኢትዮጵያ እንደ ሃገር፤ ኢትዮጵያዊነት እንደ ዜግነት መለያ ሊቀጥሉ አይችሉም። በኔ ጥናትና ምርምር፤ በኔ እምነት ከህወሓት/ወያኔ ጋር የሰላም ድርድር ለማድረግ የሚቻልበትን መስፈርት ፈልጌ ለማግኘት አልቻልኩም። ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ዋና ጸር ከሆነ፤ ከኢትዮጱያ የውጭ ጠላቶች ጋር ሴረኛ ከሆነ ድርጅት ጋር እንዴት ለመስማማት ይቻላል? የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ እንድትመልሱት አሳስባለሁ። በኢትዮጵያ ላይ የሚካሄደው የኢኮኖሚ ጦርነት ኢትዮጵያን እንደ ሃገር እንዳትቀጥል ለማድረግ፤ ሕዝቡ በራሱ መንግሥት ላይ እንዲነሳበት ለማድረግ ከሚደረገው ሴራ ጋር የተጣመረ ስልት ነው።
ሁለት፤ በጦርነት ወቅት የሚካሄድ የጦርነት ኢኮኖሚ (an economy that is at war) ደግሞ ይህ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል ተብሎ በዘመናዊ የመንግሥት አመራር በጥንቃቄና በእቅድ ያለ የሌለ የሰውና የቁሳቁስ፤ የገንዘብና ሌላ አቅሙን የሚያጠናክርበትን ሁኔታ ይመለከታል። ፊሊፕ ለቢሎን የተባለው ባለሞያ በዊኪፒዲያ እንዲህ በሚል አቅርቦታል። A war economy is a “system of producing, mobilizing and allocating resources to sustain the violence.” እልቂትና ሁከት የሚያካሂደው ህወሓት/ወያኔ እንጅ የኢትዮጵያ መከላከያ፤ የአፋር ልዩ ኃይል ወይንም የአማራ ፋኖ አይደለም። የአፋሩ፤ የአማራው፤ የኦሮሞው ወዘተ ተራ ገበሬ አይደለም።
ሂሳብ “እናወራርዳለን” ያለው ህወሓት/ወያኔ ያስከተለው የኢኮኖሚ ውድመት
ያለፈው ዓመት (2012 ዓ.ም) እንዴት አንዳለፈ ባጭሩ ልገምግም። የወረራውን ዋጋ በባጀት ብቻ መተመን ትክክል አይደለም። የኢትዮጵያ እናቶች፤ ሴቶች ተደፍረዋል፤ ተዋርደዋል። ቁጥራቸው በቅጡ ባይታወቅም ቅሉ፤ በብዙ ሽህ የሚገመቱ ወገኖቻችን፤ ወጣት ሴቶችን፤ ህጻናትን፤ አዝዋንትን ጨምሮ ተጨፍጭፈዋል። ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል። ለመተካት የማይቻሉ ቅርሶች ተሰርቀዋል፤ ወድመዋል። በድሃው ሕዝብ የተሰራው መሰረተ ልማት ወድሟል። በአማራው ክልል ብቻ ሰባት ሽህ ትምህርት ቤቶች ወድመዋል። ክሊኒኮች፤ ሆስፒታሎች ተዘርፈዋል፤ ተቃጥለዋል። የጤና አገልግሎት ባለሞያዎች ተገድለዋል። በቅጡ ባይታወቅም ብዙ ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። በሰሜን ወሎ ሰው ሰራሽ እርሃብ ተከስቷል። ይህ የህወሓት/ወያኔ የውድመት መሰፈርት ነው።
ህወሓት/ወያኔ ባስፋፋው ጦርነት ምክንያት አርሶ አደሩ እርሻውን በወቅቱ ለማረስ አልቻለም። የዚህ አሉታዊ ውጤት ሰው ሰራሽ እርሃብ እንዲከሰት አድርጎታል። ይህንን የኢኮኖሚ ቀውስ እንዴት እንተወጣዋለን? ችግሩን እንዴት ኢትዮጵያ እንደ ገና ወደ ስንዴ ልመና እንድትሄድ እየተገደደች ነው? ልመናው ጫናውን አያጠናክረውም?
