September 1, 2021
20 mins read

የኢትዮጵያ ኪስ በጦርነትና በኮቪድ ተመታ!!! የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ 502 ሚሊዮን ዶላር ደረሰ!!! – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

(ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

eeeeeየምዕራባዊያን የሚዲያ አውታሮች በ2021እኤአ የኢትዮጵያን የትግራይ ጦርነት የውሽት ዜና “Fake News” በዜና መዋላቸው ለአስር ወራቶች ሲዘግቡ ከርመዋል፡፡ በዘመናችን የዲጂታል ሚዲያ ዘመን በኢትዮጵያ ላይ የተሠራ የውሸት ዜና  የዓለማችን የውሽት ሪከርድ በጊኒስ ሪከርድ የተመዘገበበት የዲጂታል ቴክኖሎጅ ዘመን ለመሆን በቅቷል፡፡  በዚህ የጠርነት ኢኮኖሚ የቴሌኮሙኒኬሽን የማሠራጫ ቌቶች፣ የመብራት ኃይል የኤሌትሪክ ማሠራጫ ቌቶች፣ ግድቦች፣ ድልድዬች፣መንገዶች፣ የኤሌትሪክ ባቡር መሥመሮች፣ የውኃ ማከፋፈያ ጋኖች፣ የኢንዱስትሪ ዞኖች፣ ፋብሪካዎች ወዘተ መጠበቅ የሁሉም ተጠቃሚ ዜጎች የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ካለዛ የመብራት አገልግሎት የለም በጨለማ ውስጥ እኖራለን፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት የለም፣ ንጹህ ውኃ የለም፣ ድልድይ ከሌለ መንገዶች የሉም፣ መኪኖች ይቃጠላሉ፣ ቤቶች ይጋያሉ፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ይቃጠላሉ፣ ወዘተ ብዙዎቹ እቃዎች ከባህር ማዶ የውጭ ምንዛሪ በዶላር፣ በፓውንድ፣ በዩሮ ወዘተ ተገዝተው የመጡ በመሆኑ በቀላሉ መተካት አይቻልም፣ ልንጠብቃቸው ግድ ይላል፡፡ የትህነግ አሸባሪ ቡድን በጦርነቱ በመሸነፉ ወደ ‹‹አጥፍቶ መጥፋት›› ስልት  ተሸጋግሮል ስለዚህ ኢትዮጵያዊን የሃገሪቱን ዋና የኢኮኖሚ መሠረተ-ልማቶች ቀን ከሌት ዘብ የመቆምና የመጠበቅ ኃላፊነት አለብን፡፡ በኢትዮጵያ ከተሞች ሁሉ አዲስአበባ፣ ናዝሬት፣ አዋሳ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረብርሃን፣ ሃረር፣ ድሬዳዋ፣ ጅማ፣ ጋምቤላ፣ ጅጅጋ፣ ሰመራ ወዘተ ከተሞች በወጣቶች ቀን ከሌት መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡  ይህን ለማድረግ ከጦርነት ኢኮኖሚ በአስቸኳይ ተላቆ፣ ኢኮኖሚያችንን በአፋጣኝ ማሳደግ ይኖርብናል፡፡

