August 30, 2021
32 mins read

ታዋቂነት እኮ ሁሉን ማወቅ ማለት አይደለም! – ጠገናው ጎሹ

August 30, 2021
ጠገናው ጎሹ

ታዋቂነት (prominence/popularity)) ግለሰቦች ወይም ቡድኖች በተሠማሩባቸው የሙያ ፣የእውቀት ፣ የክህሎት ፣ የማህበራዊ አገልግሎት ፣ ወዘተ መስኮች በአንፃራዊነት (በገሃዱ ዓለም ፍፁም የሚባል ነገር የለምና) ልዩ የሆኑ አወንታዊ አስተዋፅኦዎችን በማበርከታቸው የሚ ያገኙት መጠሪያ ቅፅል ነው ።

famousእውነተኛ ታዋቂነት እራስን በሁሉም ነገር (ጉዳይ) አዋቂና ሁልጊዜም ትክክል አድርጎ ከማሰብ  እጅግ እንጭጭና የተሳሳተ አስተሳሰብ (very infantile and wrong way of thinking) ጋር ጨርሶ ግንኙነት የለውም። እንዲያውም በተቃራኒው እውነተኛ ታዋቂነት ማለት ለሚደረጉ ንግግሮች አስፈላጊውን ትኩረት ወይም ጥንቃቄ የማድረግ እና ሊከሰቱ የሚችሉ ስህተቶችን  በፀጋ ተቀብሎ ለመታረምና ለማረም ሃላፊነነትን ለመውሰድ የሚያስችል ባህሪን  የተላበሰ ሰብእና ነው።

ከዘመን ጋር አብረን እንድንዘምን የሚያስችሉንን ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊ፣ ሥነ ልቦናዊ ፣ ሥነ ምግባራዊ ፣ ሞራላዊ ፣ ወዘተ ሁኔታዎች መሠረታዊና ዘላቂ በሆነ አካሄድ ለመፍጠርና ለማዳበር ባለመቻላችን የታዋቂነት ትርጉምና እሴት በሁሉም ነገርና ሁልጊዜም ትክክል ከመሆን እጅግ የተሳሳተ አስተሳሰብ ጋር  እየተደበላለቀብን ተቸግረናል።  አብዛኛዎቹ ታዋቂዎቻችንም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የዚሁ አይነት አስተሳሰብ ሰለባዎች ናቸው በሚለውን ሂሳዊ አስተያየት እንደ ድፍረት ወይም እንደ ክብረ ነክ ወይም እንደ ነውር በመቁጠር አካኪ ዘራፍ (ያዙኝና ልቀቁኝ) ከማለት  ክፉ አባዜ ለመውጣት ከእራሳችን ጋር እና በመካከላችን እልህ አስጨራሽ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል።

የሩብ ምእተ ዓመቱ የመከራና የውርደት ፖለቲካ ሥርዓት ወደ መማሪያ ታሪክነት ተለውጦ   እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን ይሆናል ስንል በዚያው ሥርዓት ውስጥ በባሰ ሁኔታ ተመልሰን ከተዘፈቅንባቸው ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ በምሁርነቱ (intellectualism) ፣ በኪነ ጥበቡ (art) ፣ በፖለቲካ/በማህበራዊና በሰብአዊ መብቶች አንቂነቱ (activism) ፣ ወዘተ ዘርፍ ያገኘነውን ታዋቂነት የሥርዓትን ለውጥ እውን ከማድረግ ጥያቄ ጋር ሳይሆን  ከህወሃት መወገድ ጋር  ብቻ  ማያያዛችን እና ታዋቂነትን  እጅግ ከተሳሳተ ሁሉን የማወቅ አስተሳሰብ ጋር  እያደበላለቅን የስሜታዊነት ፖለቲካ ሰላባዎች የመሆናችን እውነታ ነው።

ባሳለፍነው የአውሮጳዊያን ወር መጨረሻ (July 31, 2021) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የወቅቱ ተመራቂ ተማሪዎቹን ማስመረቁ ይታወሳል። ዩኒቨርሲቲው ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ከታዋቂ የሙዚቃ (የኪነ ጥበብ ዘርፍ) ባለሞያዎች አንዱ ለሆነው ለቴዎድሮስ ካሳሁን የክብር ዶክትሬት መስጠቱም ይታወሳል።

