ኢትዮጵያ ….ኢትዮጵያ እያለ በቃላት የሚጠሩት ዕልፍ አዕላፍ ናቸዉ ትናትም ኢትዮጵያ ሲሉ በልባቸዉ የጥላቻ እና የጥፋት ቋጠሮ ሸክፈዉ ለዉድቀቷ ከዉስጥ እና ከዉጭ ጠላት ጋር ህብረት ፈጥረዉ የሚኳትኑት ልክ በአፍ አገር እያሉ በስራቸዉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን አይንህ ካፈር የሚሉት ናቸዉ ፡፡
እነኝህ ወንዙን ካናቱ በማደፍረስ ከዘመናት የዜጎች ስቃይ የፖለቲካ ንግድ አትራፊዎችን ይዞ የደፈረሰዉን የወንዝ ዉኃ ለማጣራት መሞከር የዚህችን አገር እና ህዝብ የመከራ ዘመን እንዲራዘም አድርጎታል ፡፡
ባለንበት ዘመን ለዓመታት አንድን ህዝብ ከሌላዉ ህዝብ ለይቶ በማጥቃት ለስደት፣ ድህነት እና ሞት ለጥቃት መሳሪያነት በማገልገል ላይ የሚገኘዉ የ1987 ዓ.ም. ህገ መንግስት በፅንሰ ሀሳብ ደረጃ ካለፉት ዘመናት በነበሩ የኢትዮጵያ መንግስታት ህገ መንግስት ተመሳሳይነት ያለዉ ቢሆንም በተግባራዊነቱ፣ በአሳታፊነቱ / አካታችነቱም ሆነ በልዩነቱ ላይ ግምት ባለመስጠት ከዉስጥ ችግር አልፎ ለዉጭ ጠላት የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ፣ የመኖር መብት ፣ የአገር ባለቤትነት የመሳሰሉትን አደጋ ዉስጥ ከማስገባቱ በላይ የብሄራዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት ላይ የዉጭ ዓለም ጣልቃ ገብነት መንስዔ ሆኗል ፡፡
ለዚህም በማዕከላዊ መንግስት እና በትግራይ ክልል ለተነሳዉ ለወራት የዘለቀ ግጭት መፍተሄ መራቅም ሆነ ለምዕራባዉያን በሉዓላዊት አገር የዉስጥ ጉዳይ ዉሻ በቀደደዉ ጅብ… እንዲሉ በተለይም የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ እና ህዝቧ ጉዳይ ላይ ሌት ተቀን ተግተዉ ስራዉ ብዙ በመሆን በአገር ክህደት እና በዘር ፍጅት ሊጠየቅ የሚገባን አካል በእኛ ድክመት ዋስ እና ጠበቃ ሆናለች(አሜሪካ)፡፡ በዝርዝር ሲገለጥ አሜሪካ የኤርትራ እና የአጎራባች ክልል ( አማር) የፀጥታ ኃይል ይዉጣ በማለት ሲወተዉቱ መቆየት ፡፡ ከዚህ ቀጥለዉ ብሄራዊ የመከላከያ ኃይል ከትግራይ እንዲወጣ በቀጥታም ሆነ በእጅ አዙር ምዕራባዉያን እና የዕኛ አሜን ማለት ከህገ መንግስቱ ይዘት የሚመነጭ መሆኑን ያሳያል ፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጦር ከትግራይ እንደወጣ ደግሞ ኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ መንግስት በአግባቡ ትርጉሙንም ሆነ ጣዕሙን የማያዉቁትን እና ጥርስ ያስገባቸዉን ህገመንግስት ከዚህ የሚቀዳዉን የክልል አስተዳደር በመጥቀስ የዓማራ ክልል የፀጥታ ኃይል( የኢትዮጵያ ጠባቂ ቢባል የማያንስበትን) ከቅድመ ግጭት(የማዕከላዊ መንግስት እና ትግራይ) ወደነበረበት ይመለስ ህገ መነግስቱ ይከበር ባይ ሆናለች ( አሜሪካ)፡፡
