ውድ ወንድሜ ታማኝ በየነ፤  አህያውን ፈርተህ ዳውላውን? – መስፍን አረጋ

Tsmsgn 631x499 ውድ ወንድሜ ታማኝ በየነ፤  አህያውን ፈርተህ ዳውላውን?  መስፍን አረጋ

ውድ ወንድሜ ታማኝ በየነ፣ ወያኔ አረጋዊ እናትህን ማጎሳቆሉ ከፍተኛ ቁጭት ውስጥ ሊከት የሚገባው አንተን ወይም የቅርብ ዘመዶችህን ብቻ ሳይሆን አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ነው፡፡  ለአማራ ሕዝብ ደግሞ ሞት ብቻ ሳይሆን የቁም ሞት ነው፡፡

ነገር ግን፣ ወያኔ አረጋዊ እናትህን በማጎሳቆሉ ሊወቀስ አይችልም፣  ምክኒያቱም ያደረገው የባሕሪውን ነውና፡፡  የአሲል ዕባብ የተፈጥሮ ባሕሪ ሲያቃጡበት መጥመልመል፣ ሲዞሩለት መንደፍ ስለሆነ፣ ጥፋተኛው ወይም ስህተተኛው ተነዳፊው ግለሰብ እንጅ ነዳፊው ዕባብ አይደለም፡፡  ወያኔ የተፈጠረው ደግሞ ምቹ አጋጣሚ እየጠበቀ የአማራን ሕዝብ በመንደፍ ከአጋም እንደተጠጋ ቁልቋል ዘላለም ለማስለቀስ ብቻና ብቻ ነው፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ይህን የደደቢት ዕባብ እተፈጠረበት እደደቢት ድረስ ሂዶ ራስ፣ ራሱን ቀጥቅጦ ካልገደለውና መቸም እንደማይነሳ ካላረጋገጠ በስተቀር እንዳለቀሰ ይኖራታል፡፡

ስለዚህም ወንድሜ ታማኝ በየነ፣ መውቀስ ያለብህ ውድ እናትህን የነደፋቸውን ዕባብ ሳይሆን፣ እንዲነድፋቸው ያመቻቸውን ሰው ነው፡፡  ያ ሰው ደግሞ ስሙን በክፉ ላለማንሳት እጅጉን የምትጠነቀቅለት ኦቦ ዐብይ አሕመድ ነው፡፡  ሰምተኸኛል ወንድሜ ታማኝ?  እናትህን ያስነደፋቸው ኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ ነው፡፡

ስለዚህም ወንድሜ ታማኝ፣ ዕባቡን በጀርባው ተሸክሞ፣ እያንከባከበ እናትህ ደጃፍ ድረስ ያመጣውን አህያውን ዐብይ አሕመድን እንጅ፣  ዳውላውን ወያኔን አትኮንን፡፡  ወያኔንማ ያማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ጣዕረ ሞት ውስጥ ከተውት ነበር፣ ዐብይ አሕመድ በፍጥነት እንዲያንሰራራ አደረገው እንጅ፡፡

እስኪ ልጠይቅህ ወንድሜ ታማኝ፡፡  ዳውላውን ወያኔን ያለ የሌለ ውርጅብኝ እያወረድክበት፣ አህያውን ዐብይ አሕመድን ለማውገዝ ቅረቶ ለመተቸት እንኳን የምታቅማማው ለምንድን ነው?  ዐብይ አሕመድን ለመተቸት እንኳን የማትፈልገው፣ ዐብይ አሕመድ ባለፉት ሦስት ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመውና ያስፈጸመው ወንጀል፣ ወያኔ በሃያ ሰባት ዓመታት ባማራ ሕዝብ ላይ ከፈጸመውና ካስፈጸመው ወንጀል በብዛትም ባሰቃቂነትም አያሌ እጥፍ እንደሚበልጥ ጠፍቶህ እንዳልሆነ በርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ዐብይ አሕመድን ለመተቸት እንኳን የማትፈልገው፣ እንደ አንዳርጋቸው ጽጌና ብርሃኑ ነጋ የሰሜን ጠል ፖለቲካ አቀንቃኝ ስለሆንክ እንዳልሆነ ደግሞ የረዥም ዘመን የትግል ታሪክህ በግልጽ ይመሰክራል፡፡ ዐብይ አሕመድ ለመተቸት እንኳን የማትፈለገው፣ በጥቅም ተገዝተህ ነው ለማለት ደግሞ በጣም ይቸግራል፣ ምንም እንኳን እግር ሂዶ፣ ሂዶ ጭቃ መግባቱ ያለ፣ የነበረና የሚኖር ቢሆንም፡፡

ስለዚህም ዐብይ አሕመድን ለማውገዝ ቀርቶ ለመተቸት የማትፈልገው ስለምትፈራው ነው ማለት ነው፡፡   ነገር ግን፣ ዐብይ አሕመድን የምትፈራው ለምንድን ነው?  አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ብርሃኑ ነጋና መሰሎቻቸው ሁርንጭላወች ስለሆኑ አህያውን ቢፈሩ አይፈረድባቸውም፡፡  አንተ ታማኝ በየነ ግን አህያውን የምትፈራው ለምንድን ነው?

አህያውን የምትፈራው ባንድ ወቀት አህያው አጠገብ ተደፍተህ ስለነበረ ከሆነ በጣም ተሳስተሃል፡፡  ያን ቀን የተደፋኸው ኢትዮጵያ እግር ሥር እንጅ አህያ ኮቴ ሥር አልነበርም፡፡  እርግጥ ነው፣ አህያው አህያ ስለሆነ፣ የወደቅከው እሱ እግር ሥር ሊመስለውና ሊበሻቀጥብህ ይችላል፡፡  እሱ ኮቴ ሥር አለመደፋትህን ግን አህያ ያልሆነ ሁሉ ያውቀዋል፡፡  ስለዚህም በዚህ በኩል አሳብ ሊገባህ አይገባም፡፡

አማራን በመግደል ኢትዮጵያን መግደል የሚቻለው በኦነግ፣ በወያኔ፣ በዐረብ ወይም በነጭ ኃይል ሳይሆን አማራን መስሎ አማራን በማደንዘዝ ብቻና ብቻ ነው፡፡  ይህን እውነታ በደንብ የተረዱ ዐብይ አሕመድና ለማ መገርሳ በቀመሙት አማራን የማደንዘዣ መርዝ ደንዝዘህ የነበርከው አንተ ታማኝ በየነ ብቻ ሳትሆን ሁላችንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያኖች ነበርን፡፡  ዐብይ አሕመድን ስናይ፣ እናይ የነበረው የምንመኛትን ኢትዮጵያን ስለነበር፣ እግሩ ሥር ከመውደቅ አልፈን ደረታችንን ለጥይት ልንሰጥለት ሙሉ ፈቃደኞች ነበርን፡፡   አብይ አሕመድ ግን ክብር የማይወድለት አህያ ስለሆነ፣ የኢትዮጵያን አልጋ ትቶ የኦነግን ዐመድ መረጠ፡፡  እኛም ዐብይ አሕመድ፣ ዐብይ አሕመድ፣ ያህያ ሥጋ ባልጋ ሲሉት ባመድ በማለት ክብረቢስነቱን ነገርነው፡፡

 

በዲስኩሩ አክብረን ብናወጣው ላይጌ
በምግባሩ ዘቅጦ ወረደ እታችጌ
ተነስ አይባልም ክብረቢስ ባለጌ፡፡

 

እኔን ራሴን መስፍን አረጋን ብንወስድ፣ በዐብይ አሕመድና በለማ መገርሳ መርዝ ተመርዠ አቅሌን በማጣት ሙሉው ከክፍሎቹ ድምር ይበልጣል (the whole is greater than the sum of its parts) የሚለውን መሠረት አድርጌ የሚከተለውን መወድስ እስከመግጠም ደርሸ ነበር፡፡

 

ጎጠኛ ማይም ነው ደንቆሮ የማያቅ
ከክፍሎቹ ድምር ሙሉው እንደሚልቅ፡፡
ይህንን እውነታ ሲገልጥ አሳምሮ
መደመር ብሎታል ዐብይ ዘአጋሮ፡፡
የሥሁልን ሽንሽን ቴድሮስ እንደሰፋ
የመለስን ክልል ዐብይ አህመድ ያስፋ፡፡

 

ዐብይ አሕመድ ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚያደርጋቸው ንግግሮች ሁሉ ምጸቶች (irony) እንደሆኑና፣ በዐብይ አሕመድ ቋንቋ መደመር ማለት መቀነስ ማለት እንደሆነ ስገነዘብ ግን፣ ዐብይ አሕመድን ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ለመቀነስ በምችለው ሁሉ ለመታገል ቆርጨ ተነሳሁ፡፡

 

ዐብይ አህመድ አሊ የኦነጉ ኦቦ
አፉና ምግበሩ ሐራምባና ቆቦ፡፡
ያብይ አህመድ ስሌት፣ ኦነጋዊ ቀመር
በተግባር ቀንሶ፣ በወሬ መደመር፡፡

 

ዐብይ አሕመድን ስመለከት፣ የምመለከተው የምመኛትን ኢትዮጵያን እንደልነበር፣  አሁን ላይ ግን ይህን ሰው ስመለከት የምመለከተው፣ አገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ መቸም አይታው የማታውቀው እጅግ ሲበዛ አጭበርባሪ፣ በዚያ ላይ ደግሞ እጅግ ሲበዛ አረመኔ የሆነ ኦነጋዊ ግለሰብ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድን ስመለከት ባይነ ሕሊናየ ላይ የሚመጡብኝ፣ ወለጋ ውስጥ ቤት ተዘግቶባቸው እናቴ፣ አባቴ እያሉ እያለቀሱ በአቶን እሳት የተንጨረጨሩት የአማራ ሕፃናት፣ አሩሲ ውስጥ ሬሳቸው በሞተር ሳይክል የተገተተው አማሮች፣ ሻሸመኔ ላይ እንደ ዱላ የተጨፈረባቸው ከአማራ አስከሬኖች የተቆረጡ እጆችና እግሮች፣ አጣየ ላይ የተዘረከቱት የአማራ ማሕጸኖች፣ እንዲሁም መተከል ላይ ደማቸው እንደ ጠጅ የተጠጣው፣ ሥጋቸው እንደ ብርንዶ የተበላው የአማራ ሽሎች ናቸው፡፡  ይበልጥ ቆሽቴን የሚያደብነው ደግሞ እነዚህ ሁሉ አሰቃቂ ወንጀሎች በተፈጸሙ ማግሰቱ ዐብይ አሕመድ በሰፊው የአማራ ሕዝብ ላይ የሚያፌዘው ማፌዝ ነው፡፡ የአማራን ሞት ከዝንብ ሞት እንደሚቆጥረው ለማሳየት ሲል ብቻ፣ በአማራወች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ እስኪፈጸም ድረስ ሥራየ ብለ ይጠብቅና፣ በነገታው አዳባባይ ወጥቶ አበባ ይተክላል፣ ወይም ደግሞ በፌስቡክና በትዊተር ስለ አበባ ውበት ይደሰኩራል፡፡  የአማራን ሕዝብ ያቆስልና፣ ማቁሰሉ ስለማያረካው በቁስሉ ላይ እንጨት ይሰድበታል፡፡

ዐብይ አህመድ የጭቆናን ምንነት በቅጡ ሊረዳ በማይችልበት ለጋ እድሜው “ያማራ ጨቋኞችን” ለመታገል ጫካ ገብቶ የወያኔን ጡት እየጠባ ባማራ ጥላቻ ተመርዞና ተሰቅዞ ያደገ፣ አማራን በማጥፋት አማራዊ ናት የሚላትን ጦቢያን አፈራርሶ በሷ መቃብር ላይ የኦሮሞ አጼጌ (Oromo empire) ለመመሥረት ቆርጦ የተነሳ፣ በዚያ ላይ ደግሞ በማንነቱ ምክኒያት በሥርሰደድ (chronic) የስነልቦና በሽታ የሚሰቃይ ኦነጋዊ አውሬ ነው፡፡  ስለዚህም፣ የአማራ ሕዝብ ለሕልውናው ሲል ይህን ኦነጋዊ አውሬ መንቀል አለበት፡፡  መንቀል ያለበት ደግሞ ሁለተኛ እንዳይበቅል ከሥሩ መንግሎ ነው፡፡

ስለዚህም ወንድሜ ታማኝ በየነ፣ ባንድ ወቅት ከሥሩ ወድቄ ነበር ብለህ ዐብይ አሕመድን አትፍራው፡፡  ምን ማለት እንዳለብህ ላንተ ለመናገር ባልደፍርም፣ ብትለው ደስ የሚለኝ ግን የሚከተለውን ነው፡፡  በዲስኩርህ ደንዝዠ የኢትዮጵያ መሲህ መስለኸኝ ከእግርህ ሥር ወድቄ ነበር፡፡  አሁን ግን የኢትዮጵያ መላከሞት መሆንህን ከተግባርህ ስለተረዳሁ፣ ለኢትዮጵያ ሥል ከሥርህ እንደወደኩ ለኢትዮጵያ ስል ከሥርህ እመነግልሃለሁ በለው፡፡  ልትመነግለው ከፈለክ ደግሞ፣ ወያኔን ለመመንገል ከፍተኛ ሚና እንደተጫወትክ፣ ዐብይን ለመመንገል ከፍተኛ ሚና የመጫወት እምቅ ችሎታ እንዳለህ ነጋሪ አያስፈልግህም፡፡  ዐብይ አሕመዳውያን ደግሞ ከዐብይ አሕመድ ሥር ወድቀኻል በማለት ሞራልህን ለመስበር የሚሞክሩት፣ ዐብይ አሕመድን መንግለህ ለመጣል ማድረግ የምትችለውን ወሳኝ አስተዋጽኦ አሳምረው ስለሚያውቁና እንደጦር ስለሚፈሩት ነው፡፡

ባሁኑ ወቅት የአማራ ሕዝብ ትልቁ ጠላት ዐብይ አሕመድ እንጅ ወያኔ አይደለም፡፡  ወያኔ ማለት በዐብይ አሕመድ ላይ የተጫነ ዳውላ ማለት ስለሆነ፣ አህያው ከተወገደ ዳውላው የትም አይደርስም፡፡  የአማራ ሕዘብ ከዐብይ አሕመድ አፍዝ አደንግዝ ከተላቀቀ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

13 Comments

 1. አቶ መስፍን አረጋ ታሞዋል !!! በ እጅጉ ታሙዋል ሁለት ፟ ሶስት ጠበል መነከር ስለሚያስፈልገው ዘመድ የሆንክ እርዱት እባካችሁ ፡፡

  • It is Aligaz Ougaz “which” is seriously sick. Which is used for animals and that is why I used to express Aligaz as an animal that blindly becomes a pet to one vampire known as Abiy Giragn Ahmed. Abiy has so many megajawoch which are used to carry his zigntil that is used to destroy Ethiopia. It is irritating to see such puppets.

 2. I found this comment clearly, genuinely , straightforwardly and constructively rational and critical !
  I strongly believe that if we are seriously concerned about the real change of a political system that must negate the very criminal political system of EPRDF/Prosperity and bring about a gear change in all aspects of peoples’ lives, we desperately need to be courageous to talk with each other to this extent !

 3. መስፍን አረጋ የሚፅፈዉ ዉሃ የሚቋጥርና በማስረጃ የተረጋገጠ ነው። ሀቁን ለመናገር ወደሁዋላ አይልም። የአብይ አህመድን የስነልቡና ወቅር በደንብ ተረድቶታል። አብይ የሚይዘውን እና የሚጨብጠዉን በደንብ የማያዉቅ ደፋር ያልሆነ ገዢ ነው።

 4. መስፍን አረጋ የጻፈው ቢይምህም ያየነውንና የሰማነውን ነው። ታማኝ በየነ የኢትዮጵያን በተለይም የአማራን ፖለቲካ ካሳከሩት አላዋቁዎች መሀል አንዱ ነው። ስልጠናው የህዝብ እይታን ስለሚፈልግ ጭር ሲል አይመቸውም። አማራ ላለመባል አጥብቆ ይጠነቀቃል አማራ እግሩ በረገጠበት የምድር ሲኦል ሲሆንበት ድምጹ አይሰማም። አማራው በነገዴ መኖር አልቻልኩም ሲለው አማራ ነኝ አትበል ብሎ ይቆጣሀል በዚህ ሳያበቃ የአማራ ክልልን ወጣቶች ሰብስቦ ሊያደንዝዝ ይፈልጋል። ሰውዬው የጎንደር ትውልዱን እንደ አማራ password በመጠቅም ብዙ ጉዳት ያደረሰ ነው። በኢሳትና በግምቦት 7 የአንዳርጋቸውና የብርሀኑ ሎሌ ሁኖ የሰራውን ጉዜ ሱገኝ በዝርዝር ይወጣል። ማይክ ተከልክሎ እረፍ ካልተባለ ጥፋቱ ይቀጥላል እራሱን እንዲያውቅ ቢደርግ ጥቅሙ ለራሱ ነበር።

 5. የወያኔን የጥፋት ጥግ የማየው በኦሮሞ የሸኔን ፅንፈኞች በአማራም የአማራ ሸኔዎችን አሰልፏል:: በእነዚህ ባንዳዎች በኢትዮጵያ ላይ ብዙ ጉዳት አስከትሏል:: የወያኔ እቅድ ዐቢይን አውርዶ እንደገና ለአመታት የኢትዮጵያ ዝርፊያ ላይ እንደገና ለመሰማራት ነው:: ዐቢይ አልተቻለም: ሰኔ 14 ሚሊዮኖች ለ5 አመታት መርጠውታል:: ፋይሉ ተዘግቷል::
  ወያኔ የማመሰግንበት አንድ ብቸኛ ምክንያት ነካክታ ነካክታ፣ ቆስቁሳ ቆስቁሳ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነትና የሀገር ፍቅር ስሜት ከማይመለስበት የከፍታ ማማ ላይ ሰቀላዋለች::የዐቢይም መንግስት እጅግ ጠንካራ እንዲሆን ረድታዋለች::ሙሾ ደርድሩ አልቅሱ losers can’t win? ያለው ማን ነበር::

 6. የዶ/ር ዐቢይ አህመድ ድቤ ደለቀ፤ ዝም አልነው
  የአንዳርጋቸውን አነሳ፤ ዝም አልነው
  የታማኝን አነሳ
  የሚቀጥለው የማ ይሆን?
  ዲባቶ መስፍን አረጋ ወልደ ዮሐንስ ሥራ ፈት ነው።
  አንደበቱ ያልተገራ ነው፤
  ስም ማጥፋት፣ ሰው ማማትን ውሎ አድርጎታል።
  የአገሩ ልጅ አሳምነው ጽጌ መንግሥት ሥልጣን ካልያዝኩ ብሎ ሲንጠራራ መገደሉ
  ዲባቶን ትልቅ ድብት ጥሎበታል።
  ተከታዮቹ እነ የለምጨኑ ናቸው። እነ ጠገናው። እነ ብርሌ። ፡)

  • አለምዬ ከመስፍን ጋር ትውውቅ አታጡም ሳያስቀይምሽም አልቀረም በግል ማለቴ ነው። በተረፈ የፊዚክስ ፕሮፌሰር መሆኑን አምልጦሽ ነግረሽናል እንዲህ አይነቱን ሰው ነው ስለሀገሩ ተብከንኮ ለጻፈው የምትዘልፊው? በውነት ትኩስ የፈለቀ ጠበል ሳያስፈልግሽ አልቀረም። በእርግጠኝነት ትክክለኛዋ እህተማርያም እኔ ነኝ ብለሽ መምጣትሽ አይቀርም። የፊዚክስ ፕሮፌሰር ምን እንደሆን ይገባሻል የሰውዬው ትልቅነት እወቁልኝ ብሎ ይህንን እንኳን አልጻፈም። በይ እህቴ ወይ ቄሮ ወይ ግምቦት 7 ፈርሞብሽ ሂዷል መዳኛም የለሽም። የአንዳርጋቸውን ተረት ደጋግመሽ ከልሽው ላንች ተመጥኖ የተሰነደ ነው።

 7. ወያኔ ማለት አውሬ ማለት ነው። ጭካኔአቸው በሰው ላይ ብቻ ሳይሆን በቤትና በአራዊቶች ላይም ነው። ላስረዳ። ነፋስ መውጫ ወያኔ እንደገባ የቤት ለቤት ዝርፊያና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችን ከቆረጠ በህዋላ ባንክን፤ የግልና የመንግስት መ/ቤቶችን ንብረት ክጫኑና ካወደሙ በህዋላ ወደ ታማኝ ቤተሰቦች ቤት በመሄድ ያደረጉት ጥፋት በሚዲያ የታየ በመሆኑ እዚህ ላይ መድገም አያስፈልግም። ግን በታማኝ ቤተሰቦች ቤት በሚገኝ ውሻ ላይ ያደረጉት ግፍ ከሰው ዘር ውጭ የሆኑ አረመኔዎች መሆናቸውን ያሳያል። ውሻውን በሰንሰለት አስረው እየጎተቱ ታማኝ ያድንህ እያሉ ይሳሳቁ እንደነበር በስፍራው የነበረ የዓይን ምስክር ይናገራል። ለዚህ ነው ከወያኔ ጋ በምንም ሂሳብ አብሮ መኖር አይቻልም የምንለው።
  አማራ መዋጋት አያውቅም። አማራ ሰነፍ ነው ይሉ የነበሩት እነዚህ ትዕቢተኞች አሁን አማራ ሆ ብሎ ተነስቶ በየሸለቆው በሚገባቸው ቋንቋ ሲያናግራቸው ምን ይሰማቸው ይሆን? እኔ የሚገርመኝ ለወያኔ ወታደሮች ሞት የሚያዝኑ እንዝህላሎች ናቸው። የሰሜን እዝን በተኛበት በሴራ ያረደው ወያኔ በኢትዮጵያ ወታደሮች አስከሬን ላይ ቆሞ እያጨበጨበ ሲጨፍር ምን አስቦ ነው? ለምንስ በወታደሮች ላይ የሲኖ ትራክ ነዳባቸው? ለምንስ የወታደር ሴቶችንና የወታደር ሚስቶችን ጡት ቆረጠ? አኖሌን ያቆመልን ወያኔ እንዲህ ያለ የጭካኔ ተግባር ሲፈጽም አንድም የትግራይ ተወላጅ ይህ እብደት ነው እንዴት ይደረጋል በማለት ድምጽን ያሰማ የለም። ያው በተቃመሱበት የዘር ፓለቲካ ግን ሲደነፉና የውሸት ጡሩንባ ሲነፉ ያኔም አይተናል አሁንም እየሰማን ነው። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት በጉራ የተወጠረው ወያኔ ተመልሶ ሲወቃና መቀሌን ሰራዊቱ ሲቆጣጠር ወያኔ ለትግራይ ህዝብ አይመችም ስሙ ሲባሉ የፈጸሙት የሰውርና የይፋ ሸር አያቀባብርም። በየትኛው ሃገር ነው ሰው ውሃ ሲጠይቅ መርዝ ተጨምሮ የሚሰጠው? በሰራዊቱ ላይ የተሰራበት ግፍ ሰማይ ጠቀስ ነው። ግን የአብይ መንግስት ህዝብን ከህዝብ አላጋጭም ይህን ግፍና ደባ ደብቀን እንያዘው በማለት ዛሬም እውነቱ ተሸፍኖ ቀርቷል። የትግራይ ህዝብ ወያኔን ይወዳል። ባይወደው ኑሮ ያኔ ከሰራዊቱ ጎን በመሆን ዳግም እንዳይመለስ ማድረግ ይችል ነበር። አሁን እንሆ ወያኔ በተለመደው የውሸት ፕሮፓጋንዳው ከአንድ ቤት ሁለት ሰው አዋጡ እያለ ልጆቹን እሳት ውስጥ ሲማግድ ምን ይሰማቸው ይሆን? የትግራይ ቲቪን ላዳመጠ፤ የሬዲዮ ጣቢያቸውን ለሰማ በእውነት እነዚህ ሰዎች እንስሳ እንጂ ሰዎች አይደሉም ብሎ ለማመን ደቂቃ አይፈጅበትም። ጎንደርን ተቆጣጥረን ወደ አዲስ አበባ እየገሰገስን ነው በማለት ድሮ በሻቢያና በወያኔ ጥምረት የተማረኩ ወታደሮችን ፊልም በማሳየት የትላንት ውጊያ ላይ የተማረኩ እያለ ይለፋል። ወያኔ ውሸት አልቆበት አያውቅምና!
  አሁን በጦር ሜዳ የተማረኩ ሁሉ እኛ ምንም አናውቅም የሚሉት ውሸት ነው። በደንብ አምነውበት የአማራን ሃብት ለመዝረፍ፤ ቀሪውን ለማቃጠል ተደራጅተውና ታጥቀው ነው የተላኩት። የሚያሳዝነው የምርኮኛ ቃለ መጠየቅ አድራጊዎች ስርዓት ያጣ ጥያቄና ለሚዲያ ፍጆታ ተብሎ የሚደረግ የቶሎ ቶሎ ነገር ወልጋዳነት ነው። የጦር ምርኮኛ አያያዝ፤ የሚያውቀውን ሚስጢር መመርመር፤ አንድ ነጥብ ከሌላው ምርኮኛ ጋር ማገጣጠም፤ በመሬት ላይ ከሚታየው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ማዛመድ የአንድ ወታደራዊ ክህሎት አካል ነው። ያ ከምርኮኞች የተገኘ ሚስጢር ደግሞ በጦር አውድማው ላይ ላሉ የሚተላለፍ ድጋፍ ሰጪ ሃሳብ ሆኖ ይሰራበታል። በመሰረቱ የምርኮኛ አያያዝና ምርመራ ሥራ ብዙ መሰረታዊ ነገሮች እንደሚጎሉት እያየን ነው። እገሌ የሚባል ከፍተኛ የወያኔ የጦር መሪ ተያዘ ተገደለ ከማለት ይልቅ ዝምታው ሊያስገኝ የሚችለውን ወታደራዊ ግባት መመርመር መልካም በሆነ ነበር። የወያኔ ምርኮኞች ቢለቀቁ ተመልሰው ፊልሚያ ውስጥ እንደሚገቡ የአለም አጫዋቹ አብርሃም ገብረመድህን ለወያኔ የእሳት ማገዶ እንጨት ለቃሚ ሆኖ በለቀቀው ፎቶ አይተናል። መቀሌ ላይ ተይዞ የተለቀቀ አፍቃሪ ወያኔ ሃገሩንና ወገኑን የካደ ለመሆኑ እማኝ አያስፈልግም። ለዚህም ነው ምንም ይሁን ምንም የወያኔ ልክፍተኞች መዳኛ የላቸውም የምንለው። በራሳቸው አስበውና ተንፍሰው እንዲኖሩ አይፈቀድላቸውም። ሁሌ በወያኔ ጭንቅላት ታስቦላቸውና በወያኔ የተውሶ ሳንባ እየተነፈሱ ነው የሚኖሩት።
  ስለሆነም የዶ/ር አብይ መንግስት ወያኔን ሙሉ በሙሉ ካጠፋ በህዋላ በእጅ የሚገኙ የወያኔ ምርኮኞችን ሁሉ በመመዝገብ መልሶ መቀሌ በመውሰድ ተራፊና ቋሚን የትግራይ ህዝብ እንዲለይ ለማድረግ ከአሁኑ መዘጋጀት አስፈላጊ ነው።
  በታማኝ ቤተሰብ ላይ የደረሰው ግፍ ወያኔ ከበረሃ ጀምሮ እስከ አሁን በአማራ ህዝብ ላይ ካደረሰው ሰቆቃ አይበልጥም። በጋይንት፤ በወሎ፤ በደ/ታቦር በአፋር በጭልጋ፤ በወለጋ፤ በቤኒሻንጉልና በሌሎች አካባቢዎች በሰዎች ላይ የሚደርሰው ግፍ በዚሁ በወያኔ መሪነትና አይዞህ ባይነት የሚከናወኑ የግፍ ጥቃቶች ናቸው። ግን የወያኔን አውሬነት ለመረዳት የዛሬውን ተግባራቸው ብቻ ሳይሆን ለ 27 ዓመት በምድሪቱ የፈጸሙትን ግፍ መርምሮ ማወቅ ተገቢ ይሆናል። ስንቶች ናቸው እንደ ወጡ የቀሩት። ስንቶች ናቸው ከቤትና ከት/ቤት ታፍነው የት እንደገቡ የማይታወቁት? ሶዶማዊው ወያኔ የስንቶችን ሴትና ወንድ ብልት ነው ዳግመኛ መውለድ እንዳይችል ያመከነው? ስንት የወያኔ ሰላዪችና ገዳይ ክንፎች ናቸው በሆስፒታል ሰው ከተኛበት ሞተ ብለው የሰውን አስከሬን ለቤተሰብ ያስረከቡት? በሃገራችን ረጅም ታሪክ ውስጥ እንደ ወያኔ ያለ አረመኔ በምድሪቱ በቅሎ አያውቅም። የታማኝ ወላጆች ቤትና ንብረት መውደም ከዚሁ ከዘመናት በፊት ለአማራና ለኦርቶዶክስ እምነት ከነበራቸው ጥላቻ የመነጨ የማያቋርጥ ሬት ውጤት ነው። የነቃ ወያኔን በህብረት ይውቃ፡፤ እኖራለሁ ከወያኔ ጋር የሚል ደንቆሮ ደግሞ አብሮ ይሰለፍና ይየው። አኝከው ይተፉሃል። በቃኝ!

 8. የመስፍን አርጋ የህሊና እና የኣዕምሮ ህመም ጸበል መዳን ከሚቻለው በላይ ነው። በመሆኑም ዘመድ ወገን ካለው አማኑኤል ሆስፒታል ዝግ ከሆነ ክፍል ቢያደርስልን ወጭው በጎፈንድሚ መሸፈን ይቻላል እና የምትወዱትና የምታከብሩት አማኑኤል ሆስፒታል አድርሱቱ። የሚዘበዝበው የአይምሮ ችግር ያለበት ነውና

  • አምባው በቀለ ባንተ ቤት ማንጓጠጥህ ነው ይልቁንስ የሀሳብ ውስንነት ስላለብህ መስፍን አረጋ እንዲመራመርብህ እራስህን በፈቃደኝነት ብትሰጠው።

 9. የኢትዮጲያን በጎሳ መከፋፈል ያቀደውና ለአማራውም ከፍተኛ ጥላቻ በማራመድ እንዲያልቅ ዘመቻ ከጥንት የጀመረውን ወያኔን ትተን ከወያኔ ሰፈር በቃኝ ብሎ ኢትዮጲያዊነትን በአዲስ መንፈስ ያቀጣጠለውን አብይ አህመድን በዚህ ወቅት መንቀፍ የዘራፊው የጁንታውን የጥፋት ዘመቻ ድጋፍ ከመስጠት ለይቼ አላየውም:: በትክክል የአማራ ወገኖቻችን በወለጋ በአርሲ በወሎ በባሌ ያረደ ኦነግ ለአብይም ሳይመለስ ሊገድሉት ከመስቀል አደባባይ ጀምሮ ያደርጉትን ቅን ህሊና ያለው ይረዳዋል:: አማራው በሚገባ ልዩሃይሉን እንዳያጠናክር ክፍተት የፈጠረው የአማራው በጎጥ መከፋፈልና አሳምነው ባለማስተዋል በራሱ ባልደረቦች ላይ የደረገው ግድያና የመሳሰሉት ናቸው:: የአማራ ልዩ ሃይል እንዳይጠናከር የአብይ መንግስት ያደረገው ጫና ባይረሳም አማራ ያልቅ ዘንድ ያቀናበረው አብይ ነው ማለት ፈጽሞ ሃሰት ነው:: ስለዚህ ወቅቱን በማስተዋል የከፋውን የአማራ ዋና ጠላት ወያኔና ኦነግን ለመመከት ከአብይ ጋር እንቁም:: በዚህ አጋጣሚ አማራው በያለበት በሚገባ ይታጠቅ ዘንድ የተጀመረው ግስጋሴ ይቀጥል ከዚያ በኋላ የኦነግ የውስጥ አርበኞች ከሆዲድ ሲነሱ መመከት ይቻላል:: ከዚህ ውች የተሻለ አማራጭ ኢትዮጲያም አማራም የላቸውም ::ዲጎኔ ሞረቴው

 10. ማየት ማመን ነው፡፤ መኖር ደግሞ በውስጡ አልፎ ማረጋገጥ መቻል ማለት ነው፡፤ የአማራ ህዝብ መከራውን እያየውም እየኖረውም ነው፡፡ አማራው እንደነገድ በአብይ አህመድ ኦሮሙማ ሆን ተብሎ ታቅዶና ብሴራ ተሾርቦ ቀና እንዳይል ለመደረጉ ማረጋገጫውው ነጋ ጠባ የሚፈጸምበት ግዲያ ፣መፈናቀል ፣መታረድና መሰደድ ወዘተ ናቸው፡፤ ለምን ይህ ሆነ ብንል መልሱ አንድና አንድ ነው፡፡ አብይ አህመድ ጠንካራ የአማራ ብሄረሰብን አምርሮ ስለሚፈራና በዙሪያው የሰበሰባቸውም የኦሮሙማ አበጋዞች ይህንኑ ዘረናና አድሎአዊ አሰራሩን እያከረረ እንዲሄድ በስውር ጉባኤወች አበክረው ስለሚመክሩበት ነው፡፡ አማራ ራሱን ችሎ ጠንክሮ የወጣ እንደሆነ የአብይ አህመድ ድሪቶ የብልጽግና ፖለቲካ እርቃኑን ከመቅረቱ ባሻገር የማደናገሪያወቹ ትህነግ እንደዚሁም በስውር የሚመራቸው ሸኔና ሌሎች አማራ ተል ቡቃያወች ሽርጉዱ ሁሉ ያበቃለትና አብይ እርቃኑን ይቀራል ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ሁሉም ሀቅና እውነት ተፍረጥርጦ በህዝብ ይታወቃል ማለት ነው፡፤ ከዚያ በኋላ አብይ ታሪኩ በጥቁር መዝገብ ውስጥ ሲሰፍር መገኛውም ወህኒ ቤት ይሆናል ማለት ነው፡፤ ይህንን እያወቃችሁ የምትክዱ ሆዳሞችና ተከፋዮች ጊዚአያችሁን ጠብቁ እንጅ የፈለገውን ጊዜ ቢወስድም ሀቁን እውነቱ ወጥቶ ከመሆን አታግዱትም፡፡
  መስፍን አረጋ፦ አድናቂህም ተከታይህም ነኝና በርታ፡፤ በማንም ሆዳም ከንቱ የብቀላ ፖለቲከኛ ሸብረክ የማትል መሆንህን እኛ ተከታዮችህ አበክረን እናምናለን!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.