እንደ እኔ ግንዛቤ ወይም አረዳድ የእለቱ ዝግጅት በጥቅሉ ሲታይ ፦

ሀ) ተመራቂዎቹ የከፍተኛ ትምህርታቸውን አጠናቀው ለመመረቅ መብቃታቸውን በደስታ የማብሠር ፣ በተግባር ወደ የሚፈተኑበት የህይወት ምእራፍ እየተሸጋገሩ መሆናቸውን  የማስገንዘብ እና ይህንኑ በአግባቡ ተረድተው በተለይ አገራቸው ከምትገኝበት የወቅቱ  ግዙፍና መሪር እውነታ አንፃር  አስፊላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የማስገንዝብ ፤

ለ) ለቅድመ ምረቃ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች፣ በየትምህርት ደረጃው ለሚገኙ ሌሎች  ተማሪዎች ፣ አሁን እድሉ ባይገጥማቸውም ወደ ፊት ለመማር ዓላማና ፍላጎት ላላቸው ወገኖች እና እንዲሁም ልጆቻቸውን እያስተማሩ ላሉና ለማስተማር ለሚፈልጉ ወላጆች  “እኛም እንችላለን” የሚል  የበጎ ተስፋ ስሜት የማሳደር ፤ እና

ሐ) የኪነ ጥበብ ሙያ አንዱ ዘርፍ  በሆነው የሙዚቃ ባለሙያነቱ የአገርን ታሪክ ፣ ባህል፣ ወግ ፣ ፍቅርና አንድነት አጉልቶ በማሳየት ረገድ  የህዝብን አድናቆት  (popuparity) ካተረፉት መካከል አንዱ ለሆነው ለቴዎድሮስ ካሳሁን የክብር ዶክትሬት (honorary degree) በመስጠት በዚሁ ዘርፍ ለተሰማሩ ወይም ለመሰማራት ጥረት እያደረጉ ላሉ ወገኖች በጎ ተፅዕኖ የማሳደር  ቁም ነገሮችን  የያዘ ነበር ማለት ይቻላል።

ይሁን እንጅ ዝግጅቱ መከረኛው ህዝብ ለዘመናት የመጣበትንና አሁንም በሸፍጠኛ፣ ሴረኛና ጨካኝ የኢህአዴግ ውላጅ ገዥ ቡድኖች ሥር መከራና ውርደቱን እየቆጠረ ያለበትን ግዙፍና መሪር ሃቅ በሚመጥን ሁኔታ አንፀባርቋል ማለት አይቻልም።  ይህ ማለት ግን ዝግጅቱ የፖለቲካ መድረክ መሆን ነበረበት ማለት አይደለም። የትምህርት ትክክለኛው ትርጉምና እሴት ማህበረሰብ የሚያጋጥመውን ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሠራሽ አደጋ (catastrophe) ሲሆን ቀድሞ መከላከል ካልሆነም ቀድሞ በመድረስ መታደግ ከመሆኑ አንፃር እና ኢትዮጵያም እጅግ ፈታኝ በሆነ አጠቃላይ ቀውስ ውስጥ የምትገኝ ከመሆኗ  አንፃር  ከዝግጅቱ ብዙ ሲጠበቅ የተጠበቀውን ያህል አለመሆኑ ን መግለፅ ዝግጅቱን ማኮሰስ ተደርጎ ሊታይ አይገባም።

የዝግጅቱ አጠቃላይ ድክመት አልበቃ ያለ ይመስል ጭራሽ በመሬት ላይ ያለውን የጎሳ/የጎጥ/የቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማር መሪር እውነታ “… በስብሶ ተቀብሯል” በሚል ቅዠታዊ (dellusional) ዲስኩር  ሲገለፅ መስማት ሚዛናዊ ህሊናን ይኮሰኩሳል ።

የአስተያየቴ ትኩረት ቴዎድሮስ ካሳሁን ባደረጋት አጭር ዲስኩር (ንግግር) ውስጥ ስለታዘብኳት የንግግሩ ክፍል በመሆኑ እንጅ ከዚያ ባሻገር ሂሳዊ ትችት በሚያስፈልጋቸው ወይም ጥያቄ በሚያጭሩ ጉዳዮች ላይ ብዙ ማለት ይቻላል።