የዚህ ዘርፈ ብዙ ተግዳሮት ክስተት የሚያሳየኝ አንድ መሰረታዊ ሁኔታ አለ። ይኼውም፤ ጦርነቱን ለማሸነፍ፤ የምርት አቅምን ማሳደግና የሚመረተውን በእቅድና በስልት ማሰራጨትና ማከፋፈል ወሳኝ መሆኑን ነው። ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊቆጣጠርቱና ሊመኩበት የሚችሉት እምቅ አቅም ራስን በራስ መደገፍ ብቻ ነው። የኢኮኖሚውን መዋቅር እየለወጡ የስራ እድል በመፍጠርና ምርትን በማሳደግ ላይ ትኩረት ከተደረገ ኢትዮጵያ ችግሩን ትወጣዋለች።
ይህንን የስራ እድል በሰፊው የመፍጠርና የምርት አቅምን የማሳደግ ኃላፊነቱን የተሸከሙት ደግሞ የፌደራሉ መንግሥትና ተባባሪ የክልል ባለሥልጣናት ናቸው። በጦርነት ኢኮኖሚ የመንግሥት ሚና ከፍ ያለ መሆኑን መቀበል ያስፈልጋል። ይህንን ስል ግን በጦርነት ኢኮኖሚ ደጀኑ ሕዝብ መሆኑን አስምርበታለሁ። አመራሩ ግን መንግሥት ነው። ሁለቱ እጅና ጓንት ሆነው ከሰሩ ጦርነቱን አስተማማኝ በሆነ ደረጃና በተወሰነ ጊዜ ስኬታማ ለማድረግ ይቻላል። የተበታተነ ከሆነ ግን የሚባክነው መዋእልንዋይና ሌላው ግብዓት ግዙፍ ነው።
የጦርነት ኢኮኖሚ ዋናው መርህ ቁሳቁሶችን ማምረት፣ መሰብሰብና አግባብ ባለው ደረጃ ለተጠቃሚው ክፍል ማቅረብና ማሰራጭት ነው። የምርት ውጤትን ማሳደግ፤ ማሻሻልና ማሰራጨት የስኬቱ አካል ነው። ወጣቱን ትውልድ፤ ሕዝብህን ከአረመኔው ኃይል አድን፤ ኢትዮጵያን ታደግ ብሎ መቀስቀስ አግባብ ያለው መርህ መሆኑን እጋራለሁ። አገር ከሌለ ማንኛውም ጉዳይ ፋይዳ ቢስ ነው። የግሉ ክፍል መገንዘብ ያለበትም ይህንኑ ነው። አገር ከሌለ እንኳን ትርፍ ሊገኝ ቀርቶ ያለውንም ካፒታል ለመጠቀም አይቻልም። አገር ካለ ግን ትርፍ የሚገኝበት እድል ይስፋል። ወጣቱን ሆነ ገበሬውን፤ ባለሞያውን ሆነ የኔ ቢጤውን ወዘተ “ተነስ” ልዩ ኃይሉን፤ ሚሊሻውን፤ ፋኖውን፤ መከላከያውን ተቀላቀል ሲባል ከጀርባ ሆኖ ስንቅ ማቀረብ ወሳኝ ነው። የመንግሥት ባለሥልጣናት ሚናም ይኼው ነው። አስተማማኝ ሁኔታዎችን መፍጠር።
የስልታዊ ዝግጅት ወሳኝነት
የጦርነት ኢኮኖሚ መርህ በዘፈቀደ ሊሰራ አይችልም። ድርጅት፤ እቅድ፤ አመራርና ቁጥጥር ይጠይቃል። እቅድ ማለት ያለውን ቁሳቁስ ገምግሞ ጥንካሬንና ድክመትን ማወቅ ማለቴ ነው። ቁጥጥር ማለት የሚመረተው ለተፈለገው ዓላማ መዋሉን ማረጋገጥ፤ እንዳይባክንና እንዳይሰረቅ ማድረግ ማለቴ ነው። ጠላት እንዳይጠልፈውና እንዳይስርቀው ማድረግ ማለቴ ነው። ሰርጎ ገቦችና ከሃዲዎች ካሉ እነሱን መንጥሮ ማስወገድ ማለቴ ነው። ለጥቃት ዋና ሚና የሚጫወቱት ደግሞ አካባቢውን በሚገባ የሚያውቁት ናቸው። ለመስረቅና ለመጥለፍ ችሎታ ያስፈልጋል። ችሎታ ያላቸው ሌቦች ህወሓት ያሰለጠናቸው፤ ያዘጋጃቸውና በየድርጅቱ ያሰማራቸው ናቸው። በየኤምባሲውና በስደት ዓለም ያሉት ጭምር።
