ጥላቻ አስከ ዕለተ “ፍች እና ሞት” መባቻ – ማላጂ

tplf nazi
tplf nazi

በዝቅተኝነት ስሜት ዉስጠ ማንነቱ ሰለሊት እንደበላዉ ሽክላ  የደበዘዘዉ እና ያደፈዉ ፀረ ኅዝብ እና አገር የፈለገዉን ቢል ፤ያሻዉን ቢደርግ   ይህ ከዘመናት አስቀድሞ የተጠነሰሰ ዕድሜ ጠገብ ሴራ በመሆኑ በድንገት እንደሆነ አድርጎ ማቅረብ ጠላት ምኞቱን ለማሳካት የሚያደርገዉን ዘመቻ እንደመደገፍ ነዉ ፡፡

የት.ህ.ነ.ግ   የጥፋት ኃይል እና ግብረ አበሮች በስያሜ ካልሆነ በንግባርም ሆነ በተግባር አንድ መሆናቸዉን ያስመሰከሩት ገና ከመነሻቸዉ በ1960 ዓ.ም መጀመሪ ኢትዮጵያን ለማክሰም እና እና የራሳቸዉን የምኞት ዓለም  ለመመስረት ብቸኛዉ መንገድ ኢትዮጵያዊነት ማንነት ላይ የጥላቻ እና የበቀል ዕንክርዳድ መዝራት እና ማሳደግ ነበር ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የሚታየዉ  የአጥፍቶ መጥፋት ትንቅንቅ ካለፉት 50 ዓመታት ከተከተለሏቸዉ እና ከተገበሯቸዉ ኢትዮጵያን የማዳከም ዘመቻ የሚለየዉ የመጨረሻዉ እና ከጥፋት ተባባሪወቻቸዉ ያገኑትን የተስፋ ቃል ከዳር ማድረስ ወይም ከዚህ በተቃራኒ የሆነዉን “ላልበለዉ ጭሬ ላጥፋዉ” ያለችዉን ዶሮ መርህ መከተል ነበር ፤ነዉ ፡፡

በትግል መነሻ ቃል ኪዳን / መርህ ጨቋኝ  እና ተጨቋኝ ህዝብ ብሎ የከፋፈለ  በቀድሞዎ መንግስት  አጥፍቶ ፤ጠፊ ፣ ተገንጣይ ከተባለ ድፍን 50 ዓመት ሲሞላዉ በህዝብ ስም መንበረ ስልጣን ይዞ ህዝብን ለጅምላ ፍጅት፣ በአገር አንድነት ክህደት እና መሰል ኢሰባዊ ግፍ የፈፀመ እና እየፈፀመ ላለ እንደ ድንገት ጉዳዩን ማጓን የህልዉና እና የብሄራዊ አንድነት ትግሉን  ግለት መአቀዝቀዝ ነዉ ፡፡

ጠላት በኢትዮጵያ አንድነትም ሆነ ታሪካዊ ምንነት ላይ አንድም ቀን ዕምነት እንዳልነበረዉ እና ከዚያ ይልቅ “የተዉሶ በሬ ወደ መጣበት ይስባል ”እንዲሉ  በህዝብ እና በአገር ሀብት የት ፤ለማን እና ምን እንደሰራ ለሚያዉቅ የወቅቱ የጥላቻ ጋብቻ ላስረሳሰራቸዉ ሁሉ ፍላጎታቸዉም ሆነ ምኞታቸዉ በኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ዓማራ በሚሉት ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያ ዉድቀት ላይ የራሳቸዉን ጎጆ መቀለስ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም ፡፡

ዜጎችን በዕምነታቸዉ ፣ በማንነታቸዉ  እና ሠዉ በመሆናቸዉ በተደራጀ እና መንግስታዊ መመሪያ እና ድጋፍ እየተሰጠበት ሲገደሉ፣ ሲሳደዱ ፣ በማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮች  ሲገለሉ የመኖሩ ጉዳይ ሚስጥር እና አሁናዊ ሳይሆን የነባር ሴራ ዉጤት ነዉ ፡፡

በዓለማችን ላይ ዕዉነተኛ ዳኝነት እና ፍትህ ቢኖር ያለፉት ሶስት ዓመታትን ትተን የቀደሙት ከሁለት አሰርተ ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ የደረሰዉ መጠነ ሰፊ በደል ለዚያዉም በራሱ አገር ፣ ህዝብ ላይ አስተዳደረዋለሁ ፤እወክለዋለሁ በሚል መንግስት በቀል የደረሰበት ምድር ከኢትዮጵያ ዉጭ ሌላ አገር ሊኖር ስለመቻሉ አላዉቅም፡፡

በመኖሪያ ቤቱ፣ በአደባባይ፣ በዱር በገደሉ …….በጭካኔ እና በግፍ በዕብሪት እና በትዕቢት ህዘብ እና አገር የአገሳቆለ ት.ህ.ነ.ግ / ኢህዴግ ዉጭ ማን ነበር ፡፡