ለምሳሌ ፦

  • እጅግ ሃላፊነት በጎደለው የሥርዓቱ ካድሬዎችና አድርባይ ምሁራን ምክንያት ላለፉት ሦስት ዓሥርተ ዓመታት በእጅጉ ከተጎሳቆለው እና አሁንም በባሰ አኳኋን ከቀጠለው የትምህርት ፍልስፍና እና ፖሊሲ አንፃር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እያተሙ የሚያድሏቸው የላቀ ትምህርት ደረጃ እና የላቀ የሙያ አስተዋፅኦ የምሥክር ወረቀቶች ትውልድን በመቅረፅ ረገድ ምን ያህል ተሳክቶላቸዋል? የመደበኛ ትምህርትና የክብር ዶክተርነት መመዘኛዎቻቸውስ የገሃዱን ዓለም ችግር ለመፍታት ካላቸው ብቃትና ዝግጁነት አንፃር ምን ያህል የተፈተሹ፣ አስተማማኝና የተዋጣለቸው ናቸው? ወዘተ ብሎ መጠየቅ ነውር ወይም ክብረ ነክ ወይም ስም አጥፊነት ከቶ ሊሆን አይችልም።
  • ቴዎድሮስ ካሳሁንን በተመለከተም በሙዚቃ ባለሙያነቱ ለአገር ያበርረከተው እጅግ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደ ተጠበቀ ሆኖ የኢህአዴግ አንጃ የሆኑት የጎሳ ፖለቲካ ቁማርተኞች “ዴሞክራሲያዊ ተሃድሶ” በሚል በመከረኛው ህዝብ ላይ በሚሳለቁበት በዚህ እጅግ አስቸጋሪ ወቅት  ምን ተናገረ ወይም ምን አይነት የዴሞክራሲያዊ አርበኝነት መልእክት አስተላለፈ?  ለመሆኑ ቤተ መንግሥቱን በተረኝነት የተቆጣጠሩትን ኢህአዴጋዊያንን (ብልፅግናዊያንን) ጨምሮ በሸፍጠኛና ሴረኛ የጎሳ ፖለቲካ ቁማርተኞች ምክንያት አገር ከሦስት ዓመታት በላይ ለንፁሃን ዜጎቿ ምድረ ሲኦል ስትሆን በሙያውም ይሁን በሌላ የመልእክት ማስተላለፊያ ዘዴ (መንገድ) ምን መልእክት አስተላለፈ? በሙያው ያሽሞነሞነው ህዝብ እና ያሽሞነሞናት አገር በዓላማ ሳይሆን በቤተ መንግሥት ዙፋን እና በአገር አንጡራ ሃብት ዝርፊያ ዙሪያ በሚተናነቁ ኢህአዴጋዊያን አንጃዎች ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ አኳኋን ምስቅልቅሏ ሲወጣ በየትኛው አደባባይ ወይም የመገናኛ መድረክ  ወጥቶ  ምን ተናገረ? ምንስ አደረገ? ብሎ መጠየቅ ከቶ ነውር ወይም ክብረ ነክ ወይም ስም አጥፊነት ወይም ጭፍን ጥላቻ ፣ወዘተ ሊሆን አይችልም። “የገንዘብ እርዳታ ስላደረገ ወይም እያደረገ ስለሆነ ከቃል ይልቅ ድርጊቱ ይመሰክርለታል” የሚል መከራከሪያ የሚያቀርቡና “እንደ ቴዎድሮስ ካሳሁን አይነት ታዋቂዎቻችን ለቀቅ” የሚሉ ወገኖች ሊኖሩ እንደሚችሉ በሚገባ እረዳለሁ። ስሜታቸውንም እረዳለሁና አይገርመኝም ።

ለዚህ ያለኝ አጭርና ግልፅ ምላሽ የሚከተለው ነው። በምንም መክንያትና የትም ይሁን ለተጎዱ ወገኖች ሁሉ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ የማድረግ አስፈላጊነት አያጠያይቅም። ይህ ግን የመከራውና የውርደቱ ዋነኛ ምክንያት የሆነውን ብልሹና ጨካኝ የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ከማስወገድ እና እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን ከማድረግ ጋር በጥብቅ  ካልተያያዘ (ካልተቆራኘ) በእራሱ  ብቻ ከአስከፊው ሃዘንና መከራ ከቶ አያስጥለንም ወይም አይገላግለንም። አዎ!  የሰበብ ድሪቶ በመደረት የመከራና የሃዘን ምንጭ ከሆነው አስከፊ ኢህአዴጋዊ (ብልፅግናዊ)  ሥርዓት ጋር እየተሻሸን (እየተላላስን) እና ቆመን እያስገደልንና  እያጋዳደልን  የምንሰጠውን የሃዘን ወይም የማስተዛዘኛ ሳንቲም እንደ ትልቅ ገድል ወይም መስዋእትነት ወይም እንደ ስም መጠሪያ የምንቆጥር ከሆነ አደገኛ አስተሳሰብ ነውና ቆም ብለን ከምር ማሰብን ይጠይቀናል ።

 

ታዋቂዎቻችን የታዋቂነታቸውን ልኬታ በሚመጥን ሁኔታ ለአድናቂው ህዝብ (ለአገራቸው) የሚጠበቅባቸውን የዜግነት ሃላፊነት እንዲወጡ የሚያስችል ሂሳዊ ድጋፍ (critical support or offering support but with critique ) ስለ አላስለመድናቸው ሊነግሩን የሚፈልጉት  መከረኛው ህዝብ ቀን በቀን እየኖረበት ያለውን ግዙፍና መሪር ሃቅ ሳይሆን በምናባቸው የሚፈጥሩትን ግልብ ስሜትን ኮርኳሪ ፣ የተሳሳተና አሳሳች ዲስኩሮቻቸውን ነው። ለዚህም የሚቸራቸውን (የሚያገኙትን)  ጭብጨባና ጩኸት እንደ የታዋቂነታቸው ማረጋገጫ አድርገው ቢቆጥሩት ያሳስብ እንደሆነ  እንጅ ከቶ የሚገርም አይሆንም።

እንዲህ አይነቱ እጅግ ግልብና የተሳሳተ ዲስኩር ስሜታዊ የፖለቲካ ትኩሳት የሚንጠው ጭብጨባና ጩኸት ሲበረከትለት (ሲቸረው) መታዘብ ለዘመናት ከመጣንበትና አሁንም በባሰ ሁኔታ እንዲቀጥል ከተደረገው የመከራና የውርደት ሥርዓተ ፖለቲካ ለመውጣት የሚጠብቀን ፈታና እጅግ ከባድ መሆኑን ነው የሚነግረን።

“በዚያ የቴዎድሮስ ካሳሁን ለስሜት የሚስማማ (የሚጥም) ንግግር  አለማጨብጨብና አለመጮህ አስቸጋሪ ነበር” የሚል መከራከሪያ አስተያየት ሊነሳ እንደሚችልና መነሳቱም ተገቢ እንደሚሆን እረዳለሁ። እንዲህ አይነት በስሜት ፈረስ የሚያስጋልቡ ሁኔታዎችን ጨርሶ ማስወገድ ስለማይቻል ትናንትም ነበሩ፣ ዛሬም አሉ፣ ነገም ይኖራሉ ። የእኔ ትችታዊ አስተያየት እንዲህ አይነት አጠቃላይ እውነታዎች ለምን ኖሩ ወይም ይኖራሉ? የሚል አይደለም። የእኛ የፖለቲካ እውነታ ከዚህ አይነት አጠቃላይና ጨርሶ ማስወገድ ከማይቻለው እውነታ አንፃር ሲፈተሽ በእጅጉ ልኩን ያለፈና ከተሞክሮ ተምሮ ተገቢውን እርምት ከማድረግ ይልቅ እያደር እየተበላሸ የሚሄድ ክፉ ልማድ ነውና ሊያሳስበንና የሚበጀውን እርምት እንድናደርግ ግድ ሊለን ይገባል የሚል ነው። አዎ! ከሦስት አሥርተ ዓመታት እጅግ መሪር ተሞክሮ በኋላም እራስን እዚያው ክፉ አባዜ ውስጥ ማግኘት በእጅጉ ሊያሳስበንና ዛሬውኑ የሚበጀውን እርምት እንድናደርግ ሊያስገድደን ይገባል።

