አሸባሪው ህወሓት በነፋስ መውጫ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ዘርፎ፣ አውድሞና የባንኩን የጥበቃ ሠራተኛ ገድሏል

በጋይንት ነፋስ መውጫ ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገብርዬ ቅርንጫፍ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ሙሉ ለሙሉ ተዘርፎ መውደሙን የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ አለምነው ስዩም ገለፁ፡፡
አቶ አለምነው በሥፍራው ለሚገኙት ዘጋቢዎችን እንደገለጹት፤ አሸባሪው ህወሓት ባንኩን በመሳሪያ በመደብድብ የኤቲ ኤም ማሽኑን ጨምሮ የባንኩን ቋሚ ሀብቶች ሙሉ ለሙሉ አውድሞታል፡፡
3444
3444

የአሸባሪው ታጣቂዎች የዘረፉትን ገንዘብ ሳይጨምር ከአንድ ነጥብ ስምንት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሀብት ኪሳራ አድርሰዋል፡፡

አቶ አለምነው እንዳሉት፤ አሸባሪው የተቋሙንና የግለሰቦችን መረጃ የያዙ ፋይሎችን፣ ኮምፒዩተሮችን፣ የዳታ ሰርቨሩን፣ ጠረጴዛና ወንበሮችን ጨምሮ አጠቃላይ የባንኩ ንብረት ላይ ኪሳራ አድርሷል፡፡
ቋሚ ንብረቶችን ከማውደሙ በተጨማሪ ካዝና ውስጥ ከነበረው ገንዘብ ውጭ በኤቴም ማሽን ውስጥ ያለውንም ሰብሮ ዘርፏል፡፡
የአሸባሪው ታጣቂዎች የባንኩን ጥበቃ ሠራተኛ አንደገደሉትም ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው ዝርፊያ ለማድረስ በርካታ ቁጥር ያላቸው ህጸናትን ይዞ ሲንቀሳቀስ እንደነበርና የመከላከያ ሠራዊትና የልዩ ሀይል አባላት በፈጸሙት ተጋድሎ አካባቢውን ማስለቀቅ እንደተቻለም የባንኩን ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ጠቅሶ ኢፕድ ዘግቧል፡፡
በአሁኑ ወቅት የነፋስ መውጫ ከተማ ሙሉ ለሙሉ ከአሸባሪው ነጻ ወጥታ ማህበረሰቡ ሠለማዊ ኑሮውን ለመምራት እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
ተጨማሪ ያንብቡ:  የ ኢትዮጵያውያን ማህበረስብ በቤልጅግ በአምስተርዳም ከተማ ሕዝባዊ ስበስባ ጠራ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share