  • አጠቃላይ የአገርውስጥና የውጭ ዕዳ:-የኢትዮጵያ መንግሥት ከአገር ውስጥና ከውጭ ላለፉት ዓመታት የተበደረው ውዝፍ የዕዳ መጠን 2.4 (ሁለት ነጥብ አራት) ትሪሊን ብር ደረሰ፡፡ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ እስከ ጁን 30 ቀን 2020 እኤአ ድረስ 2.4 ትሪሊዮን ብር ሆኖ መመዝገቡን ይፋ ያደረገው፣ የገንዘብ ሚኒስትር ሰሞኑን ያወጣው የዕዳ መግለጫ ሰነድ  ነው፡፡ ብሄራዊ ባንክ ላለፈው አንድ አመት ባደረገው የብር ምንዛሪ ተመን ለውጥ ምክንያት የብር የመግዛት አቅም በከፍተኛ ደረጃ በመውረዱ፣ አጠቃላይ የአገሪቱ ውዝፍ ዕዳ በ221.5 (ሁለት መቶ ሃያ አንድ ነጥብ አምስት) ቢሊኝ ብር እንዲያሻቅብ ምክንያት እንደሆነም ሰነዱ ያመላክታል፡፡ አጠቃላይ የአገሪቱ የዕዳ መጠን በውጭ ምንዛሪ ሲሰላ 55.6 (ኃምሳ አምስት ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰም ሰነዱ ያመላክታል፡፡
  • የአገር ውስጥ ዕዳ፡- ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ውዝፍ ዕዳ መጠን በ2013ዓ/ም 1.14 (አንድ ነጥብ አስራአራት) ትሪሊዮን ብር    ሲሆን በ2012ዓ/ም 918.9 (ዘጠኝ መቶ አስራ ስምንት ነጥብ ዘጠኝ) ቢሊዮን ብር ነበር፡፡
  • የውጭ አገር ዕዳ፡- ከአጠቃላይ የውጭ አገር ውዝፍ ዕዳ መጠን በ2013ዓ/ም 1.29 (አንድ ነጥብ ሃያ ዘጠኝ) ትሪሊዮን ብር  ሲሆን በ2012ዓ/ም 1.01 (አንድ ነጥብ ዜሮ አንድ) ትሪሊዮን ብር እንደነበር ሰነዱ ይገልፃል፡፡
  • የኢትዮጵያ መንግሥት ከአጠቃላይ የውጭ ውዝፍ ዕዳውን ለማቅለል በ2013ዓ/ም በጀት ዓመት መዝጊያ ድረስ 73.1 (ሰባ ሦስት ነጥብ አንድ)ቢሊዮን ብር ወይም 1.8 (አንድ ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ዶላር ለውጭ አበዳሪዎች ከፍሎል፡፡ በ2012ዓ/ም ተመሳሳይ ወቅት ከከፈለው 64.03 (ስልሳ አራት ነጥብ ዜሮ ሦስት) ቢሊዮኝ ብር ከፍ ያለ ቢሆንም፣ በወቅቱ በነበረው የምንዛሪ ተመን መሠረት ግን ሁለት ቢሊን ዶላር በመሆኑ  የከፈለው የእዳ መጠን ብልጫ ነበረው፡፡
  • በ2013ዓ/ም የኢትዮጵያ መንግሥት 1.4 (አንድ ነጥብ አራት)ቢሊዮን ዶላር ከዓለም ባንክ ተበድሮል፡፡ በዚሁ አመት የዕዳ ክፍያ 1.8 (አንድ ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ዶላር ሆኖ በማደጉ ምክንያት የተጣጣው የብድር ገቢ፣ በዓመቱ መጨረሻ ዜሮ ወይም በዓመቱ ከተገኘው የውጭ ብድር ፍሰት በ432 (አራት መቶ ሠላሳ ሁለት)  ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ያለው ገንዘብ ለዕዳ ክፍያ ውሎል፡፡
  • በ2016/17 እኤአ የነበረው የአገሪቱ አጠቃላይ የውጭ ብድር ዕዳ መጠን 23.3 (ሃያ ሦስት ነጥብ ሦስት) ወይም 539.5 (አምስት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ነጥብ አምስት)ቢሊዮን ብር በወቅቱ የብር ምንዛሪ ተመን እንደነበር መረጃው ያመለክታል፡፡
  • በ2020/21 እኤአ የአገሪቱ አጠቃላይ የውጭ ብድር ዕዳ መጠን 29.5 (ሃያ ዘጠኝ ነጥብ አምስት) ከፍ ብሎል፡፡ ይሁን እንጂ በሰኔ ወር 2013 ዓ/ም በነበረው የብር ምንዛሪ ተመን ሲሰላ ግን 1.29 (አንድ ነጥብ ሃያ ዘጠኝ) ትሪሊዮን ብር በወቅቱ የብር ምንዛሪ ተመን እንደጨመረ  መረጃው ያመለክታል፡፡
  • በ2016/17 እኤአ የነበረው የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥ የዕዳ መጠን 522.8 (አምስት መቶ ሃያ ሁለት ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፣በ2020/21እኤአ (በሰኔ ወር በ2013ዓ/ም) ላይ የዕዳ መጠኑ ከእጥፍ በላይ በመጨመር 1.14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት) ትሪሊዮን ብር ደርሶል፡፡
  • አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ዕዳ:-በ2016/17 እኤአ የነበረው የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ዕዳ መጠን 1.06 (አንድ ነጥብ ዜሮ ስድስት) ትሪሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፣በ2020/21እኤአ (በ2013 ዓ/ም) ላይ የዕዳ መጠኑ 2.4 (ሁለት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር አሻቅቦል፡፡
  • ከአጠቃላይ የዕዳ መጠን ውስጥ 1.29 (አንድ ነጥብ ሃያ ዘጠኝ) ትሪሊዮን ብር የሚሆነው የእዳ መጠን በዶላር ተመንዝሮ ለውጭ አበዳሪዎች የሚመለስ በመሆኑ ፣ የአገሪቱ የውጭምንዛሪ ግኝትን ማሻሻል ከተቻለ አሳሳቢ እንደማይሆን ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡››………{1}

በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ጦርነት

  • ‹‹በትግራይ፣ በአማራና አፋር ክልሎች በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ከሰባት ሽህ በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉና  አንዳንዶች ደግሞ በከፊል መውደማቸውን የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ አስታውቀዋል፡፡ በጦርነቱ ሳቢያ በትግራይክልል ከ 1.4 (አንድ አጥብ አራት) ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችንና ከ48000 (አርባ ስምንት) ሽህ በላይ መምህራን ከትምህርት ሥርዓት ውጪ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ ጨምረውም በአንድ ወር ብቻ በአፋር ክልል 88000 (ሰማንያ ስምንት ሽህ) ተማሪዎች ይማሩባቸው የነበሩ 455 ትምህርት ቤቶች  በአማፂው የህወሓት ኃይሎች መውደማቸውን እንደተናገሩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡ በተመሳሳይ በአማራ ክልል ውስጥ 140 ትምህርት ቤቶችና ሁለት የመምህራን ማሰልጠኛና ኮሌጆች ሙሉ በሙሉና በከፊል ለውድመት መዳረጋቸውን ገልፀዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ በሦስቱም ክልሎች የሚገኙ ከ1.42 (አንድ ነጥብ አርባ ሁለት) ሚሊዮን ተማሪዎች  በተለያዩ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ውጪ ለመሆን ይገደዳሉ ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡ በዚህም በጦርነትቱ ሳቢያ በትግራይ ክልል ውስጥ ከተፈናቀሉትና ለችግር ከተጋለጡት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በተጨማሪ በአፋርና በአማራ ክልል ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተናግረዋል፡፡››……….{2}
  • የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል የቴሌኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤት ያስገነባው የየቴሌኮሙኒኬሽን  ማከፋፈያ ቌት መሠረተ ልማት  አስራአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ወጪ እንዲሁም የኤሌትሪክ ማከፋፈያ ቌት ትህነግ እንዳወደመው  ታውቆል፡፡ በዚህም የተነሳ የትግራይ ህዝብ በጨለማ ውስጥ እንዲኖር በትህነግ የጦር አበጋዞች ተፈርዶበታል፡፡ ከዚህ ልምድ በመውሰድ የትህነግን የጦር አበጋዞች ወደ ሌሎች ክልሎቻችን ገብተው መብራት እንዲቆረጥብን፣ ውኃ እንዲቆረጥ፣ ስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት እንዳይጠፋብን፣ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች እንዳይወድሙብን፣ ሰዎች እንዳይሞቱ፣ ህዝብ እንዳይፈናቀልና እንዳይሰደድ የትህነግን አሸባሪ ቡድን የአማራና የአፋር ህዝብ በንቃት መጠበቅና መመከት የዛሬው ትውልድ ኃላፊነት ነው፡፡

ኢትዮጵያ በጦርነት ኢኮኖሚ

ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ የዓለም የማክሮ ሞዴሎችና ትንተና ግምቶች መሠረት ኢትዮጵያ በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ  በ2021 እኤአ መጨረሻ ድረስ ወታደራዊ ወጪዋ  502 (አምስት መቶ ሁለት) ሚሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ተተንብዬል፡፡ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከ2011 እስከ 2022 እኤአ ከ466 ወደ 502 ሚሊዮኝ ዶላር እንዳደገ ይስተዋላል፡፡ በዚህም መሠረት እድገቱ

በ2011 (466) ሚሊዮን ዶላር፣በ2012 (437) ሚሊዮን ዶላር፣በ2013 (438) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2014 (477) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2015 (489) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2016 (537) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2017 (545) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2018 (560) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2019 (545) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2020 (460) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2021 (502) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2022 (475) ሚሊዮን ዶላር፣ እንደሚሆን የመረጃው ምንጭ ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ዶት ኮም ዘግቦል፡፡

Military Expenditure in Ethiopia is expected to reach 502.00 USD Million by the end of 2021, according to Trading Economics global macro models and analysts expectations. In the long-term, the Ethiopia Military Expenditure is projected to trend around 475.00 USD Million in 2022, according to our econometric models………..{3}