እናም ከሰሞኑ የማደናገሪያ ቧልቶች አንዳንዶች የሚያዝ ጠላት ህግ ይቅረብ፣ ተስፋፊዉ እና አጥፊዉ ትህነግ አዲስ አበባ ለመግባት የነበረዉ ህልሙ ተዳፈነ ፣ ወደ መጣበት ይመለስ፣ ከወረራቸዉ የኢትዮጵያ ግዛቶች ይዉጣ ማሳሰቢያ፣ ድርድር…….ስንቱ ይጠቀስ ….እነዚህ ሌላ የኢትዮጵያን እና ህዝቧን የመከራ ዘመን ለማራዘም እና ወራሪ ፣ተስፋፊ እና አጥፊ ኃይል ለመጨረሻዉ ህልሙ ( አዲስ አገር ምስረታ) መደላድል መፍጠር እና ጊዜ የመግዣ መደንቆሪያ እና ማደናገሪያ ነዉ ፡፡

ጠላት ለመግደል እና ለመገንጠል ህዝብ እና አገር ሲያምስ ህግ እና ህግ አስፈጻሚ በተወረሩ እና በተመዘበሩ አካባቢዎች ስላልነበር አይደለም ፡፡ ነገር ግን አንድም ተስፋፊዉ የጥፋት ቡድን/ኃይል  በኢትዮጵያ ህግ እንደማይገዛ ከ፪ ዓመት አስቀድሞ በይፋ አረጋግጧል፡፡

ሁለተኛዉ በመጨረሻዉ የመለየት ሰዓት  ለዘመናት በጥላቻ ጋብቻ ከተሳሰራቸዉ ግብረ አበሮች ጋር የሞት ሽረት ትግል አድርጎ ማዕከላዊ ኢትዮጵያን ከመሰረት ለመናድ ምሰሶዉ በጠላቶች አመለካከት ዓማራን ማክሰም በሚል የጥፋት ቃል ኪዳን የመጨረሻዉ መጨረሻ የሆነዉን ትንቅንቅ ማድረግ እንደነበር በገቢር ታይቷል ፡፡ “ሆድ ያበዉን ጌሾ ያወጠዋል”እንዲሉ አበዉ   ፡፡

እናም የጥፋት ሰይፍ እና ጦር ይዞ አገር ለማጥፋት ላይ ታች የሚልን ጠላት እሽሩሩ ብሎ  በህግ……ወዘተ ማለት በብርቱ ዜጎች መስዋዕትነት የምተገኝ አገርን እና ለዘመናት የመከራ ቋጥኝ የተጫነበት ህዝብ ለሚያደርገዉ የመኖር አለመኖር እና ብሄራዊ ክብር ተጋድሎ ማሳነስ ብሎም መድበስበስ እንዳይሆን በየትኛዉም ጊዜ እና ረገድ ጥንቃቄ ሊወሰድበት ይገባል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቁርጠኛ እና በመከራ ጊዜ አለኝታነታቸዉን በተግባር ያስመሰከሩ እና እያስመሰከሩ ያሉ ኢትዮጵያዉያን  ገድለ ታሪካቸዉ እንደ ንጋት ኮከብ የሚደምቅበት ጊዜ ምዕራፍ ላይ እንደመገኘታችን  ከዚህ በተቃርኖ በልማድ እና በዘመነ ኦሪት የጠጫኑትን ባርነት ቀንበር እንደተሸከሙ  ከህዝብ ኋላ ሆነዉ እየተጎተቱ ህዝባዊ ታግድሎዉን እና ብሄራዊ ድሉን የሚጎትቱ ከዉስጥ እና ከዉጭ ፣ ከሩቅ እና ቅርብ  መኖራቸዉን እያወቅን ለአፍታ ለራስ ፣ ለወገን እና ለአገር ክብር እና ዳር ድንበር  በዓላማ እና በፅናት በህብረት ሁላችንም ለሁላችን ዘብ መቆም ያለብን ዛሬ አሱም አሁን ነዉ ፡፡

በመጨረሻም የህዝብ እና የአገር ጠላት በጥላቻ ተጠንስሶ ፣ በጥላቻ ገስግሶ  ከፍላጎቱ እና ምኞቱ ዉጭ የሚለዉን ሁሉ እንዳልነበር ማድረግ  ሲወለድ ያጠለቀዉን ሲሞት ያወልቀዋል እንዲሉ “ጥላቻ አስከ ዕለተ ፍች እና ሞት መባቻ ” ነዉና መቸም ፣የትም ፣ በምንም ፣ በማንም  አለመዘናጋት ለዓላማ መኖር ነዉ ፡

አንድነት ኃይል ነዉ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወለፌንድ አገዛዝ፦ በረመዳን እሥር፣ በዒድ-አልፊጥር ግድያ

ማላጂ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share