“የአሸባሪው ታጣቂዎች ትግራይ የኢትዮጵያ አይደለችም የሚሉ ጽሁፎችን በየግድግዳው ጽፈው ሄደዋል August 25, 2021 ዜና ” - ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ ጥላሁን በሰሜን ምእራብ እዝ የኮር አንድ አዛዥ Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ ጥላሁን በጋይንት በኩል የማጥቃት እርምጃ የተወሰደባቸው የአሸባሪው ኃይሎች “ትግራይ የኢትዮጵያ አይደለችም” የሚል ጽሁፎችን በየግድግዳው ጽፈው መፈርጠጣቸውን ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ ጥላሁን ገለጹ፡፡ አሸባሪው የህዝቡን ሀብት ጨምሮ በርካታ መሠረተ ልማቶችን እንዳወደመም አስታወቁ፡፡ በሰሜን ምእራብ እዝ የኮር አንድ አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ ጥላሁን ትላንት በነፋስ መውጫ ጨጨሆ ግምባር ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ አሸባሪው በሰሜን ጎንደር በተለይም በጋይንት በኩል አድርጎ ወደ ደብረ ታቦር ለመግባት ያደረገው ሙከራ ከሽፎበት የማጥቃት እርምጃ ተወስዶበታል፡፡ ቡድኑ ባለፈባቸው አካባቢዎች ሁሉ “ትግራይ የኢትዮጵያ አይደለችም”፤ “ኢትዮጵያ የኛ አይደለችም” የሚሉ የጽሁፍ መልዕክቶችን በየግድግዳው ላይ ጽፎ መሄዱን ያስታወቁት ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ፤ ይህ ምን ያህል አገር ጠል መሆኑን ያመላከተ ነው ሲሉ አስታውቀዋል። እንደ ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ ገለጻ፤ አሸባሪው ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች ኢትዮጵያ ጠል መሆኑን በግልጽ አሳይቷል፡፡ኢትዮጵያ የኛ አይደለችም ከሚለው መልዕክቱ ባሻገር፤ በጋሳኝ፣ በክምር ድንጋይና ነፋስ መውጫ፤ የግለሰብ ንብረት ዘርፏል፡፡የህዝቡን ሀብት ጨምሮ በርካታ መሠረተ ልማቶችን አውድሟል፡፡ ዓላማውም ማውደም ስለሆነ ጸረ መንግሥት መሆን ብቻ ሳይሆን ጸረ አገርና ጸረ ህዝብ መሆኑንም አሳይቷል፡፡ በዚህ መሠረት ሱቆችንና ድሆች የሚጠቀሙበት እለታዊ ፍጆታቸውን ሳይቀር በመዝረፍ ሰብዓዊ ቀውስ ማድረሱን የገለጹት ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ ፤ ለዚህ ምላሽ ሠራዊቱ አሸባሪውን እየቀጣ በአሁኑ ወቅትም በነፋስ መውጫ ጨጨሆ ግምባር ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡ (ኢ ፕ ድ ) Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story አሸባሪው ህወሓት በነፋስ መውጫ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ዘርፎ፣ አውድሞና የባንኩን የጥበቃ ሠራተኛ ገድሏል Next Story ሞደርና ኮቪድ-19 ክትባት ከሌሎች ክትባቶች በምን ይለያል?