ይህን የሚሉት የዉጭ እና የዉስጥ ጠላቶች የኢትዮጵያን እና ህዝቧን አንድነት እና ደህንነት ሳይሆን የሚየሳስባቸዉ የራሳቸዉን ጥቅም ማስጠበቅ እና ማስቀጠል መሆኑን አሳይ ነዉ ፡፡
ኢትዮጵያ ዉስጥ በየትኛዉም ዓለም ክፍል ያልደረሰ በኢትዮጵያዉያን ያልደረሰ ኢሰባዊ ግፍ ፣ ጅምላ ፍጅት ፣ ምዝበራ ያስከተለዉ ድህነት ማስከተሉን ዕያወቁ ጠላቶች ለ27 ዓመት ያሉት አልነበረም ፡፡
አሜሪካ የባህር በር የነበራት አገር ኢትዮጵያ ባህር በር እንድታጣ ከማድረጓ በተጨማሪም ኢትዮጵያ የብስ መገናኛ እናዳይኖራት በጎንደር እና በጎጃም መተከልን ከዓመታት በፊት መነጠል የዚህ ሤራ አካል እንደነበር መረሳት የለበትም ፡፡
የሚያሳዝነዉ ግን ዛሬ ኢትዮጵያን እና ኤርትራ ዝም በሉ አይናችሁን ጨፍኑ የሚለዉ የት.ህ.ነ.ግ. ዋስ እና እንደራሴዎች ምን ያህል ለኢትዮጵያ እና ህዝቦች ያላቸዉ ስጋት እና ንቀት ስር የሰደደ መሆኑን አመላካች ነዉ ፡፡
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ዕድል እና ታላቅነት እንጅ ወንጀል ሆኖ በአስተሳሰብም ሆነ በድርጊት የመቀጠሉ ሚስጢር እና ምንጭ የሕገ መንግሰቱ እና ክልላዊ አደረጃጀቱ መሆኑ እና ይህም በዜጎች ላይ ለዘመናት የደረሰዉ ኢሰባዊ ( ስደት፣ ሞት ፣ፍጅት…….) ጥፋት ባለቤት ለሆኑት ቁርጠኛ እና የማያዳግም ዕርምጃ ባለመወሰዱ ነዉ ፡፡
በተለይ የህገ መንግስቱ የ 1987 ዓ.ም አንቀፅ ፪፣ ፲፮፣፴፱ እና ፵፮ በተከታታይ ስለ ኢትዮጵያ የወሰን አስተዳር ድንበር በዓለም ዓቀፍ ስምምነት ፣ የዜጎች የግል ጥበቃ መብት፣አስከመገንጠል ፣የክልል አስተዳደር ወሰን በኗሪ ዜጎች ማንነት እና ስምምነት ላይ ተመስርቶ መሆን እንዳለበት የሚያትት ቢሆንም ዛሬ እኛ እና አገሪቷ አሁን የምንገኝበት ሁኔታ ለዓመታት ከደረሰዉ እና ካለዉ አኳያ ማየት ይቻላል፡፡
ስለዚህ ሁሉም ነገር ባአገር ስለሆነ እና አገርም ሠዉ በመሆኑ አገር እየሞተ እና ዕለታዊ መሆኑ ማቆም ዕዉነተኛዉ ኢትዮጵያን የማስቀጠል እና ወደ ታላቅነት ለማምጣት ህገ መንግቱን ጨምሮ ሌሎች በተጨባጭ መወሰድ ያለባቸዉ እና መከፈል ያለበት ዋጋ ሁሉ ሊከፈል ይገባል ፡፡
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ሳይነጣጠሉ የሚኖሩ እንጅ ዜጎችን በማሳደድ ምድረ በዳ መሬት መፈለግ ጤናማነት ብቻ ሳይሆን ለአገር አንድነት የሚደረገዉን ርብርብ እና ሊኖር የሚገባዉ ብሄራዊ ጥቅም ማምጣት ባዶ ህልም ( ቅዠት) ይሆናል ፡፡
ማላጅ
“አንድነት ኃይል ነዉ !!”
Unity is power