በጦርነት ወቅት፤ መንግሥት የሚመረተውንና የሚሸምተውን ቁሳቁስ ለምን ለምን እንደሚውል አስቀደሞና፤ በእቅድ፤ በጥንቃቄና በስልት ማዘጋጀት አለበት። ዋናው ዓላማ ጦርነቱን በበላይነት አሸንፎ ወደ ሰላም ለመሸጋገር ስለሆነ ስርጭቱ (Allocation of scare resources) በአንድ በኩል ለሚዋጋው ኃይል ማቅረብ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ አስፈላጊ የሆኑ የፍጆት ቁሳቁሶችን የሕዝቡን የመግዛት አቅም በሚያንጸባርቅ ደረጃ ማቅረብ ነው። የሕዝቡ ፍላጎት ካልተሟላ ሕዝቡ በመንግሥቱ ላይ ያምጻል።
በተጨማሪ፤ ከጦርነቱ በኋላስ ምን አይነት የስራ እድል ፈጠራና የኢኮኖሚ ልማት ፍኖተ ካርታ ያስፈልጋል? የሚለው ከአሁኑ እንዲታሰብበት እመክራለሁ። ከጦርነቱ የሚመለሰው ወጣት በዝቅተኛ ወለድ፤ ያለ ምንም መያዣ (minimum collateral) ብድር እየተሰጠው ወደ አዲስ የምርትና የአገልግሎት ስራዎች እንዲሰማራ ማድረግ ያስፈልጋል።
የጦርነት ኢኮኖሚ በዝርዝር
ጥናቶችና ምርምሮች የሚያስተምሩት የሚከተሉትን ነው፤
የጦርነት ኢኮኖሚ ማለት መላውን የአገሪቱን ኢኮኖሚ ሁሉ የሚሸፍን ነው፤ አፋር፤ አማራ፤ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፤ ጋምቤላ፤ ኦሮምያ፤ ሶማሌ ወዘተ አይለይም፤ አንዱ የሌለው ደጋፊና አጋር መሆን አለበት።
በጦርነት ላይ ያለ መንግሥት የጋራ ግንዛቤ ካደረገ (shared understanding and common platform) በኋላ ማድረግ ያለበት የሚመረተውንና የሚሸመተውን ቁሳቁስ ሁሉ በእቅድ፤ በስልት፤ ከፍተኛ ውጤት በሚያሳይ ደረጃ አገሪቱን ለመታደግ፤ ሕዝቡን ከአጥፊዎች ለመከላከል በሚያስችል ደረጃና አቅም ማስራጨት መሆን አለበት።
በጦርነት ላይ ያለ መንግሥት የገቢ አቅሙን ለማጠናከር የገቢ ምንጮችን መገምገምና ልዩ ልዩ ዘዴዎችን መቀየስ አለበት፤ አንዳንድ በጦርነት የተበከሉና የተፈተኑ አገሮች የቀረጥ ጭማሬ አድርገዋል፤ ልዩ የጦርነት ቦንድ አውጥተው ተጠቅመዋል።
በጦርነት ላይ ያለ መንግሥት ጦርነቱን እንደ አዲስ የምርት እድል ተጠቅሞ የኢንዱስትሪ፤ የመድሃኒት አቅርቦትና ሌሎች የፍላጎት ቁስቁሶችን ለአስፈላጊው ጉዳይ በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባል። ጦርነት ሲካሄድ ጠላት ከሚያደርጋቸው አስኳል ጉዳዮች መካከል የዋጋ ግሽፈት እንዲከሰት ማድረግ ነው። የውጭ ምንዛሬ በጥቁር ገበያ እንዲገበይ ማድረግ፤ ንግድ ከጉምሩክ ውጭ እንዲካሄድ ማድረግ ወዘተ። የመንግሥት ባለሥልጣናት ልዩ ትኩረት ከሚያደርጉባቸው ፖሊሲዎች መካከል የውጭ ምንዛሬን የጥቁር ገበያ መረብና ሰንሰለት ከምንጩና ከመሰረቱ መቆጣጠርና ማምከን ዋናው ስልት ነው። በውጭ የምንኖር አገር ወዳዶች ያለብን ግዴታ ደግሞ ለዚህ የጥቁር ገበያ መጋቢ አለመሆን ነው። ለትንሽ ትርፍ ብለን ኢትዮጵያን አንጉዳት!