‹‹የኢትዮጵያ ኪስ በጦርነትና በኮቪድ ተመታ!!!››

የኢትዮጵያ ኪስ በጦርነትና በኮቪድ ተመታ!!! በማለት የዘገበው የብሪቲሽ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዜና መዋዕል በድር-ገፅ ዘግቦል፡፡ የኢትዮጵያ የአስር ወራት ጦርነት ከፍተኛ ስብዓዊ ቀውስ አስከትሎል፣ በሽህዎች የሚቆጠሩ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል አንዲሁም ብዙ ህዝብ የስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ እገዛ ይሻሉ፡፡ በአፍሪካ ሁለተኛዋ የህዝብ ቁጥር ያላት ሃገረ ኢትዮጵያ፣ በጦርነቱ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ወጪን ለመተካት ዓመታት ያስፈልጋታል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ዜጎች የወር ወጫቸው በእጥፍ መጨመሩን በሁለት ምክንያቶች እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ የመጀመሪያው በሰሜኑ የትግራይ ክልል  በጥቅምት ወር የተጀመረው ጦርነትና የኮሮና ቨይረስ ወረርሽኝ ናቸው፡፡

“Ethiopia’s 10-month war has come at a huge human cost, with thousands killed, millions displaced and many in desperate need of assistance. But that’s not the only damage being done to Africa’s second most populous nation – the war has incurred a huge economic cost, too, that could take years to repair.

In the capital Addis Ababa, citizens say their monthly expenses have doubled for two reasons: the war that broke out in the northern region of Tigray in November and the coronavirus pandemic. Official statistics show the cost of basic consumer goods has indeed gone up in Ethiopia – they were on average around a quarter more expensive in July than a year earlier.

የጦርነቱ ወጪ ግልፅ ባይሆንም ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ትንበያ መሠረት ኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ 502 (አምስት መቶ ሁለት) ሚሊዮን ዶላር በ2021 እኤአ መጨረሻ እንደሚደርስ ተተንብዬል፡፡ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከ2020 እኤአ 460 ሚሊዮን ዶላር እንደነበረ ተገልፆል፡፡ በአለፈው አመት የተባበሩት መንግሥታት ሴክረተሪ ጀነራል አንቶኒዬ ጉቴሬዝ እንዳሉት ግጭቱ ‹‹ ከሃገሪቱ የገንዘብ ግምጃ ቤት አንድ ቢሊዮን ዶላር ወጪ ያስወጣና ያራቆተ ነው›› ብለው ነበር፡፡ እንደ ዓለም ባንክ መረጃ መሠረትም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከጦርነቱና ከኮሮና ቨይረስ ወረርሽኝ በፊት የአፍሪካ ሃገራቶች ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በዓመት አሥር በመቶ ላለፉት አስር አመታቶች እስከ 2019 እኤአ ድረስ  ካስመዘገቡ   ውስጥ አንዶ እንደነበረች የዓለም ባንክ ዘግቦል፡፡

It is not clear how much the war has cost but Trading Economics forecasts military expenditure will reach $502m by the end of the year, up from $460m last year. Last week, UN secretary general Antonio Guterres said the conflict had “drained over a billion dollars from the country’s coffers”. Prior to the global pandemic and the war, Ethiopia’s economy was one of the fastest-growing in the region, expanding by an average of 10% a year in the decade to 2019, according to the World Bank. ………..{4}

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በኮሮና ቨይረስ ወረርሽኝ የጥቂት ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በከፍተኛ ደረጃ ከተጠቁ አገሮች ጋር ማወዳደር ግን ፍፁም አይቻልም፡፡ ለምሳሌ በኮሮና ቨይረስ ወረርሽኝ የሞቾች ቁጥር  በአሜሪካ (640,000 ሽህ ሰዎች)፣ በህንድ (439,000)፣ በብራዚል (580,000)፣ በራሽያ (180,000)፣ በእንግሊዝ (133,000 ሽህ ሰዎች)፣ በፈረንሳይ (4.53 ሽህ ሰዎች)፣ በጀርመን (92,229 ሽህ ሰዎች)፣ በቅዲስቲቷ ኢትዮጵያ በኮሮና ቨይረስ ወረርሽኝ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 4,675 ሽህ ሰዎች ብቻ ሆነው ሳለ ‹‹የኢትዮጵያ ኪስ በጦርነትና በኮቪድ ተመታ!!!›› ብሎ መዘገብ የውሸት ዜና ይሆናል፡፡

 

 

ምንጭ

{1} መንግሥት ከአገር ውስጥና ከውጭ የተበደረው ውዝፍ የዕዳ መጠን 2.4 ትሪሊዮን ብር ደረሰ/1 September 2

{2} በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከ7 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች መውደማቸው ተነገረ/31 ነሐሴ 2021

{3} Ethiopia Military Expenditure – Forecast (tradingeconomics.com)

{4} Ethiopians’ Pockets Hit by War and Covid// August 31,2021/ BBC

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop