፪ቱምልክ ነበሩ ፤ናቸዉ – ማላጂ

በአስራ ዘጠኝ መቶ መማንያ ዓ.ም.አጋማሽ ሚኒል መፅሄት ላይ በወጣ ፅሁፍ የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጀ/ል ቁምላቸዉ ደጀኔ  በጊዜዉ ይኖሩበት ከነበረዉ የአሜሪካ ግዛት ሆነዉ በሰጡት አስተያየት ወይም ትንቢት ት.ህ.ነ.ግ. ራሱን በራሱ የሚጠፋበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን መግለጻቸዉን  በዚህ ዓመት መመልከት ችያለሁ ፡፡

ይህ ዕዉነተኛ ግምት እና ትንቢት ዕዉን ለመሆን በተጨባጭ ማየት ሳይሆን የኒህን ከፍተኛ የጦር መሪ ብቃት እና አርቆ አስተዋይነት የሚያሳይ  ብሩህ አስተሳሰብ እና ጥልቅ ግንዛቤ እንደነበራቸዉ ነዉ፡፡

ጀ/ል ቁምላቸዉ በህይዎት ኑረዉ ይህን በዕዉቀት እና በዕዉነት የተነበዩትን ሁነት ቢያዩ ኑሮ ርግጥ  የሁሉም ዕዉነተኛ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ታላቅ ድስታ በሆነ ነበር ፡፡

ኢትዮጵያን ከማፍረስ አልፎ ለቀጠናዉ ስጋት የመሆን ምኞት እና ፍላጎት አንግበዉ አጥፍቶ ከመጥፋት ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸዉን ላለፉት 27 ዓመታት ላስተዋለ ዛሬ ላይ የሚያደርጉት ሁሉ የዕኩያን የጥፋት አረም ቅጥያ  እና የጀነራሉ ዕዉነተኛ እና ሀቀኛ ጥልቅ ትንታኔ ዉጤት መሆኑን እንረዳለን፡፡

የኢትዮጵያ ጠላቶች ዜጎችን በማንነታቸዉ እና ኢትዮጵያዊ በመሆናቸዉ  በህይዎት እያሉ ቆዳ  ልጠዋል፣ አቃጥለዋል፣ ቀብረዋል፣ በበሽታ ብዙዎችን መርዘዋል ፣ዘረፋዉን በትግል ወቅትም ፣ በስልጣንም እንዲሁም “ከፉ ሞቶም ይገላል ”እንዲሉ በዓመታት የህዝቦች ትግል እና መስዋዕትነት ወደ መቃብር እየሄዱም ይገድላሉ፣ያስገድላሉ ፤ይዘርፋሉ ያዘርፋሉ  ያአሁኑ የኢትዮጵያ መድር እነርሱ የዓማራ የሚሉት ሁሉ  አፈሩ እንዲቃጠል፤ ዉሃዉ / ጅረቱ እንዲነጥፍ፤ እንስሳት ከምድረ ገጽ እንዲጠፉ  የዘረፉትን ይዘዉ ፤ያልቻሉትን ገድለዋል፤ ለዚህም ቀን ተሌት ሳይታክቱ ከሳጥናኤል ጋር ሳይቀር ህብረት ለመፍጠር  የማይፈነቅሉት ድንጊያ ፤የማይበጥሱት ቅጠል የለም ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወያኔና ትግሬ | መስፍን ወልደ ማርያም

ይህ በቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግስት በተለይም በሊ/መንበር መንግስቱ ኃይለ ማርያም ሆኑ እኝህ ከፍተኛ  የጦር መኮንን አንድም ሳይቀር ተናግረዋል ሰሚ ባያገኙም ፡፡

እዚህ ላይ ት.ህ.ነ.ግ አስቀድሞ በጠላትነት ገና ከጥንስሱ 1967/68  ዓ.ም. ጠላቴ ያለዉን ኢትዮጵያዊ/ ዓማራ  ለማጥፋት ከዚያ አስከዚህ በይፋ የገፋበት የአጥፍቶ ጠፊነት የጥላቻ ዘመቻዉን  ማቀጣጠሉ የሚጠለፍበትን ወጥመድ እያሳጠረ እና እያጠበቀ መሆኑ የያኔዉ (1968.ዓ.ም.) የጥላቻ  እና የጥፋት ስምምነቱን እያደሰ ስለመሆኑ እሱም እንደ ጀነራሉ በቅንነት ባይሆንም የተነሳበት አጥፍቶ የመጥፋት ዓላማ ነዉ እና ትክክል እንደነበር እና እንደሆነ በኢትዮጵያ እና በዓለም ህዝብ ፊት  ሲያረጋግጥ የትግራይ/ ትግሬ ወረራ በይፋ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሲያዉጅ ከራሱ እና ህዝቤ ከሚለዉ ዉጭ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ሆነ ኢትዮጵያዊ የሚባል ህዝብ ወትሮም ሆነ አሁን መንም አለመሆኑን አረጋጧል፡፡

 

አንድነት ኃይል ነዉ ”

ማላጂ

 

 

 

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share