የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እንደምትደግፍና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበል ኤርትራ አስታወቀች

የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እንደሚደግፍ እና በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደሚያወግዝ የኤርትራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር አስታወቀ፡፡
የግንባሩ ዋና ፀሐፊ አል-አሚን ሙሐመድ አሊ ይህን ያስታወቁት የኤርትራ አብዮትን 60ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው፡፡
አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ በምትከተለው የተዛባ ፖሊሲ እና በምታደርገው ጣልቃ ገብነት ምክንያት የቀጣናው ሀገራት በግጭት መታመሳቸውን ቀጥለዋል ብለዋል፡፡
ሀገራቸው ኤርትራ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እንደምትደግፍ እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበለው አረጋግጠዋል፡፡
“የአፍሪካ ቀንድን ለመበታተን ይፈልጋሉ፤ በሶማሊያ ያደረጉትን እና ዛሬም በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለውን ተመልከቱ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ስላለው ነገር ምን ያገባቸዋል፤ ይህ የውስጥ ጉዳይ አይደለምን?” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

241058158 4751961261502379 2365070814647221166 n

አሜሪካ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እየገባች ያለችው አሸባሪው ህወሓትን ዳግም ወደስልጣን ለማምጣት ያላትን ፍላጎት ስለማይቀበሉ ነው በማለት ይመልሳሉ፡፡
በኢትዮጵያ የሚፈጠር አለመረጋጋት በጥቅሉ በቀጣናው ሰላም ላይ በተለይ ደግሞ በኤርትራ ሰላም ላይ ቀጥተኛ ስጋት ይደቅናል ነው ያሉት፡፡
የአሜሪካ አጀንዳ የአፍሪካ ቀንድን መበታተን ነው፤ የእኛ ምርጫ ደግሞ ከኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ጅቡቲ ጋር በትብብር በመስራት ሰላምን ማረጋገጥ ነው ብለዋል
የኤርትራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ዋና ፀሐፊ አል-አሚን ሙሐመድ አሊ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  ስብሃት ነጋን ጨምሮ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ዘጠኝ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ

1 Comment

  1. የኤርትራው መሪ የነጮችንና የአረብ ሃገሮችን ሴራ ከሚረድት ጥቂት የአለም መሪዎች አንድና ቀዳሚው ናቸው። ለዚህም ነው ለዶ/ር ደብረጽዪን ፊት ለፊት ስማ መረጃ አለኝ ለጦርነት እየተዘጋጃችሁ ነው። ይህ ደግሞ ለማንም አይጠቅምም ሲሉት የወያኔው ቁንጮ ዓሊ ብሎ የካደው። ይህ በቪዲዪ የተደገፈ መረጃ ስለሆነ የሚሻ ፈልጎ ማየት ይችላል። ሸፍጥና ሌብነት፤ ማሸበርና መግደል፤ መዝረፍና ከእኛ ወዲያ ውጊያ ላሳር የሚሉት የወያኔ ጥርቅሞች ራሳቸው በለኩሱት እሳት በመለብለብ ላይ ናቸው። ይህ የሽብር ቡድን ሃገርን ለማፍረስ ሲኦል ድረሰ እንወርዳለን በማለት የሚደነፋ የሙታን ጥርቅም ለመሆናቸው በጦር ሜዳ የሚማግዷቸው ህጻናት የሚናገሩት በቂ ነው። የሚገርመው ወያኔ ያኔ ገና በበረሃ እያለ ይጠቀምበት የነበረውን የማጭበርበር ስልት ለዛሬም መጠቀሙ እጅግ የዛገና የሻገተ ሃሳብ እንዳለው ያሳያል። ያለፈውን ከአሁን ጋር አጣቅሼ ላስረዳ።
    ጊዜው 1977 ዓ.ም ሲሆን ወያኔ የትግራይ ሰውን በካድሬዎቹ አማካኝነት እየዞረ ኑ አባይና ተከዜ ወንዝ ጥግ በቀን 4 ብር የሚያስከፍል ሥራ አለ በማለት ሰውን እያጋበሰ ሱዳን ጥግ ካሰፈረ በህዋላ ለተራድኦ ድርጅቶች ደግሞ ደርግ ህዝባችን አባሮብን በማለት የማጓጓዣ መኪና በማሰለፍ ሱዳን የሰፈራ ጣቢያዎች በመውስድ የመለመኛ ኮሮጆ እንዳደረጋቸው ታሪክ ይናገራል። በሱዳን የስደተኛ ሰፈሮች የረገፉት የትግራይ ልጆች ደም ዛሬም ይጮሃል። የሚያሳዝነው ሰው በዚያ መጠለያ እንኳን እያለ ከድንኳን ድንኳን መነጋገር አይፈቀድለትም ነበር። አሁን እንሆ ስራ አለ እያለ የትግራይን ልጆች ልክ እንደ በፊቱ ጦር ሜዳ ወስዶ ሲማግዳቸው ማየትና መስማት ከሰው ለተፈጠረ ያማል። ይህ ድርጅት ነው ለ 27 ዓመት የአማራን ህዝብ ሲያፍን፤ ሲገድል፤ የማምከኛ መርፌ ሲወጋ የኖረው። ይህ ስብዕና የሌለው የአጋዚ ጦር ነው የኦሮሞዋን እናት በልጇ አስከሬን ላይ እንድትቀመጥ ያደረገው። ኸረ ምን ያልሰሩት ግፍ አለ። የግፋቸውንና የሴረኝነታቸውን የክርፋት ደረጃ ለማወቅ “ሞቶ መነሳት” በሚል ርዕስ ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ የጻፈውን ጉግል ላይ ፈልጎ ማንበብ ብቻ በቂ ይሆናል። ወያኔዎች አውሬዎች ናቸው። መርዝ አብልተው ገድለው ሃዘን ቤት ቁጭ ብለው የሚያላቅሱ አራዊቶች። ለዚህ ነው ዛሬ ለእውነት የዘገዪ የኦሮሞ ልጆች ከወያኔ ጎን ሆነው ህዝባችን ሲወጉ ሰው ጨርቁን አውልቋል እንዴ የሚያስብለው። ወያኔ በከፋፍለህ ግዛው የፓለቲካ አሻጥሩ ስንቶችን የኦሮሞ ልጆችን ነው አፈር የመለሰባቸው? ስንቶችሽ ናቸው የአካልና የአዕምሮ ጉዳት የደረሰባቸው? እንዴት ያለ የኦሮሞ ወይም የአማራ ወይም የሌላ ብሄረሰብ ሰው ነው ከእነዚህ ሃገርን ከሚሸጡ ሰዎች ጋር ጥምረት የሚፈጥረው። በድን ብቻ!
    ወደ ኤርትራ ጉዳይ ስንመጣ አብሮ በአንድ የቀበሮ ጉድጓድ የኢትዮጵያን ወታደር እንዳልተፋለመ ሻቢያ በአስመራ ወያኔ በአዲስ አበባ አለቆች ሲሆኑ ያጋጫጨው ጉዳይ የሃብት ክፍፍል እንጂ ባድሜ አልነበረም። ያው በጊዜው ጋዜጠኛው እንዳለው የባድሜ ጉዳይ ሁለት መላጣ ሰዎች በጸጉር ማበጠሪያ (በሚዶ) እንደሚጣሉት ነው እንዳለው ነው። ስንቶች በዚህ የእብደት ጦርነት ረገፉ? የፓለቲካን ከንቱነት ልረዳ ለሚል ሰው የባድሜው ጉዳይ በቂ ትምህርት ነው። ይሁን እንጂ በዚያ ፊልሚያና እብደት አይደለም ማተኮር የፈለኩት።
    የአይናችሁ ቀለም አላማረንም በማለት ወያኔ ተወልደው ከደጉበት ሃገር እንደ በግ እየጎተተ ከሃገር ስለ አባረራቸው ኤርትራዊያን እንጂ። የኤርትራ ሪፈረንድም ተብሎ (ባርነት ወይም ነጻነት) ምርጫ ሲባል ከኤርትራ ውጭ ያሉ ኤርትራዊያን ሁሉ ምርጫ እንዲያደርጉ ወያኔ ይገፋፋ ነበር። ሁሉም ባይባልም የሚበልጠው በየአለበት በምርጫው ተሳታፊ ሆኗል። ያን የምርጫ ስም ዝርዝር ይዞ ነው ወያኔ ኤርትራዊያንን ከሃገር ያባረረው። ሸመድማዳ የፓለቲካ ስልት ይሉሃል ይሄ ነው። ጠ/ሚ መለስ ባይረዳው እንጂ የኤርትራዊያን አይን ከራሱ አይን ቀለም አይለይም ነበር። ግን ወያኔ ሰካራም ነው። ሁሌ በጥላቻ የተሞላ። ለዚህም ነው ጦርነቱን ከፍቶ የሰሜን እዝን ሲያጠቃ ኤርትራንና የአማራ ክልልን በሮኬት የደበደበው። በአሁኑ የወያኔ እይታ ኤርትራዊያንና አማራ ጥምር ጠላቶቹ አርጎ ነው የሚወስዳቸው። ሁለቱም ወያኔን አክ እንትፍ ያሉት የፓለቲካ አኞ በመሆኑ። ዞሮ ተመልሶ የኤርትራ ሰራዊት ወረረኝ፡ አጠቃኝ ገለ መሌ እያለ ለአሜሪካና በሃሳብ ለዘገዪ የአውሮፓ መሪዎች የአዞ እንባን የሚያፈሰው ወያኔ ጸሃይ እየጠለቀችበት ነው። ድርጅቱ ወደ 50 ዓመት በተጠጋ ታሪኩ ውስጥ እንዲህ ባለ አጣብቂኝ ውስጥ ጭራሽ ገብቶ አያውቅም። የማይወጣበት ማጥ ውስጥ ራሱን ከቶ የትግራይ ልጆችን በማስጨረስ ላይ ይገኛል። የመጨረሻ ግባተ መሬቱም መቀሌ ላይ በትግራይ ህዝብ ፊት እንደሚፈጸም ምንም ጥርጥር የለኝም።
    ባጭሩ የአሜሪካን ተንኮል ተረድቶ የምስራቅ አፍሪቃን ህብረት ለማጠናከርና ሃገራዊና አህጉራዊ ሰላምን ለማስፈን ኤርትራ ግንባር ቀደም መሆኗ እሰየው ያሰኛል። እናውቃለን ግብጽ ኢሳያስን በኢትዮጵያ ላይ ጫናና ሌላም ነገር እንዲያደርግ በብዙ እንደሞከረች፤ ይገባናል የሳውዲ መንግስት በስደተኞች ላይ የሚሰራው ወንጀልና ስቃይ ሆን ተብሎ የአረብ ራቢጣን ለማስደሰት ኢትዮጵያ ላይ የችግር ጫናችን ለመከመር የታለመ የሴራ ፓለቲካ እንደሆነ። ግን እኮ ሰው ሁሉ አሁን የውጭውንም ሆነ የውስጡን ሴራ ተረድቶታል። ወያኔ አብቅቶለታል። ገጣሚው ባለው አንድ ግጥም ሃሳቤን ልቋጭ።
    የሞተ የቆመን ያሸነፈ መስሎ
    ህዝብን ያታልላል እውነቱን ደብቆ
    ነግቶ ጸሃይ ወቶ እውነት ስታበራ
    መደበቂያ የለም ለወያኔ መንጋ።
    በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share