በአጭሩ በጦርነት የተበከለ ኢኮኖሚ የሚመረተው ቁሳቁስና የሚሰጠው አገልግሎት በጥራትና በብዛት ተመጣጣኝ ወይንም የበለጠ እንዲሆን ቅደም ተከተል አውጥቶ ጦርነቱን በኣሸናፊነት ለማካሄድ እንዲያስችል ማድረግና አገሪቱ ካለችበት አጣብቂኝ እንድትወጣ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ነው። ጦርነት ሲካሄድ የምርት ኃይልንና የአገልጎት አቅርቦትን ማሳደግ እንጅ መቀነስ የሚረዳው ጠላትን ነው። የአገልጎት ግድፈት የሚረዳው ጠላትን ነው። የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽፈት የሚያስመርረው ተራውን ሕዝብ ነው። እነዚህን ክስተቶች ጠላት እንደ መሳሪያ ይጠቀምባቸዋል።
የመንግሥት ባለሥልጣናት የቁሳቁስና የአገልግሎት አቅርቦት ቅደም ተከተል ያውጡ ሲባል ምን ማለት ነው? ለመከላከያ በተጣመረ መልኩ፤ ለብሄራዊ ደህነት፤ ከላይ እስከ ታች በሆነ መልኩ፤ በእቅድ ማሰራጨት ማለቴ ነው። ተደጋጋፊነትን ማጠናከር ማለቴ ነው። ለምሳሌ የአፋር ክልል የማያመርተውን የኦሮሞያ ክልል ሊያመርት ይችላል ወዘተ። ጦርነቱ ለአንዲት አገር ስለሆነ የምርትና የአገልግሎት ተደጋጋፊነት ወሳኝ ነው። በዚህ በኩል በክልሎች መካከል ጤናማ የሆነ የማምረትና አገግሎትን ለመከላከያውና ለተራው ሕዝብ ለማቅረብ የጦፈ ውድድር ቢፈጠር (healthy intra and inter regional competition) መልካም ነው እላለሁ።
የመንግሥት ባለሥልጣናት ለቅንጦት የሚወጣውን መዋእለንዋይ የመቀነስ ግዴታ አለበት። ተራውን ሕዝብ ቀበቶህን ጠበቅ አድርግ ብሎ ለመናገር መንግሥት ምሳሌና አርዓያ የመሆን ግዴታ አለበት።
የጦርነት ኢኮኖሚ ዘላለማዊ ሊሆን አይችልም። ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር ከተባለ ጦርነቱ በአጭር ጊዜ እንዲገባደድ የማድረግ እቅድና ስልት መኖር አለበት። ይህንን ብሄራዊ ግዴታ ለማድረግ የሚችለው ተራው ኢትዮጵያዊ አይደለም፤ ሊሆንም አይችልም። ልዩ ኃይሉ፤ ፋኖው፤ ሚሊሽያውና መከላከያውም ብቻውን ሊያደረገው አይችልም። ጦርነቱ አላማውን ስኬታማ አድርጎ ሕዝቡ ወደ ተራው ኑሮውና ስራው እንዲመለስ የማድረጉ ኃላፊነትና ግዴታ የመንግሥት ባለስልጣናት ነው። ጦርነቱ በረዘመ ቁጥር የሚሞተው ወገን፤ የሚባክነው ኃብት፤ የሚወድመው መሰረተ ልማት እየጨመረ ይሄዳል። ድሃዋና ኋላ ቀሯ ኢትዮጵያ አትችለውም።
የጦርነት ኢኮኖሚ ሲባል ሁሉም መሰረተ ልማት፤ ሁሉም የኢንዱስትሪና የምርት አቅርቦት ክፍል፤ የእርሻና የአገልግሎት ክፍል ይቆማል ማለት አይደለም። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የአሜሪካ ኢኮኖሚ ምርትና አቅርቦት ተመጣጣኝ ወይንም የላቀ እንደ ነበረ ጥናቶች ያሳያሉ። በተመሳሳይ፤ ኢትዮጵያ በተቻለ መጠን ራሷን መቻል ስላለባት በብዙ ልዩ ልዩ የኢንዱስትሪና የማምረቻ (የማኒፋክቸሪንግ) ክፍሎች ምርቶችን የማሳደግ እድልና እምቅ አቅም አላት፤ በተለይ የፍጆች እቃዎችን በአገር ቤት ለማምረት እቅድ ተልማ ተግባራዊ ማድረግ አለባት። ይህንን ነው፤ ጦርነቱን እንደ እድል እንጠቀምበት የምለው። እርግጥ ነው፤ በዚህ ጦርነት ዋናው ትኩርት የመከላከያውን ክፍል ማጠናከር ነው።
ምክንያቱም፤ መከላከያውና የኢትዮጵያ ሕልውና የአንድ ሳንቲም ግልባጭ ስለሆኑ ነው። በፌደራሉ መንግሥት የተመራው የአሚሪካ የኢንዱስትሪ እድገት ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ለማሸነፍ አስችሏታል። የአገር ውስጥ ምርት እድገት ወሳኝነትን ያሳያል። አሜሪካ ወደ ጦርነት ኢኮኖሚ አቅም ግንባታ የተሸጋገረችው ጃፓን አሜሪካን ለማጥቃት ከሞከረችበት ጊዜ ጀምሮ ነው። በጦርነቱ ኢኮኖሚ የአሜሪካ ሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር።
ኢትዮጵያም ይህንን የሴቶችን ተሳትፎ ለማጠናከር የምትችልበት እድል አላት። ሴቶች ለጦርነቱ የሚያደርጉት የስንቅ ዝግጅት ለኢንዱስትሪም አመች ሁኔታን እየፈጠረ ነው። ወንዶች ወደ ጦርነት ሲሄዱ ሴቶች ወደ ኢንዱስትሪ የሚሸጋገሩበትን እድል መፍጠር ወሳኝ እመርታዊ የስራና የልማት እድል ፈጣሪ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል። የመንግሥት ባለሥልጣናት ይህንን እድል እንዲያስቡበት እጠቁማለሁ።
አንዳንድ ተመልካቾች የጦርነት ኢኮኖሚ አድካሚና አምካኝ እንጅ የልማት መሰረት ሊሆን አይችልም ይላሉ። ትክክል ነው። መልሴ አጭር ነው። ኢትዮጵያ ጦርነቱን አልጀመረችም። ጦርነቱን የጀመረውና አምካኝ ሆኖ የማየው ሕወሓትን/ ወያኔን ነው። ያልተቆጠበ ድጋፍ የሚሰጠው የባይደን መንግሥት ነው። ጦርነቱን ወደ አፋርና ወደ አማራው ክልል ገፍቶ ለብዙ ሽህዎች እልቂት፤ ቢያንስ በአማራው ክልል ብቻ ለሰባት ሽህ ትምህርት ቤቶች ውድመት ምክንያት የሆነው ይህ ከሃዴና ጨካኝ ቡድን ነው። ከሱዳንና ከግብጽ ጋር የሚዶልተው ጠላት ህወሓት/ወያኔ ነው። የሞራል ድፋፍ የሚሰጠው ደግሞ የባይደን መንግሥት አመራር ነው።
ይህ ጨካኝ፤ አረመኔና ከሃዲ ቡድን ከጦርነት ይልቅ እርቅና ሰላምን እፈልጋለሁ ብሎ ቃል ቢገባ ኖሮ ለትግራይ እናቶችና ወጣቶች ከፍተኛ በረከት ያደርግ ነበር። ግን ይህንን ሊያደርግ የሚፈልግ ሆኖ አላየውም። ማኒፈስቶውን አልቀየረውም፤ እንዲያውም በአዲስ መልክ ሂሳብ አወራርዳለሁ ብሎ የፈረደው በጎንደሬው ሕዝብ ላይ ነው።
ከአጥፊነት ወደ እርቅና ወደ ሰላም ለመመለስ ግፊት ማድረግ ያለበት ኢላማ የሆነው የጎንደር፤ የዎሎ፤ የአፋር ሕዝብ አይደለም። የትግራይ ሕዝብ ጫና የሚያደርግበት ወቅት ዛሬ ነው። በጭካኔ የሚሰቃየው፤ በየቀኑ የሚሞተው የአፋር ወይንም የአማራ ህዝብ ተወረረ እንጅ ትግራይን አልወረረም። መከካለያም ወራሪውን ታገለ እንጅ የትግራይን ወጣቶች አልጨፈጨፈም።
ጦርነቱ በሰላም መፍትሄ እንዲያገኝ ምኞትና ፍላጎት ካለ፤ የትግራይ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የምእራብ አገር ባለሥልጣናትም ቢሆን ህወሓትን/ወያኔን ለእልቂቱና ለጥፋቱ ሳያመነቱ ይኮንኑት ነበር። የሚሰሩት ግን ተጻራራውን ነው። የባይደን መንግሥት ተጨማሪ ጫና በኢትዮጵያ ላይ ቢያዳርግ አልደነቅም። አጀንዳቸው ሌላ ነው። አገልጋይና ታዛዢ ቡድን ይፈልጋሉ።
ከላይ እንዳቀረብኩት፤ የጦርነት ኢኮኖሚ ተመን የሚለካው በመዋእለንዋይ ወጭና ፈሰስ ብቻ አይደለም። የመሰረተ ልማት ውድመት ግዙፍ ነው። የንጹህ ዚጎች እልቂት በገንዘብ ብቻ ሊተመን አይችልም። የቆሰልቱን ለማከም ወጭው ብዙ ነው፤ ወዘተ።
በመሆኑም ያለፈው ዓመት በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ የጨለማ ዓመት፤ የውድመት ዓመት፤ የእልቂት ዓመት፤ የመፈናቀል ዓመት፤ የክህደት ዓመት ወዘተ ተብሎ ሊሰየም ይችላል። ይህን በኢትዮጵያ ታሪክ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ጥቁር ቀለም የመራው አጥፊ ኃይል ህወሓት/ወያኔ ነው። ይህ አጥፊ፤ አድካሚና ከሃዲ ቡድን ካልተወገደ ሰላም ሊኖር አይችልም።
ማጠቃለያ
አንደኛ፤ የችግሩ እምብርት ህወሓት/ወያኔ በምእራብ አገሮች፤ በተለይ በአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ የጸነሰው የማይታረቅ የዘውግ ልዩነት መርህ አሁንም እንደ ተዘረጋ መሆኑ ነው። ይህንን አጥፊ መርህ የሚጋራው ኦነግ ሸኔ ነው። ይህ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ኃይል ደግሞ ህወሓትም ቢጠፋ ራሴ እተካዋለሁ ወደሚል ድምዳሜ ተሸጋግሯል። ይህም አጥፊና አድካሚ ኃይል የኢኮኖሚ ጦርነት በማካሄድ ላይ ይገኛል። ትኩረቱ በመስረተ ልማት ውድመት ላይ ነው።
ሁለተኛ፤ የኢትዮጵያ የጦርነት ኢኮኖሚ ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ገጥመውታል። እነዚህን ተግዳሮቶች እንደ እድል ፈጣሪ አድርጌ ስገመግማቸው የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ትኩረት ማድረግ ያለበት የአገሪቱን የማምረት አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማቀድና መምራት ነው። ኢትዮጵያ ራሷን የምትችልበትን መንገድ ስልታዊና እቅድ ባለው መልኩ ካቀናጀች ፈተናውን ልትወጣው ትችላለች።
ሶስተኛ፤ ራስን መቻል በምኞት ብቻ ስኬታማ ሊሆን አይችልም። ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፤ የሰው ኃይል፤ ገቢና ሌላ የመዋእለንዋይ ኃብት፤ ብድር ካስፈለገ ከአፍሪካ ተቋማት፤ ለምሳሌ ከአፍሪካ የልማት ባንክ በዝቅተኛ ወለድ በሚከፈልና ለምርት ጭማሬ ለሚያበረክቱ ኢንዱስትሪዎች፤ ለዘመናዊ እርሻዎችና ተመሳሳይ የኢኮኖሚ ክፍሎች በመበደር ጭምር ራሷን የመቻል አቅሟን ለማጠናከር ትችላለች። ራሷን ከመቻል ውጭ ግን ሌላ አማራጭ የላትም።
አራተኛ፤ ስርዓቱ ራሱ አምካኝና አድካሚ መሆኑን መረዳት ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ ስር ነቀል የሆነ የአስተሳሰብና እድል የመፍጠር ባህል ያስፈልጋታል። ሁሉም ሌባ፤ ሁሉም ሙሰኛ፤ ሁሉም የመደለል ሰለባ ሁሉም መንደርተኛ፤ ሁሉም ዘውገኛ ወዘተ የሆነበት ኢኮኖሚ በጦርነትንም ባይደማ፤ እመርታዊ ልማት ሊመሰርት አይችልም። ለአስተሳሰብ ለውጥ ቦታ ይሰጠው የሚል ምክር እለግሳለሁ።
በመጨረሻ፤ “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንዲሉ እኛ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት የምናምነው ሁሉ መረባረብ ያለብን፤ ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደ ጎን ትተን፤ ኢትዮጵያ ከጥገኝነት ወጥመድ መጥቃ ወጥታ ራሷን የቻለች አገር እንድትሆን መስራት ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!! ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!!
September 15, 2021
References you can access on economic war and the war economy
Arellano, M., and Bond, S. (1991) “Some Tests of Specification for Panel Data: Monte Carlo Evidence and an Application to Employment Equations.” Review of Economic Studies 58 (2): 277–97.
Auvinen, J. (1997) “Political Conflict in Less Developed Countries, 1981–89.” Journal of Peace Research 34 (2): 177–95.
Barro, R. J. (1991) “Economic Growth in a Cross Section of Countries.” Quarterly Journal of Economics 106 (2): 407–44.
Barro, R. J., and Lee, J.-W. (1993) “Losers and Winners in Economic Growth.” NBER Working Paper No. 4341.
Baum, C. F. (2019) “Dynamic Panel Data Modeling.” In P. Atkinson, S. Delamont, A. Cernat, J. W. Sakshaug, and R. A. Williams (eds.) SAGE Research Methods Foundations. Available at http://methods. sage pub.com/foundations.
Bolt, J.; Inklaar, R.; de Jong, H.; and van Zanden, J. L. (2018) “Rebasing ‘Maddison’: New Income Comparisons and the Shape of Long‐Run Economic Development.” Maddison Project Working Paper No. 10.
Burdekin, R. C. K. (2006) “Bondholder Gain from the Annexation of Texas and Implications of the U.S. Bailout.” Explorations in Economic History 43 (4): 646–66.
Cederman, L.-E.; Gleditsch, K. S.; and Wucherpfennig, J. (2017) “Predicting the Decline of Ethnic Civil War: Was Gurr Right and for the Right Reasons?” Journal of Peace Research 54 (2): 262–74.
Coyne, C. J., and Mathers, R. L., eds. (2011) The Handbook on the Political Economy of War. Northampton, Mass.: Edward Elgar.
Ellingsen, T., and Gleditsch, N. P. (1997) “Democracy and Armed Conflict in the Third World.” In K. Volden and D. Smith (eds.), Causes of Conflict in Third World Countries, 69–81. Oslo: North‐South Coalition and International Peace Research Institute.
Fabro, G., and Aixala, J. (2012) “Direct and Indirect Effects of Economic and Political Freedom on Economic Growth.” Journal of Economic Issues 46 (4): 1059–80.
Farr, W. K.; Lord, R. A.; and Wolfenbarger, J. L. (1998) “Economic Freedom, Political Freedom and Economic Well‐Being: A Causality Analysis.” Cato Journal 18 (2): 247–62.
Ferguson, N. (2006) “Political Risk and the International Bond Market between the 1848 Revolution and the Outbreak of the First World War.” Economic History Review 59 (1): 70–112.
Frey, B. S., and Waldenstrom, D. (2004) “Markets Work in War: World War II Reflected in the Zurich and Stockholm Bond Markets.” Financial History Review 11 (1): 51–67.
Gleditsch, N. P.; Wallensteen, P.; Eriksson, M.; Sollenberg, M.; and Strand, H. (2002) “Armed Conflict 1946–2001: A New Dataset.” Journal of Peace Research 39 (5): 615–37.
Gwartney, J.; Lawson R.; and Block, W. (1996) Economic Freedom of the World: 1975–1995. Vancouver: Fraser Institute.
Gwartney, J.; Lawson, R.; and Hall, J. (2017) Economic Freedom of the World, 2017 Annual Report. Vancouver: Fraser Institute.
Hansen, L. (1982) “Large Sample Properties of Generalized Method of Moments Estimators.” Econometrica 50 (3): 1029–54.
Harbom, L.; Melander, E.; and Wallensteen, P. (2008) “Dyadic Dimensions of Armed Conflict, 1946–2007.” Journal of Peace Research 45 (5): 697–710.
Hegre, H.; Ellingsen, T.; Gates, S.; and Gleditsch, N. P. (2001) “Toward a Democratic Civil Peace? Democracy, Political Change, and Civil War, 1816–1992.” American Political Science Review 95 (1): 33–46.
Higgs, R. (2006) “Regime Uncertainty: Why the Great Depression Lasted So Long and Why Prosperity Resumed after the War.” In Depression, War and the Cold War, 3–29. New York: Oxford University Press.
Jong‐A‐Pin, R. (2009) “On the Measurement of Political Instability and Its Impact on Economic Growth.” European Journal of Political Economy 25 (1): 15–29.
Maddison, A. (1995) Monitoring the World Economy 1820–1992. Paris: OECD.
________ (2001) The World Economy: A Millennial Perspective. Paris: OECD.
_________ (2006) The World Economy: Historical Statistics. Paris: OECD.
Marshall, M. G., and Elzinga‐Marshall, G. (2017) Global Report 2017: Conflict, Governance and State Fragility. Vienna, Va.: Center for Systemic Peace.
Mueller, J. (1989) Retreat from Doomsday: The Obsolescence of Major War. New York: Basic Books.
Murdoch, J. C., and Sandler, T. (2004) “Civil Wars and Economic Growth: Spatial Dispersion.” American Journal of Political Science 48 (1): 138–51.
Murphy, R. H., and Lawson, R. A. (2018) “Extending the Economic Freedom of the World Index to the Cold War Era.” Cato Journal 38 (1): 265–84.
Nickell, S. (1981) “Biases in Dynamic Models with Fixed Effects.” Econometrica 49 (6): 1417–26.
Pecquet, G. M., and Thies, C. F. (2010) “Texas Treasury Notes and the Mexican‐American War: Market Responses to Diplomatic and Battlefield Events.” Eastern Economic Journal 36 (1): 88–106.
Roeder, P. A. (2018) National Secession: Persuasion and Violence in Independence Campaigns. Ithaca, N.Y.: Cornell University Press.
Roll, R., and Talbott, J. (2003) “Political Freedom, Economic Liberty, and Prosperity.” Journal of Democracy 14 (3): 75–89.
Sarkees, M. S., and Wayman, F. (2010) Resort to War: 1816–2007. Washington: CQ Press.
Schneider, G., and Troeger, V. E. (2006) “War and the World Economy: Stock Market Reactions to International Conflicts.” Journal of Conflict Resolution 50 (5): 623–45.
Small, M., and Singer, J. D. (1982) Resort to Arms: International and Civil War, 1816–1980. Beverly Hills, Calif.: Sage.
Thies, C. F. (2007) “Political and Economic Freedom Reconsidered.” Journal of Private Enterprise 22 (2): 95–118.
Weidenmier, M. D. (2002) “Turning Points in the U.S. Civil War: Views from the Grayback Market.” Southern Economic Journal 68 (4): 875–90.
Weidenmier, M. D., and Oosterlinck, K. (2007) “Victory or Repudiation? The Probability of the Southern Confederacy Winning the Civil War.” NBER Working Paper No. 13567.
Willard, K. L.; Guinnane, T.; and Rosen, H. S. (1996) “Turning Points in the Civil War: Views from the Greenback Market.” American Economic Review 86 (4): 1001–18.
Xu, Z., and Li, H. (2008) “Political Freedom, Economic Freedom, and Income Convergence: Do Stages of Economic Development Matter?” Public Choice 135 (3–4): 183–205.
Zanger, S. C. (2000) “A Global Analysis of the Effect of Political Regime Changes on Life Integrity Violations, 1977–93.” Journal of Peace Research 37 (2): 213–33.