August 26, 2021
9 mins read

ኢትዮጵያዊነት እና ህዝባዊነት ከወዴት ናቸዉ ?

ዕዉነት ለኢትዮጵያዊነት እና ብሄራዊ አንድነት መኖር እና ማበብ የሚያሳስበዉ ካለዉ የቀደመዉን የታሪክ ዉርስ እና የቀደሙትን ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እና ብሄራዊ ኩራት ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉትን በህይወት የሚገኙትን ሆነ በመስዋዕትነት ያለፉትን ገድል እና ስራ ለማዉሳት እና ከታሪክ ለመማር እንሞክር፡፡

የዛሬዋን ኢትዮጵያ እና ዜጎች ሞት እና ዉርደት ላለማየት ከዘመናት አስቀድሞ ከፍተኛ መስዋዕት የከፈሉትን እያጥላላን ላለፉት  ግማሽ ክ/ዘመናት የፀረ ኅዝብ እና አንድነት ኃይሎችን  ዕኩይ እና ድብቅ ሴራቸዉን እያለባበስን  ያልሰሩትን ሰሩ የማለቱን  አድር ባይነት በቃ ማለት አለብን፡፡

ስለኢትዮጵያ  አንድነት እና የሕዝቦች ብሄራዊ ጥቅም እና ከብር በብርቱ የሰሩትን  ለምሳሌ እንደ ቀድሞዉ የኢትዮጵያ  መሪ ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም በስልጣን ዘመናቸዉ  እንደ ነብይ የተናገሩት ዛሬ ከ40 ዓመት በፊት ከተናገሩት የጥፋት ኃይሎች ተልዕኮ ዕጥፍ  ጥፋት፣ ክህደት፣ ሞት፣ ስደት እና ዉርደት እያየን  ስለ ዕርሳቸዉ አርቆ አስተዋይነት፣ ብሄራዊ እና ህዝባዊ ስሜት  እዳንመሰክር ፤እንዳንናገር  በት.ህ.ነ.ግ.ኢህዴግ  ግዝት እና ባርነት አስተሳሰብ እንደተቀፈደድን ያሳያል፡፡

የኢትዮጵያን ዕዉነተኛ እና ታሪካዊ ጠላቶች  ለማወቅ እና ለአንዴ እና ለመጨረሻ ለመጠንቀቅ፣ ለመታጠቅ እና ለመጠበቅ  በህይወት ከሚገኙ የኢትዮጵያ መሪዎች ዉስጥ  ከኮ/ል መንግስት ኃ/ማርያም ዉጭ ማን ሊሆን ይችላል፡፡

አገር እና ህዝብ ክዶ ለዘመናት ለባዕድ እና ጠላት ህዘቡን ለባርነት እና ምድሯን፤ግዛቷን  ለግዞት አሳልፈዉ ለሰጡ የታሪክ  ዕንክረዳዶች  የግል ንብረት የሆነች አገር   ለሞቱላት  ጀግኖች የምትሆን አስከ መቸ ነዉ ፡፡

ዕኮ ዕዉነተኛ ኢትዮጵያዊነት እና ህዝባዊነት የሚሰማዉ ካለ ፡-

ት.ህ.ነ.ግ እና ግብረ አበሮች ለግማሽ ክ/ዘመናት ከትግል አስከ ዛሬ  ላደረሰዉ እና እያደረሰ ላለዉ

፩) የአገር ከህደት፣

፪) የአገር እና ህዝብ ሀብት በመዝረፍ፣

፫) በኢትዮጵያዊነት እና ማንነት መሰረት ያደረገ የአጥፍቶ ጠፊነት ተግባሩን በመረጃ በማስደገፍ ይህም በቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግስት  አመራር ( ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም) …….)፣የፅሁፍ ሠነዶች፣ የምስል ማስረጃዎችን…..በማጠናከር ፡-

  • በዘር ፍጅት እና በአገር ክህደት ወንጀል (ላለፉት 50 ዓመታት) እንዲጠየቁ፣
  • የአንድ አገር ህዝብን ጠላት እና ወዳጂ  አድርጎ በመፈረጂ አንድን ህዝብ በማንነት፣ በዕምነት እና  በዕዉነት ላይ ዘመቻ በማድረግ በፖለቲካ፣ በባህል፣ በሀብት ማፍራት/ኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የጥላቻ ዘመቻ ማድረግ፣
  • የኢትዮጵያን አንድነት ለማናጋት  እና በዚህም ጠላት አዲስ አገር ምስረታ የሚሆን የመስፋፋት እና የማጥፋት ዘመቻ እና ተጠቅሶ ተጠያቂ እንዲሆን፣
  • ባለፉት የሞት እና የጥፋት ዘመናት (፳፯+፫) ከአጥፍቶ ጠፊዎች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለተባበሩት እና ላስተባበሩት ሁሉ በግልም ሆነ በቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንዲይቁ፣
  • ለ ፴ ዓመት በኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም በአማራ ህብረተሰብ  ላይ ለደረሰ  ሞት ፣ፍጅት፣ ዘረፋ ፣ ስደት….. ካሳ  እንዲጠየቅ እና እንዲከፈል፣
  • ለ ፴ ዓመት በዓማራ ህዝብ ላይ በተለያዩ የአገሪቱ ግዛቶች እና አስተዳደሮች  ለደረሰዉ ሠባዊ እና ቁሳዊ በደል እና መግደል ፤ማስገደል ፣በሰዉ ልጅ ላይ በማንነት እና አመለካከት ለይቶ የማጥፋት ዕልቂት (holocaust)…….የተደራጀ እና የተቀናጀ  የዓመታት  ሴራ  ሰማዕት  መታሰቢያ በብሄራዊ ደረጃ እንዲደረግ ማድረግ  ይገባል፡፡

ከዚህ ጋር በአሁኑ ጊዜ የብሄራዊ አንድነት እና የህዝብ ህልዉና ለመከላከል፣ለመጠበቅ እና ለማስጠበቅ የሚደረገዉ ታሪካዊ ተጋድሎ  የፊት ለፊት ትግል በተጨማሪ የአገር አፍራሽ  ጠላት እና የጠላት መሳሪያዎች የጥፋት ጉልበት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ምንጭ የሆኑትን (በመንግስት ሆነ በግል ድርጅት ስም) መለየት እና መንጭነታቸዉን ማንጠፍ ያስፈልጋል፡፡

ከዚህም በላይ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ለዘመናት ዘመቻ ጥፋት ላካሄዱ እና ለሚያካሂዱ የሀብት እና ንብረት ምንጭ ከሆኑት ድርጅቶች ምርት ላይ በማንኛዉም መንገድ ማዕቀብ ( አለመጠቀም፣ አለመግዛት፣ አለማበረታት……) የዕዉነተኛ ኢትዮጵያዊነት አንዱ እና ዋነኛዉ የጠላት ማክሰሚያ ስልት መሆኑን መገንዘብ እና መተግበር ያስፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ላለፉት ፳፯ ዓመታት  ከሰደማይ በታች በኢትዮጵያ እና በመላዉ ዓለም በኢትዮጵያ ህዝብ ስም የነበሩ እና ያሉ የእርሻ፣የንግድ፣ የአገልግሎት ፣የፖለቲካ፣ የመንግስት መዋቅር፣ የዕምነት እና ኃይማኖት ተቋማት ሳይቀሩ  ሳር ቅጠሉ በት፤ህ.ነ.ግ. እና የኢትዮጵያዊነት ጥላቻ ያዛመዳቸዉ ተባባሪ አጥፍቶ ጠፊዎች ዕዝ ስር የነበሩ እና ያሉ እንደመሆናቸዉ ያለምንም ማመንታት ወደ ህዝብ ( ብሄራዊ ) ሀብት ማዛወር ያስፈልጋል፡፡

ዕዉነተኛ ኢትዮጵያዊነት እና ህዝባዊነት የሚመጣበት ቁርጠኛ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት እንዲኖር  ለማድረግ ህዝባዊነት የሚሰማዉ አመራር እና ትዉልድ የሚመጣበትን ጊዜ መናፈቅ እና መጠየቅ  የኢትዮጵያዊነት እና ሠባዊነት ወቅታዊ  መገለጫዎች ናቸዉ ፡፡

 ይህን ዕዉነተኛ ሁነት እና ድርጊት ዛሬ ላይ ሆኖ አለመመስከር እና አለመመስከር  የምንለዉ  ዕዉነተኛ ኢትዮጵያዊነት እና ታላቅነት ከአፍ የማያልፍ ዕዉነት እና ታሪክ የማዘነፍ  ታሪካዊ ስህተት መደጋገም ነዉ ፡፡

“  አንድነት ኃይል ነዉ ”

ማላጂ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop

Don't Miss

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ! – ማላጅ

ኢትዮጵያ ….ኢትዮጵያ እያለ በቃላት  የሚጠሩት ዕልፍ አዕላፍ ናቸዉ ትናትም ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? – አንዱ ዓለም ተፈራ

ሰኞ፣ ሰኔ ፳፰ ቀን፣ ፳፻፲፫ ዓ. ም. (7/5/2021) ነፃ አስተያየት፤