ይህ አይነት የዲስኩሩን (የንግግሩን) ፍሬ ሃሳብ ሳይሆን ደስኳሪው (ተናጋሪው) በተወሰነ የሙያ መስክ ያገኘውን ታዋቂነት (popularoity) ሁሉንም እንደማወቅ አድርጎ በመውሰድ ልጓም በሌለው የስሜት ፈረስ የመጋለብ ክፉ ልማድ አንድ ቦታና ጊዜ ላይ መታረም ይኖርበታል።    አዎ! በዚህ አይነት የተደጋገመ ክፉ ልማድ ላይ ወቅታዊና ውጤታማ እርምት እስካላደረግን ድረስ ፖለቲካ ወለድ ወንጀል ለሚያስከትልብን አስከፊ ሃዘን የሃዘን መድረሻ (ማስተዛዘኛ) ሳንቲምና ቁሳቁስ እየለመንና እያስለመን እና እንደ አኩሪ ታሪክ እየተረክንና እያስተረክን እንቀጥላለን።  አዎ! የሥርዓት ለውጥ ጨርሶ በሌለበት ፖለቲካዊ እውነታ ውስጥ ከዚያኛው ወይም ከዚህኛው ግለሰብ ፖለቲከኛ ወይም ከእነዚህ ወይም ከእነዚያ የፖለቲካ ቡድኖች ርካሽ የፖለቲካ ጨዋታ ጋር ዥዋዥዌ እየተጫወትን አንዴ የመሪር ሃዘን ሙሾ ማውረድና ምፅዋእት መለመን እና ሌላ ጊዜ ደግሞ ሃዘኑና መከራው ታዋቂ በምንላቸው ወገኖች  ዲስኩር  እንደ ጉም ተኖ የጠፋ ወይም የሚጠፋ እስኪመስል ድረስ በጭብጨባና በጩኸት ጮቤ የመርገጥን (ልክ በሌለው የስሜት ትኩሳት የመጋለብን) ክፋ ልማድ ቆም ብለንና ልብ ገዝተን ልናጤነውና ወደ ትክክለኛው አስተሳሰብና አካሄድ ልንመልሰው ይገባል።ያለዚያ ለመጭው ትውልድ የምናስተላልፈው ይህንኑ አስከፊ የፖለቲካና የሞራል ጉስቁልና ይሆናል።

የገንዛ እራሳችንን ቅጥ ያጣ ውድቀት ከመጋፈጥና ተገቢውን ከማድረግ ይልቅ የሰበብ ድሪቶ እየደረትን ከእውነታው መሸሽ ክፉ ልማድ ሆኖብን ነው እንጅ ከሦስት ዓሥርተ ዓመታት በኋላም ተዘፍቀን የቀጠልንበት ግዙፉና መሪሩ እውነት ይኸው ነው። የትኛውንም ዲስኩር ምን ማለት ነው ? ለምን? እንዴት? ከየትስ ወደ የት? ብለን ሳንጠይቅ በግልብ ስሜት በታጀበ ጭብጨባና ጩኸት አሜን እያልን የመቀበላችን ክፉ ልማድ ምን ያህል እንደጎዳን ለማወቅና ለመማር  ከሦስት ዓመታት በላይ በመሬት ላይ ያለውን ግዙፍና መሪር እውነታ ወደ እራሱ  የቅዠት ዓለም ( his own illusional and delusional realm)  እየተረጎመና እያቀነባባረ “እውነት እውነት እላችኋለሁ እመኑኝ” በሚል ዲስኩሩ የሚታወቀውን ጠቅላይ ሚኒስትር ከምር ልብ ማለት ብቻ በቂ ነው።

በአንድ ወቅት   ተፎካካሪ ተብየ ፖለቲከኞችን ሰብስቦ “ለውጥ የሌለ የሚመስላችሁ በልጅነታችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ መኪና ላይ ተሳፍራችሁ መኬናው ወደ ፊት ሲሽከረከር መሬቱና ዛፉ ወደ ኋላ የሚሄድ  እንደሚመስላችሁ ሆኖባችሁ ነው” በሚል ሲሳለቅባቸው ማጨብጨባቸውን ከምር ለታዘበ ሰው ከዚህ በታች የምጠቅሰው የቴዎድሮስ ካሳሁን ምናባዊ ንግግር (ዲስኩር) በስሜት ትኩሳት የታጀበ ጭብጨባና ጩኸት ቢቸረው የሚገርም አይደለም።

ቴዎድሮስ ካሳሁን ለዘመኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎች ምሥጋና ይግባውና በቦታው ለተገኙ ታዳሚዎች ብቻ ሳይሆን በእየ እጅ ስልኩ ላይ ይከታተለው ለነበረ ሁሉ ለተሰጠው አክብሮት ምላሽ በሰጠበት እጅግ አጭር ዲስኩሩ ውስጥ ዋነኛ ከሆኑ መልእክቶቹ  አንዱን “ላለፉት ቀላል ላልሆኑ ዓመታት አገራችን አስጨንቆ የያዛትና አሁንም ላለችበት ቀውስ የዳረጋት የጎሳ ፖለቲካና ሃሳብ እንደማነኛውም ሃሳብና ፍልስፍና ተወልዶ፣ አድጎ፣ አርጅቶና በስብሶ ተፈጥሯዊ ሞቱን ሞቷል” ሲል ይገልፀዋል።

ልክ ኢትዮጵያ ለዘመናት ከመጣችበት እና አሁንም የቀድሞ ጌቶቻቸውን ከቤተ መንግሥት አስወጥተው ጥርሳቸውን ነቅለው ያደጉበትን እኩይ የጎሳና የቋንቋ ማንነት ፖለቲካ ሥርዓት አስከፊ በሆነ የተረኝነት አገዛዝ ካስቀጠሉት ሸፍጠኛና ሴረኛ ግዥ ቡድኖች በአንዳች አይነት ተአምር (ምትሃት) የተላቀቀች እስኪመስል ድረስ ጭብጨባውና ጩኸቱ አስተጋባ።  አዎ!  የሚቀርብለትን ዲስኩር (ንግግር) ፍሬ ሃሳብና ተጠባቂ  ውጤት ሳይሆን የተናጋሪውን ማንነት ብቻ እያሰበ በየዓረፍተ ነገሩ ወይም በየአንቀፁ መጨረሻ ጭብጭባና ጩኸት በማስተጋባቱ እርካታ የሚሰማው ትውልድ የእራሱን እጣ ፈንታ በእራሱ የመተማመን መርህና ተግባር ላይ ተመሥርቶ  ለመወሰን በእጅጉ ይቸገራል።

መቸም የእራችንን ልክ የሌለው ድክመት ወይም ውድቀት ተጋፍጠን ተገቢውን እርምት የማድረጉ ወኔ ሲያጥረን የሰበብ ድሪቶ እየደረትን እራሳችንን መሸንገል (ማታለል) ክፉ ልማድ ካልሆነብን በስተቀር ለዓመታት በመማርና ማስተማር ሂደት ውስጥ አልፎ የመመረቂያ ገዋንና ቆብ ያጠለቀ ወጣት ትውልድ በመሬት ላይ ካለው ግዙፍና መሪር ሃቅ ጋር ጨርሶ የማይገናኝ ዲስኩር ሲደሰኮርለት በወቅቱ በስሜታዊነት ወይም በሌላ ምክንያት ለማጨብጨብና ለመጮህ ቢገደድም እንኳ ቆይቶም (አድሮና ውሎም) ቢሆን “የሰማሁትና ያጨበጨብኩለት የንግግር ይዘት እውን ግዙፉንና መሪሩን ሃቅ ይገልፃልን?” ብሎ እራሱን ለመጠየቅ የሚያስችል ወኔ አላገኘም።

ለዚህም ነው በመንበረ ሥልጣን ላይ የሚፈራረቁ ፈሪ፣ ባለጌና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች ሁሉ የኦሮሚያው ገዥ ሽመልስ አብዲሳ እንደነገረን ሲችሉ በርካሽ ፕሮፓጋንዳቸውና በፍርፋሪያቸው በማሳመን (convince) በማድረግ እና  ካልሆነ ደግሞ ግራ እያጋቡ (confuse) እያደረጉ ይህን ትውልድ ባለቤት እንደ ሌለው እንስሳ ወደፈለጉት አቅጣጫና ግብ የሚነዱት ።

አንዳንድ ወገኖች እንደ ቴዎድሮስ አይነት በሙያው የህዝብ እውቅና (popularity) ያገኘን ሰው ተሳስቷል ማለትን እንደ ክብረ ነክ ወይም እንደ ነውር በመቁጥር በሚመስል አኳኋን  ወይም እነርሱ እራሰቸው በሚያውቁት ሌላ ምክንያት  ግልፅና ግልፅ የሆነውን “የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብና ፍልስፍና ተወልዶ፣አድጎ፣ አርጅቶና በስብሶ የመሞት” ምናባዊ ዲስኩር  ለማስተካከል እጅግ ሲቸገሩ መታዘብ ባይገርምም ምነው የፖለቲካ አስተሳሰባችን መርህ አልባ ሆነ? የሚል ጥያቄን ግን ያስነሳል።   የእውነተኛ መርህ ሰው የግለሰቦችን ዲስኩር የሚመዝነው ታዋቂ የሆኑ ወይም ያልሆኑ በሚል ሳይሆን የዲስኩራቸው (የንግግራቸው) ይዘት በመሬት ላይ ያለውን ግዙፍና መሪር እውነታ ያንፀባርቃልን? ወደ ተሻለ የተግባር እርምጃ ለመራመድ ያግዛልን?  የሚሉ ቁልፍ ጥያቄዎችን መመለስ ከመቻል ወይም ካለመቻል አንፃር ነው።

አዎ! ትክክል ያልሆነን ነገር ትክክል አይደለምና ይታረም ብሎ በአክብሮትና በገንቢነት ለመናገር (ለመግለፅ) የትምህርት ደረጃን፣ የማህበራዊ ግንኙነት ተቀባይነትን ፣የሙያ ታዋቂነትን ፣ የፖለቲካ ሥልጣን ደረጃን ፣ የእድሜ ባለፀጋነትን፣ የሃይማኖት መሪነትንና ሰባኪነትን ፣ በግል መተዋወቅን ፣ወዘተ መመዘኛ ማድረግ ፈፅሞ አይጠቅም። የሚጠይቅ መሆንም የለበትም። ከዚህ አይነት ኋላ የቀረና ደካማ የፖለቲካ አስተሳሰብ እራሳችንን በአንፃራዊነት ነፃ ሳናወጣ የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኛ ገዥ ቡድኖችን አስወግደን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን ማለት ባዶ ምኞት ነው የሚሆነው። ለታዋቂነት የምንሰጠው ትርጉምና ዋጋም መመዘን ያለበት ከዚሁ መሠረታዊ ሃሳብ አንፃር መሆን ይኖርበታል።

በመሬት ላይ ካለው ግዙፍና መሪር እውነታ በተቃራኒ የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብና ፍልስፍና “ተፈጥሯዊ ሞቱን ሞቷል” የሚልን እጅግ የተሳሳተና አሳሳች ዲስኩር ቢያንስ “ምነው እየተስተዋለ እንጅ” ለማለት ወኔው የሚሳነን ከሆነ እውነትም እየኖርን ያለነው በክፉ ቅዠት (illusion) ውስጥ እንጅ በእኛው በእራሳችን ገሃድ ዓለም  እውነታ ውስጥ  አይደለም ማለት ነው።

አገር በአንድ በኩል የአፈና እና የማጭበርበር ስልትን እያጣመሩ መንበረ ሥልጣኑን በተረኝነት በተቆጣጠሩ የጎሳ/የቋንቋ  አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኛ ገዥ ቡድኖች እና በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉን አድራጊነታችን ተደፈረብን በሚሉ የአንድ ሥርዓት ( የኢህአዴግ ሥርዓት) ሁለት አንጃዎች ወይም ጁንታዎች  መካከል በሚደረግ እጅግ አሳፋሪና አሰቃቂ የሥልጣን ሽሚያ ጦርነት ምስቅልቅሏ እየወጣ  ባለበት መሪር እውነታ ውስጥ የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብና ፍልስፍና እንደ በሰበሰና እንደሞተ አድርጎ መደስኮር ለተሰጠን ወይም ለሚሰጠን የታዋቂነት እውቅና ጨርሶ አይመጥንምና ከምር ልብ ልንለው ይገባል።

ታዋቂነት ማለት ሁሉን ማወቅ እና ከሂሳዊ ትችት ነፃ መሆን ማለት አለመሆኑን ባንወደውም በመቀበል ለእርምት ዝግጁዎች መሆን ይኖርብናል። ከዚህ በተቃራኒ ያለው አስተሳሰብና ባህሪ የውድቀት እንጅ የስኬት ምክንያት  አለመሆኑን ለአያሌ ዓመታት አይተነዋልና ጨርሶ ልናስወግደው ባንችል ከምር ልናርመው ይገባናል።

ይህን ለማድረግ ዝግጁዎች እንደምንሆንና  እንደምንችልም ያለኝን ተስፋ እየገለፅሁ አበቃሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop